2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የ10ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ


https://youtu.be/bxtabq_vFB4  👆👆   *_በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

*_ፍፁም የእግዚአብሔር ሰላም የእናታችን የድንግል ማርያም ምልጃና ጥበቃ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን_*

*እነሆ የአስረኛ (10)ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል  ጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ መልስ 👇👀*
////////👇👇/////

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣ሰኔ 30 የሚከበረው  የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ክብረ በዓል ምንንን አስመልክቶ ነው??

*//መልስ//*

👉ሰኔ 30 ልደቱ ለዮሐንስ መጥምቀ መለኮት

በዚህች ቀን የጌታን መንገድ ጠራጊው፤ ሐዋርያው፤ ነብዩ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ቀኑ ነው፤ መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ነው ሚያዚያ 15 እረፍቱ ነው፤ አንገቱ ከተቆረጠ በኋላ የተቆረጠች አንገቱ ክንፍ አውጥታ ለ15 ዓመት በሳውዲ አረቢያና አካባቢው ወንጌልን ሰብካለች፤ የካቲት 30 ቀን የዮሐንስ ራስ የተገለጸችበት ቀን ነው። ከነዚህ አራት በዓላት ሁለቱን ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉን አውጥታ በደማቁ ታከብረዋለች እነዚህም ሰኔ 30 ልደቱና መስከረም ሁለት አንገቱ የተቆረጠበትን ቀን ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 👉2⃣ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶ የመሰረተልን ማንነው??

*// መልስ//*👉እራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 👉3⃣ትውፊት ማለት፦ ምን ማለት ነው?

*//መልስ//*👉ትውፊት የሚለው  ቃሉ የግሪኩ ፓራዶሊስ የሚለው ሲሆን ትርጉሙም መቀበል፣መረከብ ማለት ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 👉4⃣የመጀመርያዎቹ  የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተፃፉት...በ... ነብይ ዘመን ነው??

*//መልስ//*👉በነብዩ ሙሴ ዘመን ነው።

✍ ጥ ተራ(ቁ)👉5⃣አራቱ(4) የቤተ ክርስቲያን አካላት ተብለው የሚጠሩት ማን ማን ናቸው???

*//መልስ//*👉ጳጳሳት፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት እና ምእመናን ናቸው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉6⃣ቅዱስ ጳውሎስ ለደቀ መዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው ስንት ነበር??

*//መልስ//*👉 በ55 አመቱ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉7⃣ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተማረባቸውን ቦታዎች ስም ጥቀስ/ጥቀሽ??

*//መልስ//* በከፊል ለመጥቀስ ያህል👉ሶርያ ፣ ገላትያ ፣ ፍልስጤም ፣ ቢታንያ ፣ ኢዮብ ፣ ቂሳርያ ፣ ሊድያ ፣ ሮሜ ፣ እየሩሳሌም ልዳ ፣   ቂሳርያ ፣ ጳንጦስ ፣  ኢስያ ወ.ዘተ ናቸው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉8⃣ በስርአተ ቅዳሴ ጊዜ/ ወንጌል ሲነበብ ሻማ/ጧፍ ለምን ይበራል???

*//መልስ//*👉1ኛ👉ክብር ይግባውና ጌታችና መድኃኒታችን እኔ የአለም ብርሃን ነኝ ስላለን ነው።

2ኛ✔ሐዋርያትና ሰማዕታት ለወንጌል የከፈቱን ዋጋ/መሰዋትነት የምናስበበት ነው። ይህ ማለት ሻማው እየበራ ይቀልጣል ቅዱሳን ሰማዕታትም ለአለም ብርሃን ብለው ደማቸውን ማፍሰሳቸውን ይዘክራል።

✍ጥ ተራ (ቁ)👉9⃣ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለቤተ ክርስቲያን ከፃፏቸው መጽሐፍት ውስጥ ቢያንስ /አምስቱን 5/ቱን ጥቀስ/ጥቀሽ??

*//መልስ//*
በእግዚአብሔር በሰጣቸው በመንፈሳዊ ጸጋ ብዙ መጽሐፍትን እንደ ፃፉ ይነገራል ከነዚያ መካከል፦
👉መጽሐፈ ውዳሴ መስቀል፣ አርጋኖ፣ መሐፈ ሰዓታት፣ መጽሐፈ እንዝራ፣የሰባቱ ጊዜያት የጸሎት መጽሐፍትመዐዛ ቅዳሴው   ወ.ዘተ የመሳሰሉትን  ጽፈዋል።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉🔟እያሱ ማለት ምን ማለት ነው???

*//መልስ//*👉እያሱ ማለት፦ መድኃኒት ማለት ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣1⃣ አሪዎስ ወልድ ፍጡር ነው ብሎ የተናገረበት ምክንያት ምንድነው???

