2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የ9ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

https://youtu.be/pm3m3DPMzBQ

👆👆👂

*_✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ? እንደምንስ አላችሁ??_

_እነሆ የ9ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀትየቃ መንፈሳዊ  የጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ መልስ👇👁_

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣👉ከዘመነ መሳፍንት ቀጥሎ ያለው ዘመን ዘመነ ምን ይባል ነበር??

*/መልስ/*

✍መልስ፡- ከዘመነ መሳፍንት ቀጥሎ ያለው ዘመነ ነገሥት ይባላል፡፡ ልዩነታቸው በዘመነ መሳፍንት የሚፈርድ ንጉሥ የለም፡ በዘመነ ነገሥት ከሕዝቡ መካከል የተመረጠ ንጉሥ አለ፡፡

✔ጥ ተራ(ቁ) 2⃣👉መጽሐፈ ሩትን የፃፈው ? ማነው? መጽሐፉስ ስንት ምዕራፎች  አሉት? ሩትስ ማን ነች?

*/መልስ//*

✍መልስ፡- መጽሐፈ ሩትን የጻፈው ነቢዩ ሳሙኤል ነው፡፡ ሩት በዘመነ መሳፍንት የነበረች ሞዓባዊት ሴት ነበረች፡፡ መጽሐፉም 4 ምዕራፎች አሉት፡፡

✔ጥ ተራ( ቁ)3⃣ 👉"በክርስቶስ ኢየሱስ የእዝአብሔር  ልጆች ናችሁ፣ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋል፤ ይህንን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን?? ምዕራፍና ቁጥሩን??

*//መልስ//*

/ገላ. 3፥26_27/

✔ጥ ተራ(ቁ) 4⃣👉
"ጥበብ ቤቷን ሰራች ሰባቱንም ምሶሶዎችንም አቆመች፣ ፍሪዳዎችንም አረደች፣ የወይን  ጠጇንም ደባለቀች፣ ማዕድዋንም አዘጋጀች። ባርያዎቿንም ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ሥፍራ ላይ ጠራች /ምሳ 9፥1/ የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ሲተነተን✍👉ጥበብ የተባለው ማነው?
👉ቤት የተባለውስ?   👉ምሶሶዎች የተባለው
 ምሥጢራትስ ምንድነው?

👇👇👇👇
ጥበብ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቤት የተባለችው ቤተ.ክርስቲያን ናት። ምሶሶዎች የተባሉትም ምሥጢረ ቤተ.ክርስቲያን ናቸው ለምሳሌ👉 ምሥጢረ ጥምቀት👉ምሥጢረ ሜሮን 👉ምሥጢረ ንስሀ👉ምሥጢረ ቁርባን 👉ምሥጢረ👉ወዘተ እያልን የምጠራቸው ናቸው።

✔ጥ ተራ(ቁ) 5⃣👉 በፍልስጤማውያንና በእስራኤላውያን መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው??

👇👇👇

✍መልስ፡- እስራኤላውያን በግርዛት ለእግዚአብሔር የተለዩ ሲሆኑ ፍልስጤማውያን ያልተገረዙና በጣዖት የሚያመልኩ ናቸው፡፡

✔ጥ ተራ(ቁ)6⃣👉ሶምሶም ፍልስጤማውያንን እንቆቅልሽ ጠይቋቸው ነበር ለመሆኑ የጠየቃቸው እንቆቅልሽ ምን የሚል ነበር?

👇👇👇👇

✍መልስ፡- ከበላተኛ ውስጥ መብል ወጣ ፣ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ አላቸው፡፡ መሳ.14÷14

✔ጥ ተራ( ቁ) 7⃣👉 ፅዮን የሚለው ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለ4 ነገሮች ተነግሯል ለምን ለምን??

👇👇👇👇👇

↪❤1ኛ ከተማ ጽዮን

✔💟ጥቂቶቹን ጥቅስ ለመግለጽ 《ሚኪ 3 ፡ 12》፣ 《2ኛ ሳሙ 5 ፡ 7》 ፣ 《2ኛ ዜና 5 ፡ 2》 ፣《 ኢሳ 64 ፡ 10》

↪❤2ኛ ሰባተኛይቱ ሰማይ ጽዮን

✔💟ጥቂቱን ለመግለጽ 《መዝ 46/50 ፡ 2》 ፣ 《ራዕ 14 ፡ 1》

↪❤3ኛ ቤተ እስራኤል ጽዮን

✔💟አንዱን ለመግለጽ 《መዝ 149/150 ፡ 1》

↪❤4ኛ ድንግል ማርያም ጽዮን
ጽዮን
✔💟ሰው ሁሉ እናታችን  ይላል በውስጥዋም ሰው ተወልዷልና 《መዝ 86/87 ፡ 5》

✔ጥ ተራ (ቁ) 8⃣👉በሰኔ 20 እና 21 ቀን የሚከበርበት  የእመቤታችን ቅድስት  ማርያምን አመታዊ በዓልን ምክንያት አስረዳ/አስረጅ???

