2017 ኖቬምበር 25, ቅዳሜ

የምዕራፍ ሁለት/2/የ18ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

*_በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፫_*

_የምዕራፍ ሁለት/የ18ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቆና መልስ_⤵⤵⤵⤵

✅1⃣ ➡ታላቁ ንጉሥ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንደተባለ ብዙ ጌዜ ሰምተናል ዳዊትን ለመጀመርያ ጊዜ ልበ አምላክ ብሎ የጠራው ነብይ ማነው? ለሁለተኛ ጊዜ ልበ አምላክ ዳዊት ብሎ የጠራው ሐዋርያስ ምን ይባላል?? ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ???

*//መልስ//👉ነብዩ ሳሙኤል ነው። (1ኛ ሳሙ13፥13*)

*ቅዱስ ጳውሎስ ነው። (የሐዋርያት ስራ13÷ 22ላይን*)

✅2⃣ ➡እኔ ማነኝ ?
ምድያማውያን እስራኤልን ሲወሩ እንዳልታይ በወይን መጭመቂያ ስፍራ ስንዴ አበጥር ነበር የእግዚአብሔር መልእክተኛ ተገለጠና አንተ ሀያል ሰው እግዚአብሔር ካንተጋር ነው አለኝ መልአኩ ተገልጦ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው ስላለኝም ምድያማውያን በ300 ችቦ ድል አደረኳቸው ይህ ሁሉ ታሪክ ያለኝ እኔ ማነኝ??

*//መልስ//*.👉  *ጌድዮን*

✅3⃣➡  የሶምሶን ሀይል በፀጉሩ ላይ እንዳለ ሚስጥር ያወጣችበት ሴት ማን ትባላለች??

*//መልስ*//* 👉 *ደሊላ*

✅4⃣ ➡ሳዖል ዳዊትን ብዙ ጊዜ ሲያሳድደው  ዳዊት ግን እግዚአብሔር የቀባውን እራሱ   እስኪንቀው ድረስ አልገልግም እያለ መግደል ሲችል አልፎታል በ፩ድ ወቅት ሳዖል በዋሻ ውስጥ  እያለ ዳዊት ወደ እርሱ ቀረበና የሚገርም ነገር ሰርቶ ነበር። ምን ይሆን??

*መልስ የሳዖልን ልብስ ለምልክትነት ተቆርጦ አሳየው ከአጠገቡ የነበረውን ኮዳና ሰይፍ ለምልክትነት ወስዶ አሳየው (1ኛ ሳሙ 24 ፥ 1 1ኛ ሳሙ 26፥8*)


✅5⃣ ➡አንድ መስፍን ጦርነት ወጥቼ በድል ብመለስ ሊቀበለኝ የሚወጣውን ማንኛውንም ሰው መስእዋት አርጌ አቀርባውለ አለ እንዳለውም ከጦርነቱ በድል ሲመለስ ለአይኑ ማረፊያ የሆነችውን አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና ከበሮ እየመታች ልትቀበለው እሮጠች ያ ሰው ግን ከሩቅ አያትና አዘነ ልጅንም መስእዋት ትሁን ብሏልና አቃጠላት ይህ ልመና የማይችልበት ሰው ማን ይባላል?

*//መልስ//👉መስፍን ዮፍታሔ ነው።( መሳፍንት 11፥ 31*)

✅6⃣ ➡አንዳንድ ጊዜ ለቅዱሳን መስገድ ለማን ይበጃል የሚሉ ጥቂት አይዱሉም መፅሀፍ ቅዱስ ግን የነብያት ማህበር እኛም እኮ ነብያት ነን ሳይሉ ለንብዩ ኤልሳዕ ሰገዱ ይሉናን። ነብያት ለኤልሳዕ የሰገዱት በምን ምክንያት ነበር??

*//መልስ//👉 መንፈስ በኤልሳዕ ላይ እጥፍ ሆኖ ስላደረበትና በመጎናፀፊያው ዮርዳኖስን ሲከፍል አይተው ነብያቱ ለኤልሳዕ ሰገዱ 2ኛ ነገሥት 2፥15*

✅7⃣ ➡ንጉሥ ሲሳራ እስራኤልን ለ20 አመት አስጨንቆ ገዝቷት ነበር አንዲት። ሴት ነብይ ባርቅን አስተርታ ተነሳ እግዚአብሔር ሲሳራን በእጅህ ጥሎልሃል አለችው ባርቅም አንች አብረሽኝ ካልሔድሽ አልነሳም አለ ያች ሴት ነብይም ባርቅን አስከትላ ወደ ታቦር ተራራ ወጣችና ሲሳራን ድል አደረጉ ይህች ሴት ነብይት ማን ትባላለች???

