2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የ5ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የማጣሪያ ውድድር

https://youtu.be/wlZ-cp5t-dE


*በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_❤ውድ ተወዳጆች ሆይ እንደምን ቆያችሁ?? ሰላማችሁ ብዝት ይበል አሜን፫_

*5ኛ ዙር የማጠርያ/ የማበላለጫ የተወዳዳሪዎች ጥያቄ የማጠቃለያ መልስ እንደሚከተለው ይቀርባል፦*👇
፨፨፨፨፨፨፨♥♥♥፨፨፨፨፨


✍የጥ ተራ (ቁ) 1⃣  ✔መልስ✔ ጌታችና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከአብርሀምና ከዳዊት ዘር መወለዱን ለማስረዳት ከአብርሃም እስከ ቅድስት ድንግል ማርያም ድረስ በሰፊው ስለ ፃፈው ከጥንት ጀምሮ ማቴዎስ በገጸ-ሰብእ ተመስሏል። ከሦስቱ ወንጌላውያን ይልቅ በማቴዎስ ወንጌል ክርስቶስ ወልድ እጓል እመሕያው ልጅ በመባል ብዙ ጊዜ ስለተጠራ ለማቴዎስ የገጸ-ሰብእ ምልክት ካሰጡት ምክንያቶች አንዱ ነው።

✍የጥ ተራ( ቁ) 2⃣✔  መልስ✔ ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያና ወንጌላዊ እንደዚሁም ሰማዕት ነው። ቅዱስ ማርቆስ በአንበሳ ተመስሏል ጌታችንተብሎ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  አሸናፊው የይሁዳ አንበሳ  መሰየሙን በራዕይ ዮሐንስ ተጽፏል(፭) ቅዱስ ማርቆስ በአንበሳ የተመሰለበት ዐብይ ምክንያት ደግሞ በግብጽ የነበሩትን የአንበሳ ዕጓል አንበሳ የተባለውን ክርስቶስን በመስበኩ ነው።

✍የ ጥ ተራ(ቁ)✔ መልስ ✔ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ በላም ይመሰላል። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት መወለዱን በዕለተ ልደቱም የከብት እረኞች ከመላእክት ጋር መዘመራቸውን ከሌሎች ወንጌላውያን ሠፋ አድርጎ ስለሚተርክ ነው። ከዚህም ሌላ ላም በብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት እንስሳ ሲሆን ሉቃስም የክርስቶስ መሰዋዕትነት በፊሪዳ ምሳሌ ጽፎታል። በዚህም መሰረት ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ክርስቶስ ቀርነ መድኃኒር እንደሆነ ነቢዩ ዘካርያስየተናገረውን ትንቢት በመግለጽ ስለፃፈ የላም ምልክት እንደተሰጠው መተርጒማን ሊቃውንት ይናገራሉ።



✍የጥ ተራ (ቁ) 4⃣✔መልስ✔ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በንስር ተመስሏል ንስር ከሌሎች አዕዋፍ ሁሉ ተለይቶ ወደ ላይ መጥቶ ይበራል። በላይም ሆኖ በመሬት ላይ ያሉትን ረቂቃን ነገሮች አጣርቶ መመልከት ይችላል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ሲጽፍ ከወንጌላውያኑ አፃፃፍ በተለየ በምሥጢረ ሥላሴ ይጀምራል ስለ ሥጋዌም ሲጽፍ ወደ ላይ መጥቆ በማሰብ ቅድመ ዓለም ስለነበረው ቃል ይተርክና ያ ቀድሞ የነበረውን ቃል ሥጋ ሆነ በማለት ይጽፋል። ቅዱስ ዮሐንስ ረቂቅና ጥልቅ የሆነውን ትምህርት ያስተምር ነበር።ለዚህም "እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ክርስቶስ ሕይወት ነው።"የሚሉትን የመሳሰሉት ናቸው።

_ስለ ቃሉ የቃሉ ባለቤት ልዑል አምላካችን የተመሰገነ ይሁን አሜን፫_

*_አውቄው ሳይሆን ከአነበብኩት ገልብጨው ነው። ይልቁንም ከእናንተ የበለጠውን እማራለሁ_*

*ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ መጠየቅ ይችላል*

*ወስብኃት ለእግዚአብሔር*saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...