2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የ8ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

saramareyama.890@gmail.comhttps://youtu.be/r_wP_d9IlM0

*በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_8ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር_

*_ማጠቃለያ መልስ_*👀

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣ 👉ቅዱስ ዮሐንስ መልእክ የፃፈላቸው ሰባቱ (7)  አብያተክርስቲያናት ማን ማን ናቸው??

*✍/መልስ/*👇

1. ⛪የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
2.⛪ የሰርሞኔስ ቤተ ክርስቲያን
3. ⛪የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
4. ⛪የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን
5. ⛪የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
6. ⛪የፍልድልፊያ ቤተ ክርስቲያን
7. ⛪የሎዶቂያ ቤተ ክርስቲያን
"

✍ጥ ተራ (ቁ) 2⃣👉አምስቱ (5) እቀባተ መስቀል የተባሉት እነማን ናቸው በዝርዝር አስረዳ/ጅ??

*✍/መልስ/*👇

👉1ኛ ጣዖት ማምለክ

👉2ኛ አፍቅሮ ነዋይ

👉3ኛ ተጣልቶ አለመታረቅ

👉4ኛ ሰው መግደል

5ኛ👉እናትን እና አባትን አለማክብር ናቸው።

♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ)3⃣👉መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ ተብሎ በእራይ የተነገረው አባት ማን ይባላል??

*✍/መልስ/*👇

👉አፄ ዘርያእቆብ ነው።

♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ) 4⃣👉በሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመርያው ሊቀ ጳጳስ ማን ይባላል??

*✍/መልስ/*👇

👉አባ ሰላማ ከታሳቴ ብርሀን ይባላሉ።

♥♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ) 5⃣👉በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ካሉ የተባረኩ ጋብቻዎች ውስጥ ሁለቱን ጥቀስ(ሽ)

*✍/መልስ/*👇

✍የኢያቆምና የሐና፣ የዘካሪያስና የኤልሳበጥ ጋብቻ

♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ)6⃣👉 በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ዲያቆን እድሜው ስንት ሲሆን ቅስና ይሾማ??

*✍/መልስ/*👇

በሰላሳ አመቱ (30) ይሾማል።

✍ጥ ተራ (ቁ)7⃣👉በኦሪቱ ታቦት የሚባለው ምንድነው ጽላት የሚባለውስ??

*✍/መልስ*/👇
በኦሪቱ ታቦት የሚባለው ጽላት የሚቀመጥበት ማደሪያው ነው። ዘጸ 40፥20-21፣25፥20-22፣መዝ131፥8፣ 2ቆሮ6፥16፣ ዕብ9፥4፣ ራዕ 11፥9 ጽላት  የሚባለው ደግሞ እግዚአብሔር ለሙሴ  አስርቱ ቃላተ ኦሪትን በእጁ የሰጠው ቃሉ ተጽፎ የሚገኝበት ከእብነበረድ የተቀረጸው ነው። ዘጸ31፥18፣24፥12-25፣10፥22አስቀድሞ፣34፥1-29

✍ጥ ተራ (ቁ) 8⃣👉መስዋዕተ ቁርባን ማቅረብ የተጀመረው በማን ነው??

*✍/መልስ/*👇

👉በአባታችን አዳም ነው።

✍,ጥ ተራ (ቁ)9⃣👉 በቅዳሴ ሰዓት ወንጌል ስንሳለም ምን ማለት አለብን??

*✍/መልስ/*👇

👉ነአምን በወንጌክ በቅዱስ እንላለን።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣0⃣👉 ቅጽር ግቢና የውጭ አደባባይ ገበያ ዘርግቶ ንግድ መነገድ ክልክል እንደሆነ  ከሚያስዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በቤተክርስቲያንውስጥ 3ቱን ጥቀሱ???

*✍/መልስ/*👇

👉ኤር 7፥11፣ ማቴ 21፥12-14፣ ማር11፥15-17፣ ሉቃ19፥45-46፣ ዮሐ2፥13-18... እናገኛለን

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣👉ሰባቱ(7) አባቶች የሚባሉት/  ማን ማን ናቸው???

*✍/መልስ/*👇

"ሰባቱ አባቶች"
1ኛ👉ልዑል እግዚአብሔር
2ኛ👉 የንስሐ አባት
3ኛ👉ወላጅ አባት
4ኛ👉 የክርስትና አባት
5ኛ👉የስልጣንየጡት አባት
6ኛ 👉 (የቆብ) አባት
7.ኛ👉የቀለም አባት

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣2⃣👉የክህነት አላማና ጥቅም ምንድነው??