*//መልስ// 👉ዲቦራ ናት የስሟ ትርጉም ንብ ማለት ነው ይህንን ታሪክ  መዝሙር ላይ ዲቦራና ባርቅ እያልን በብዛት እንዘምረዋለን መሳፍንት 4፥1*

✅8⃣ ➡እስራኤላውያን በባቢሎን ከተወረሩ ቡኋላ ህዝበ እስራኤል ወደ ባቢሎን ፈለሱ ጥቂት እስራኤላውያን ግን በእስራኤል ቀሩ ናቡከደነጾር በእስራኤል ለቀሩት ህዝብ  ንጉሥ ያደረገው ማንን ነበር??

*// መልስ//👉ጎዶልያስ ነው 2ኛ ነገስት 25 ፥23*


✅ 9⃣➡የኢያሪኮ ውሀ መመረዙ ምክንያት የከተማዋ ነዋሪዎች እጅግ ተቸገሩ ወደ ነብዮ ኤልያስም ቀረቡና እነሆ የከተማዋ ኑሮ መልካም ነው ውሀዋ ግን መራራ ነው የኢያሪኮ ውሀ መራራ ነው ሴቶች ውሀውን ሲጠጡ ይመክናሉ ፈውስልን አሉት ኤልሳም አዲስ ማሰሮ አምጡ ጨውም ጨምሩበት አላቸው ያን ጨው በውሀው ምንጭ ላይ ቢያደርገው መራራው የኢያርኮ ተፈወሰ
ወደ ቃና ዘገሊላ እንምጣ ኤልሳዕ የጌታ ምሳሌ ነው ኤልሳዕ አዲስ ማሰሮ አምጡ እንዳለ ጌታም 6 ጋኖችን አምጡ አለ ኤልሳዕ ማሰሮውን ጨው ሙሉበት እንዳለ ጌታም ማሰሮውን ውሀ ሙሉበት አለ ወይን የተሞላበት የቃና ዘገሊላ ማሰሮ ጨው የተገኘባት የኤልሳዕ ማሰሮ ማናት

*መልስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት*

✅ጥ.ተራ(ቁ)1⃣0⃣➡
👉ለኢዮብ ጽናትን
👉ለሰሎሞን ጥበብን
👉ለኤርምያስ ትንቢትን ካልን!
👉ለአብርሃም *__//መልስ* *👉_ደግነት እንላለን።*


✅ጥ.ተራ(ቁ) 1⃣1⃣➡አባታችን ፃዲቁ  ቅዱስ ላሊበላ ካነጻቸው ከሁሉም ቤተመቅደሶች በስፋት  አንደኛ የሆነው ማን ነው??

*//መልስ//* *👉ቤተ መድኃኔአለም ነው።*

✅ጥ.ተራ(ቁ)1⃣2⃣➡የመንግስተ ሰማያት መክፈቻዎች እሰጥሀለሁ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል። ብሎ ጌታ  ቃል  የገባለት ለማን ነው?/ማን /ይባላል??

*//መልስ//* *👉ለቅዱስ ጴሮስ ነው።*

✅ጥ.ተራ.( ቁ)1⃣3⃣➡የፃድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥  እግዚአብሔር  ያድናቸዋል። ይህ ቅዱስ ቃል  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይገኛል??_

_ሀ/ (መዝ 33፥ 19)_

_ለ_/ (መዝ 32፥19)_
_ሐ/ ( መዝ 20፥13)_
_መ/ መልስ የለም_


*//መልስ//* *👉ሀ)፨መዝ.33፥19 ላይ ይገኛል።*


✅ጥ.ተራ(ቁ)1⃣4⃣➡፠  እንደ ሚካኤል ማለት ምን ማለት ነው?? እያንዳንዱ ፊደል
፠   ሚ  . ...
፠  ካ......
፠  ኤል ...? የሚልቱስ.???