ድንግል👇👇👇👇👇👇

..በዓሉ እንዴት ነው ቢሉ፦       እመቤታችን ባረገች በ4 ዓመት ጳውሎስና በርናባስ ፊልጵስዩስ ገብተው አስተማሩ፤ ሕዝቡም አምነው ተጠመቁ እንግዲህ ወዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ አሏቸው የለመድነውን ከከለከላችሁንማ መካነ ጸሎት ስጡን አሏቸው፡፡  እንዲህ ብንላቸው እንዲህ አሉን ብለው ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስ ላኩ አልቦ ዘትገብሩ ወኢምንተኒ ዘእንበለ ትዕዛዙ ወምክሩ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባም እናንተም ጸልዩ እኛም እንጸልያለን ብለው ላኩባቸው፡፡ ሱባዔ ሲጨርሱ በዚህ ዕለት ጌታ በሩቅም በቅርብም ያሉ ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ዮሐንስ ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን ብሎ ጠየቀ ጌታም በእናቴ ስም ጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው አለው፡፡
   ይህንን ብሎ ወደ ምስራቅ ወሰዳቸው ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፣ በተአምራት አቀራርቦ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ሠጣቸው እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ /እየተሳቡ/ ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ከእንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ ብሏቸው ዐረገ፡፡
   በማግሥቱ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡

✔ጥ ተራ(ቁ) 9⃣👉አምስቱ(፭) ሐራ ሲኦል ነገስታት የሚባሉት ማን ማን ናቸው??

👇👇👇

ፈርኦን በኤርትራ የሰመጠው፣ ሰናክሬም፣ አንጥያኮስ፣ ሔሮድስ፣ ዲዮቅልጥያኖስ ናቸው።

✔ጥ ተራ(ቁ)1⃣0⃣👉አምስቱ(፭) አርዕስተ አበው የሚባሉት ማን ማን ናቸው?  ስማቸውን ጥቀስ/ሽ ?

👇👇👇
አዳም፣ ሄኖክ፣ ኖህ፣ አብርሃም፣ ሙሴ ናቸው።

✔ጥ ተራ (ቁ)1⃣1⃣አምስቱ(፭)ሐብታት የሚባሉት ምን ምን ናቸው???

ሐብተ ፈውስ፣ ሐብተ ክህነት፣ ሐብተ ትንቢት፣ ሐብተ መዊእ፣ ሐብተ መንግስት ናቸው።

✔ጥ ተራ (ቁ)1⃣2⃣✔ አምስቱ (፭)  ህሩያነ ነገስታት የሚባሉት ምን ምን ናቸው???

*/መልስ//*

ሕዝቅያስ፣ ኢዮስያስ፣ ዳዊት፣ ሰለሞን፣ ንግስተ ሳባ/አዜብ/ማክዳ። ናቸው

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣3⃣👉ቃለ ሕይወት ያሰማልን ምን ማለታችን ነው? /ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ማለት ምን ማለት ነው??

*/መልስ/*

//መልስ///👉 ቃለ ህይወት ያልሰማልን ማለት👉 የእግዚአብሔርን ቃል ጠብቀው እንደቃሉ ለኖሩ
 ልብን የምመረምር እኔ ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሥራችሁ ለመክፈል (ራዕ.22፥32) እስክመጣ ድረስ በፍቅር ኑሩ ያለውን ለፈጸሙ ....በአጠቃላይ በጌታ ለኖሩ ፍሬዎች...የሰው ልጅ በክብር በሚመጣበት ጊዜ (ማቴ.25፥31) በጎቹን ከፍየሎች በሚለይበት ጊዜ (ማቴ.25፥34) <<ኑ እናንተ የአባቴ ቡሩካን ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ::>> ብሎ ጌታ የሚፈርደው ፍርድ የሕይዎት ቃል ይባላል::
ሥለዚህ ቃለ ሕይዎት ያሰማልን ማለት ይህን የተወደደ፣ ዘለዓለማዊ  የሚሰጥ ቃል ያሰማልን፤ ከቀኙ ከሚቆሙት ቅዱሳን ይደምርልን እንደማለት ነው።

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣4⃣👉የእግዚአብሔር ጠባይ/ጸባይ ስንል ምን ማለታችን ነው??