*✍/መልስ/*👇

👉 ሰዎችን ከኃጢአት ከሰይጣን ስራ ሁሉ በመለየት በማስተማር በመቆጣጠር በመጠበቅ በመቀደስና በማንጻት በማናዘዝና በመፍታት
ለጨለማው ብርሃን ለመሆን ፣አልጫ የሆነውን ዓለም ለማጣፈጥ፣ ምስጢራተእንዲሆኑ ቤተክርስትያንን በመፈጸም  ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ማሰጠት የእግዚአብሔር ልጆች የመንግስቱ ወራሾች  ለማብቃትና ድኅነተ ነፍስ ለማሰጠት ፣  እግዚአብሔርን ለምእመናንበቅዳሴና በውዳሴ ለማመስገንና መንፈሳዊ አገልግሎት ለመፈጸም ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣3⃣👉⃣አምስቱ (5) ፍኖተ ኃጢአት የተባሉት እነማን /ምን ምን ናቸው??

*✍//መልስ//*👇

1ኛ👉 ትቢት

2ኛ👉ስስት

3ኛ👉ምቀኝነት

4ኛ👉ስርቆት

5ኛ👉ዝሙት ናቸው።

✍ጥ ተራ (ቁ)1⃣4⃣👉⃣ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው። ብሎ የተናገረው አባት ማን ይባላል??

*✍መልስ//*👇

👉ብፁ አቡነ ጎርጎርዮስ ካአል ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣👉ለመጀመርያ ጊዜ ካህን  ሁኖ  የተሾመው ቅዱስ አባት ማን ይባላል???

*✍/መልስ*/👇

👉ካህኑ መልከ ጸዲቅ ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣👉ለመጀመርያ ጊዜ የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው? ወይም የማን መጽሐፍ ነው??

*✍/መልስ//*👇

👉መጽሐፈ ሄኖክ ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣7⃣ሀሌ ሉያ ማለት ምን ማለት ነው???

*✍//መልስ//*👇

👉ሃሌ ሉያ ማለት እግዚአብሔር  ይመስገን ማለት ነው።

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ (መዝሙር 150፥6)

✍ጥ ተራ (ቁ)1⃣8⃣👉 በቅዳሴ ጊዜ 5ት/አምስት መስዋቶች አሉ። ምን ምን ናቸው??

*✍/መልስ//*👇

1ኛ👉 የቁርባን መሰዋት

2ኛ👉 የከንፈር መሰዋት

3ኛ👉 የመብራት መሰዋት

4ኛ👉 የእጣን መሰዋት

5ኛ👉 የሰውነት መሰዋት ናቸው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣9⃣👉 ኤልሻዳይ ማለት
👉ያህዌ ማለት
ምን ማለት ነው የሱሞችን ትርጉም አስረዳ/ጂ??

*✍//መልስ//*👇

ቅ✍🏻_*ኤልሻዳይ*ማለት ምን ማለት ነው??

//መልስ//✔ _ኤልሻዳይ ማለት ሁሉን ቻይ ማለት ነው_
አብርሀምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤
((ዘፈጥረት 17፤1))

✍🏻ያህዌ* ማለት ምን ማለት ነው??.

//መልስ//✍🏻ያህዌ ማለት የነበረ ያለና የሚኖር ማለት ነው።" አብርሃምም ያንን ቦታ ያህዌ ይርኤ ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእግዚአብሔር ተራራ ይታያል ይባላል።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 22:14)

♥♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ) 2⃣0⃣እምነ ጽዮን ማለት ምን ማለት ነው????

*✍/መልስ//*👇

✍🏻_*እምነ* ጽዮን ማለት ነውምንም ማለት ነው_??

//መልስ//እምነ ጽዮን ማለት እናታታችን ጽዮን ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያይቱ የሰው ልጆች ሁሉ እናት ሔዋን አማካኝነት ከርስታ ን ወጥተን መጠጊያ አጥተን ነበግ በዳግማዊ ሔዋን በድንግል ማርያም ደግሞ ወደ ርስታችን ተመልሰናል። እናታችን ጽዮን እንላለን።

♥♥♥♥♥♥♥

*ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነን።*

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...