*//መልስ//*👇👇
፠   ሚካኤል ማለት *መኑ አምላክ
፠   እግዚአብሔር ያለ ማነው ?*
፠   ማለት ነው  ሚካኤል የሚለው ስም
፠   ቃሉ የዕብራይጥስ ነው ።
፠   ሚ  . መኑ
፠  ካ. የሚለው  ከመ  ማለት ሲሆን
፠  ኤል ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው።


✅ጥ.ተራ(ቁ)1⃣5⃣➡ሕዳር 12 ቀን የሚከበረው ዓመታዊ የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ምንን በተመለከተ ነው???


*//መልስ//* *👉ህዳር 12 የተሾመበት ዲያብሎስን ድል የነሳበት ህዝበ እስራኤል የመራበት እለት ነው።*
2ኛ👉ህዳር 13 በዓለመ መላእክት ያሉ አእላፍ መላእክት በዓለ ሲመቱን ተሰብስበው ያከበሩበት ቀን ነው።

✅ጥ.ተራ(ቁ)1⃣6⃣➡ከሚከተሉት ውስጥ የማይገባ የክርስትና ስም/ለሰው ሊሰየም የማይገባ ስም የትኛው ነው??

ሀ) አማኑኤል

ለ)ዘአማኑኤል

ሐ/ ሣህለ ሥላሴ

መ/ ዘሚካኤል

ሠ/ ሁሉም

*//መልስ//* *👉ሀ)፨ አማኑኤል*

☞ የማይገባ የክርስትና ስም
በአምላክ ስም በቀጥታ መጠራት አይገባም ለምሳሌ፡- አማኑኤል፣ኤልሻዳይ፣ኢየሱስ እነዚህ ስሞች ለሠው ልጆች መጠናችን ስላልሆኑ መጠቀም የለብንም፡፡ በዚህ ምትክ ገብረ አምላክ፣ሣህለ ሥላሴ፣ፍቅርተ ክርስቶስ ፣ዘአማኑኤል በማለት መሰየም ይቻላል፡፡
☞በቅዱሳንም ስም በቀጥታም ሆነ ዘርፍ እየተደረለት መሰየም ይቻላል፡፡
 ለምሳሌ፡- ዘማርያም፣ዘሚካኤል፣አጸደ ማርያም፣ ተክለ ሐይማኖት ወዘተ...

✅ጥ.ተራ(ቁ)1⃣7⃣➡የቅዱስ ትውፊት ዋና ማዕከሉ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶ ነው።
 ትውፊት የምእመናን የዘወትር ሕይወት ነው። ለመሆኑ ትውፊት ማለት ምን ማለት ነው??

*//መልስ//*👉 ትወፊት ማለት በሰዋስዋዊ ዘይቤው ሲፈታ  ስጦታ፣ ልማድ፣ ትምህርት፣ ወግ፣ ታሪክ፣ ሃይማኖት፣ ሥርዓት፣ከጥንት ከአበው ሲያያዝ ሲወርድ፣ ቃለ በቃል ሲነገር የመጣ ማለት ነው።

✅ጥ.ተራ(ቁ)1⃣8⃣➡ ታቦትን በቅዱሳኑ ስም እንዲሰየም ያዘዘው ማነው??

*//መልስ//* *👉ክብር ይግባውና እራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ነው።* *(ዘጸ. 31፥1-11)(ዘጸ 37፥1)*

✅ጥ.ተራ( ቁ)1⃣9⃣➡ዘመነ ብረሃን የሚባለው ከልደተ ዳዊት እስከ ፍልሰት ባቢሎስን"14"ቱ ትውልድ ነው። ብርሀን የተባለው ጌታችን ኢየሲስ ክርስቶስ ነው ። *ትክክል ወይም ትክክል አይደለም በማለት መልስ/ሽ/*
*//መልስ//* *👉ትክክክል ነው።*

✅ጥ.ተራ(ቁ)2⃣0⃣➡ዘመነ 'ሀጋይ'  ማለት 'ከታህሳስ 26-መጋቢት 25"  ያለው ሲሆን የቃሉ ትርጎሚ ሀጋይ ፡ደርቅ,ጸሀይ፡ሀገር፡በጋ፡፡ሲሆን ከ4ቱ ክፍለ ዘመነ አንዱ ነው።
 *ትክክል ነው ወይም አይደለም በማለት መልስ/ሽ/*
*//መልስ//* *👉ትክክል ነው።*


_ወስብኃት ለእግዚአብሔር_saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...