*/መልስ/*

// መልስ ///፦የእግዚአብሔር ጠባይ ስንል በማናቸውም  ለእግዚአብሔር  እንጂ ለፍጡር የማይነገር የእርሱ የብቻው የባሕርይው መገለጫ ወይም
በእግዚአብሔር ባህርይ ውስጥ የሚገለጡትን ሁኔታዎች የሚያመለክት ነው።

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣5⃣👉በዓል ማለት ምን ማለት ነው?? የመጀመርያዋ በዓልስ ማናት??

*/መልስ/*

//መልስ ///፦ በአል ማለት፦ አብዐለ፤ አከበረ ፤ አበለጠገ፣ ዕለትን በዓል አደረገ፤ ከሚለው ግስ የወጣ ስም ነው። በቁሙ ሲፈታም የደስታ፤ የዕረፍት ቀን ፣ የዓመት፣ የወር፣ በሳምንት የሚከበር፣ ያለፈ ነገር የሚታሰብበት ተዝካር ማለት ነው።
የመጀመርያዋ በልዓ ቀዳሚት ሰንበት ናት። እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔርሰንበትን ሊያደርገው ከፈጠረው ቀደሰውም በእርሱ ዐርፎአልና> እደተባለ እግዚአብሔር  ለይቶአክብሯታል ቀድሷታልም። ዘፍ. 2፥3 ስለዚህ ይህ የበአል መጀመሪያ ሆነ።

✔ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣👉ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ትርጉም አለው። ምን ምን ??

*//መልስ//*

1ኛ👉የክርስቲያን መሰብሰቢያ/የጸሎት ቤት

2ኛ👉 እራሱ ሕንፃው ቤተ ክርስቲያን ይባላል

3ኛ👉ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን ይባላል

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣7⃣👉ክብር ይግባውና ጌታችና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ቅዱሳንን ምልጃ ተቀብሏል። ምልጃቸውን ከተቀበለላቸው ቅዱሳን  ቢያንስ ሦስቱን ጥቀስ/ጥቀሽ???

*/መልስ/*

👉የአብርሃምን (ዘፍ 18፥23)
👉የሙሴ የአብርሃም፣የይሳቅ፣እና የያዕቆብን ስም እየጠራ የማለደውን /ዘጸ. 32፥11-13)፣ ሙሴ ለእህቱ ለማርያም ሲል ያቀረበው (ዘኁ. 12፥10)፣ ሳሙኤል ስለ ሕዝቡ ያቀረበውን/ 1ኛ ሳሙ. 7፥5/ ኢዮብ/ ኢዮብ 42፥7/፣ ዳዊት ስለ ሕዝቡ/2ኛ ሳሙ. 24፥17/  ብዙ መቅጥቀስ ይቻላል

ውስጥ✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣8⃣👉
ጉባኤ ቃና ማለት ምን ማለት ነው?? ጉባኤ ቃና በሁለት ክፍል ይከፈላል። ምን ምን ???

*/መልስ/*

 ቃና ማለት የፈጣሪ ጉባኤ ተቃና፣ የቅኔ ትምህርት ተጀመረ፣ ተለካ ጉባኤው ተቃና ማለት ነው። ጉባኤ ጉባኤቃና በሁለት ክፍል ይከፈላል። ይኸውም ግእዝ  ቃና፣ ዕዝል ጉባኤ ቃና ወይም አጭር ጉባኤ ቃና፣ ረጅም ጉባኤ ቃና በመባል ይጠራል።
.

✔ጥ ተራ(ቁ)1⃣9⃣👉የማሕሌት ሰባቱ/፯/ ደረጃዎች የሚባሉት ምን ምን ናቸው???

*/መልስ/*

1ኛ 👉ቁም ዜማ

2ኛ👉ዝማሜ

3ኛ👉ቁም ጸናጽል

4ኛ👉መረግድ

5ኛ👉ጽፋት

6ኛ👉አመላለስ

7ኛ👉ወረብ ናቸው።

✔ጥ ተራ(ቁ) 2⃣0⃣👉
ማሕሌት እንዴት ተጀመረ? ማን ጀመረው? የት ተጀመረ??

*/መልስ/*

ማሕሌት በመላእክት ዘንድ እንደተጀመረ ጀማሪዎችም እነርሱ በሆናቸውን የቃሉ ትርጓሜ ምስጋና ማለት መሆኑን ቅዱሳት በጻሕፍት ይነግሩናል።

*ማጠቃለያ መልስ ይህ ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ*

*ወስብኃት ለእግዚአብሔር*

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=689617831227746&substory_index=0&id=391288387727360

👁ፔጅ⤴

https://www.facebook.com/sara.mareyame.54
✍00971 50 17 21 032saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...