2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የ7ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

https://youtu.be/l1IoBZtsdro👂👆

*✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_✍7ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ  ጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ  መልስ።_

✍/ ጥ ተራ (ቁ)1⃣👉 እሕቴ ሙሽራ የተቆለፈ ገነት የተዘጋ ምንጭ የታተመም የውኃ ፈሳሽ ናት"  መኃ 4፥ 10 የሚለው ጥቅስ ምንን ያመለክታል??

ሀ/ የእመቤታችን ፍፁም ድንግልናል

ለ/ እመቤታችን ጌታን መውለዷን

ሐ/ ለእመቤታችን የተሰጠ ቃል ኪዳን.

መ/ የእመቤታችን ስደት

*//መልስ*

👉ሀ/ የእቤባታችን ፍፁም ድንግልናን።

✍ ጥ ተራ (ጥ) 2⃣👉 ከሰው ወገን ለመጀመሪያ  ጊዜ ለእመቤታችን ምስጋና ያቀረበው ____ነው??

ሀ/ ቅዱስ ኢያቄም

ለ/ ቅድስት ሐና

ሐ/ ቅዱስ ዮሴፍ

መ/ ቅድስት ኤልሳቤጥ

*//መልስ//*👇
.
👉መ/ ቅድስት ኤልቤባጥ

✍ጥ ተራ (ቁ) 3⃣👉 ቅዱስ አግናጥዮስ በኤፌሶን ፣ በፊላደልፊያ ፣ በማግኒስያ፣ በቴራሊስ፣ በሮምና  በመሳሰሉት ሀገራት ውስጥ ላሉ ክርስቲያኖች ሰባት መልእክታትን በሰባት ዓይነት አርዕስት ጽፎላቸዋል። እነዚህ ሰባት መልእክታት ምን ምን  ናቸው??

*//መልስ//*

👉 መናፍቃንን በፍፁም መቀዋወም እንደሚገባ።

👉ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን መገዛት እንደሚገባ።

👉ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ፍፁም ድንግልና።

👉ስለ ጌታችን ፍፁም ሕማምና መከራ።

👉ስለምሥጢረ ቁርባን።

✍ጥ ተራ (ቁ) 4⃣👉የአለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት የት ይገኛል??

*//መልስ//*

👉በሆላንድ ሀገር  / በጆኔቫ ይገኛል።

.
✍ጥ ተራ(ቁ) 5⃣👉 ከገነት ፈሳሽ ወንዞች መሀል ኢትዮጽያን የከበበው ወንዝ ማን ይባላል?
ከመጽሀፍ ቅዱስ ማስረጃ ጥቅስ ??

*//መልስ*//

👉*ግዮን ይባላል*
*ዘፍ 2:13*

✍ጥ ተራ (ቁ) 6⃣👉የክርስቲያን  የችግርና የመከራ  መፍቻ ምንድነው??

*//መልስ//*

👉ፆም ፀሎት ሥግደት እግዚአብሔርን በትዕግስት ማገልገል ዘ.ዘተ ናቸው።


 ✍ጥ ተራ (ቁ) 7⃣👉ጥቂት የሰሌን ፍሬዎች እየተመገበ  በበረሀ በተጋድሎ ሲኖር የነበረው ፃድቅ ማነው ይባላል ለስንት አመትስ በተጋድሎ  ኖረ??

*//መልስ//*

👉ፃዲቅ አቡናፍር ናችው።

👉በምድር ላይ 60 አመት ኑረዋል።

✍ጥ ተራ(ቁ) 8⃣👉 ጠፈርን የሚያቀዘቅዘው  ወንዝ ማን ይባላል??

*//መልስ//*

👉ዋኖስ ይባልላ።

✍ጥ ተራ(ቁ) 9⃣ 👉እርፈ መስቀል ማለት ምን ማለት ??

*//መልስ//*

👉የጌታችን ቅዱስ  ክቡር  ደሙ የሚሰትበት ማንኪያ ማለት ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣0⃣👉የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ጥናት በስንት ይከፈላል ጥቀስ/ጥቀሽ?

*//መልስ//*

በሦስት ይከፈላል እነርሱም፦ 1ኛ 👉የጥንት ቤተክርስቲያን ታሪክ ጥናት

2ኛ👉የመካከለኛ ቤተ  ታሪክ ጥናት

3ኛ👉አዲስ  ታሪክ ጥናት በመባል ይታወቃሉ።
ክርስቲያን
የቤተክርስቲያን
✍ ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣👉የአጹማት ማውጫ የሚሆኑ 7 ቀመሮች አሉ  እነርሱን በዝርዝር አስምቀጥ / አስቀምጭ??

*//መልስ//*👇

👉ዓውደ እለት

👉ዓውደ ወርቅ

👉ዓውደ አመት

👉ዓውደ ምክቲ

👉ዓውደ ፀሐይ

👉ዓውደ መሀተብ

👉ዓውደ አብይ ይባላሉ።

✍ጥ ተራ(ቁ)1⃣2⃣👉 የቅዱስ ላሊበላ ውቅር ቤተ ክርስቶያኖች  11አሉ የእነርሱን ቅዱሳን ስም ስያሜ  ዘርዝሩ ??