*//መልስ//*👉መ.ምሳሌ ም. 8፥22 እግዚአብሔር ለሥራው የመንገዱ የመጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፥ የሚለውን ሃይቃል በመጠቀም ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 👉1⃣2⃣ ጻዲቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የትውልድ ሀገራቸው የት ነው?? እናትና አባታቸውስ ማን እና ማን ይባላሉ??

*//መልስ//*👉በመንዝ አውርጃ ነው የተወለዱት👉አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባሉ ነበር። ፍሬ ብሩክና ዮስቴና በህገ እግዚአብሔር በሃማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣3⃣ የመጀመርያው  የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር የነበረው የሐዲስ ኪዳንን መጽሐፍትን ቆጥሮ ያስረከበው ቅዱስ ማን ይባላል???

*//መልስ//*👉ቅዱስ ቀለሚንጦስ (ፊሊጲንስ 4፥1-3 ላይ ይገኛል።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣4⃣ ታምረ ማርያምን የፃፈው ቅዱስ አባት ማን ይባላል??

*//መልስ//*👉ደቅስዮስ ይባላል።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣  አትሮኖስ ማለት ምን ማለት ነው?? ጥቅሙስ ምንድን ነው?? ምሳሌነቱስ ምንድን ነው??

*//መልስ//*👉ልዑካን በቅዳሴ ሰዓት ቅዱሳት መጻሕፍትን ሊያነቡ ያጠቀሙበታል፡፡ መዘምራንም በቅኔ ማሕሌት በአገልግሎት ጊዜ የሚያስፈልጉ መጻሕፍትን በማስቀመጥ የሚዜመውን ያዜማሉ የሚነበበውን ያነቡበታል በብሉያ ኪዳን በደብተራ ኦሪትና በታላቁ ቤተ መቅደስ መጻሕፍት ማንበቢያነት ያገለግል ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳንም በቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በላዩ ይዘረጉና ያነቡበታል፡፡
ምሳሌነቱም ፡-
አትሮኖስ የጌታ ዙፋን
መጽሐፉ የጌታ አንድም
አትሮኖስ የእመቤታችን
መጽሐፉ የጌታ ምሳሌ ነው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማህፀን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተቀምጧልና፡፡

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣6⃣ልጇ ሐዋርያ ቤቷ ቤተ ክርስቲያን የነበርላት ከቅዱሳት አንስት መካከል የሆነች እናት ማን ትባላለች???

*//መልስ//*👉የቅዱስ ማርቆስ እናት ማርያም ነት።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣7⃣⃣ክርስትና በምንነሳበት ጊዜ ሦስት ዓይነት ከረር ያላቸው ክሮች ከአንገታችን ላይ እናስራለን የነዚህን ክሮችን ከረር ጥቀስ/ጥቀሽ ምሳሌነትቱንም ጭምር??

*//መልስ//*👉(1ኛ)ጥቁር ክር፦በክርስትና የምንቀበለው የመከራ ህይወት ምሳሌ ነው (2ኛ)ነጭ ወይም ቢጫ፦በጥምቀት ያገኘነውን የኃጢአት ስርየት የመመስከራችን ምሳሌ ነው (3ኛ)ቀይ ክር፦በክርስቶስ ደም የመገዛታችን ወይም የመዳናችን ምሳሌ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣8⃣  ነገረ ማርያምን የፃፈው ቅዱስ ማን ይባላል??

*//መልስ//*👉ቅዱስ ዮሐንስ አፈወቅ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣9⃣  ሚስጢረ ትንሳኤ ሙታን ማለት ምን ማለት ነው?? ትንሳኤ ሙታንስ በስንት ይከፈላል??

ሚስጢረ ትንሳኤ ሙታን ማለት በዓለም መጨረሻ የፈጣሪያችውን የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምተን ነፍስና ሥጋችን ተዋህዶ ከመቃብር የምንነሳበትና የዘላለም ሕይወትን የምናገኝ መሆናችንን የምንማርበትና የምናምንበት ምስጢር ነው። ትንሳኤ ሙታን በሁለት(2) የከፈላል እነርሱም፦ ትንሳኤ ዘለክብርና ትንሳኤ ዘለሀሳር በመባል ይታወቃል

✍ጥ ተራ(ቁ)👉2⃣0⃣ ማህበረ ጽዋ ማለት ምን ማለት ነው??

*//መልስ//*👉የተጀመረው በሐዋርያ ዘመን  ሲሆን ምእመናንና ነድያን በአንድነት ተሰብስበው በፍቅር በአንድነት ማአድ የሚካፈሉበት ነው ይከውም በጌታችን ስምና በቅዱሳን ስም መታሰቢያ የሚደረግበት የፍቅር ማአድ ማለት ነው።

*✍ማጠቃለያ መልስ*




saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...