*//መልስ//*

*እነሱም፦*
1ኛ ቤተ መድሀኒአለም
2ኛ ቤተ ማርያም
3ኛ ቤተ መስቀል
4ኛ ቤተ ደናግል
5ኛ ቤተ ጎለጎልታ
6ኛ ቤተ ቀራኒዮ
7ኛ ቤተ ጊዮርጊስ
8ኛ ቤተ ገብርኤል
9ኛ ቤተ አማኑኤል
10ኛ ቤተ መርቀሪዎስ
11ኛ ቤተ አባ ሊባኖስ ይባላሉ።👆🏻

 ✍ጥ ተራ(ቁ)1⃣3⃣👉 ለመጀመርያ ግዜ እግዚአብሔር ይፍታ ያሉት አባት ማን ይባላሉ??

*//መልስ//*

👉አባ ጼጥሮስ ይባላሉ።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣4⃣👉⃣ የቤተክርስቲያንናችን ሊቅ የዜማው ደራሲ ብርሀነ አለም ቅዱስ ያሬድ የመጀመርያው ዜማው ምን በመባል ይጠራል??

*//መልስ//*👇

👉አራራይ ይባላል። አራራይ ማለት፦ የማትጠፋ ማለት ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣👉⃣የብሉይ ኪዳን መጽሀፍ ከእብራይስጥ ቋንቋ ወደ ግሪክ  እነማን ናቸው ?ማን በነገሰ  ዘመን ቀየሩ??

*//መልስ//*👇

*በዘመኑ የነበሩት  7ቱ ሊቃውንት  ናቸው። ጥሊሞስ በነገሰ ዘመን ነው ከእብራይስጥ ወደ ግርክ ያስቀየረውና የቀየሩት።*

ሊቃውንት✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣👉ኢትዮጵያ የሚለው ቃል የእያንዳንዱን የፊደል ትርጉም ዘርዝሪ/ ዘርዝር??

ለምሳሌ ኢ ማለት
ት ማለት ምን ማለት ነው?

*//መልስ//*

ኢ= ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው።

ት= ማለት ትፍሥሕት ወሐሴት ማለት ነው።

ዮ= ማለት የድ የማነ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ጵ= ማለት ጵርስፎራ ማለት ነው።

ያ= ማለት አንተ ኬንያሁ ማለት ነው።

ከፊደላት ትርጓሜ የተወሰደ።

✍ ጥ ተራ (ቁ) 1⃣7⃣👉ሊቅና ፃዲቅ አባ ጊዎርጊስ ዘጋስጫ የት ሀገር ተወለዱ በስንት? ዓ.ም ?? ተወለዱ? የእናትና  የአባታቸው ስም ማን ይባላል የመጀመሪያው ድርሰታቸው ምን ይባላል??

*//መልስ//*👇

👉የትውልድ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ሲሆን በ 1357 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሰግላ በተሰኘው ቦታ ተወለዱ አባታቸው ህዝበ ጽዮን ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ አምሀ ጽዮን ይባላሉ። የመጀመርያ ድርሰታቸው አርጋኖን ይባላል ።

✍ጥ ተራ (ቁ)1⃣8⃣👉መጽሐፈ ቀለሚንጦስ ከ81 መጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ሲሆን የጻፉት ቅዱስ አባት ማን ይባላል???

*//መልስ//*👇

👉መጽሐፈ ቀለሚንጦስን የጻፉት ቅዱስ  ቀለሚንጦስ ሲሆን ቅዱስ ቀለሚንጦስ የተወለዱት  ሮም ውስጥ ነው።

 ያደጉትም በሮምና አካባቢዋ ነው። ቅዱስ ቀለሚንጦስ የሮም አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ሲሆን የቅዱስ ጴጥሮስ ረድዕ(ደቀመዝሙር) ነበሩ። ፊሊ 4፥3።  ክህነታቸውንም የተቀበሉት  ከመምህራቸው  ከቅዱስ ጴጥሮስ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣9⃣👉የዓለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ጉባኤ ዓላማ ምንድን ነው??

*//መልስ//*👇

👉የአለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ጉባኤ  ዋና አላማ፦  ከሁሉም በላይ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም ሳይሆን ጥላቸውን እንዲቀንስ፣ የሃይማኖት ጦርነት እንዳይኖር የክርስቶስን ሰላም ቤተክርስቲያንየሚፈጠሩትን እንዳታጣ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ በወንድማማችነት የራሳቸው ባላቸው መንፈስ እየተሰበሰቡ በመካከላቸው የተፈጠሩትንና ለወደፊትም  ችግሮች ለማስወገድ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 2⃣0⃣👉የፕሮቴስንቲዝም ሃይማኖት መነሻ የሆነው  ማነው??

*//መልስ//*👇

*//መልስ//*👇

👉ማርቲን ሉተር ነው።

*ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል።ስተት ካለብኝ አርሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ!!*

*ወስብኃት ለእግዝአብሔር*saramareyama.890@gamail.com

1 አስተያየት:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...