2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የ4ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የጠያቄና መልስ ውድድር

*✝_በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

 *_አራተኛ (4) ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር_*

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕፀ መስቀል ላይ ሁኖ  ደሙ ሲፈስ የጌታዬ ደም እንዴት ይፈሳል አያለሁ ብሎ በጽዋ የተቀበለው ሊቀ መላእክት ማነው???.

*//መልስ//*

 ቅዱስ ኡራኤል ነው።

✅ ጥ ተራ (ቁ) 2⃣ አዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፈልን ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ የፍቅር ባህሪያትን ጥቀስ/ሽ

*//መልስ//*

ፍቅር👉 ይታገሳል፣ አይቀናም፣ አይመካም፣ አይታበይም፣አይበዳጭም፣ ሁሉን ያምናል።
1ኛ ቆሮ 13፥4 -7

✅ጥ ተራ (ቁ) 3⃣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ቅዱስነት፣  ኃያልነት፣ አዋቂነት ጻዲቅነት፣ በጸሎቷ የመሰከረች ሴት/እናት ማናት/ማን ትላባለች??

*//መልስ//*

ቅድስት ሐና/ እመ ሳሙኤል ናት።

✅ጥ ተራ (ቁ) 4⃣ በአንዲት ትል ተበልቶ የመተው ንጉስ ማን ይባላል??

*//መልስ//*

ንጉስ ሄሮድስ

✅ጥ ተራ (ቁ) 5⃣ለመጀመርያ ጊዜ ማዕተብ ያሰረ አባት ማን ይባላል የምን ሀገር ተወላጂ ነው በስንት ዓመተ ምህረት ነው ማዕተብ ማሰር የተጀመረው??

*//መልስ//*.✍🏻

የሶርያ  ተወላጂ አባት ያዕቆብ አልበረዲ ናቸው 500-578 ዓ.ም ነው።

✅ጥ ተራም (ቁ) 6⃣ቤተክርስቲያን ሶስት በሮች አሏት። እነዚህ ሶስት በሮች የምን ምሳሌ ናቸው??

*//መልስ//*.✍🏻 የሶስቱ አበው አባቶች
የአብርሐም.የይስሀቅ. የያዕቆብ ምሳሌ ናቸው።

✅ጥ ተራ (ቁ)7⃣በቤተክርስቲያናችን ምንጣፍ እና መጋረጃ የምን ምሳሌ ናቸው??

*//መልስ.//*✍🏻ምንጣፍ.ምሳሌነቱ ለጌታችን  ሆሳዕና በአርምያ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያሉ የዘንባባ ዝንጣፊ ያነጠፉለት ምሳሌ ነው።

✅ጥ ተራ (ቁ)8⃣ጌታችንና ኢየሱስ ክርስቶስን ስዕለ አድህኖ መሳል ምክኒያት የሆነው ሠው ማን ነው??

*//መልስ//*.✍🏻በ14-37 ዓመተ/ምህረት ሮምን ይገዛ የነበረው "ጤባሬዪስ ቄሳር ነው።

✅ጥ ተራ(ቁ) 9⃣የመጀመርያው ኢትዮጵያ ጳጳስ በመሾም ወደ ኢትዮጵያ የተላከው የእስክንድርያ ፓትሪያርክ ማን ይባላል??

*/መልስ/*

✍ቅዱስ አትናቴዎስ

✅ጥ ተራ (ቁ)🔟ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታትን ስያሜን አስረዳ/ጅ??

*//መልስ//*

✍ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ስባለመመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ- አዳም ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ አርብይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ ፡፡

ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት አልሞተምናይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ  ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
ለመቀባት
እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣በገነት ውስጥ ስንት አይነት ዛፎች ነበሩ??

*//መልስ//*

በገነት ውስጥ 3 አይነት ዛፎች ነበሩ እነርሱም፦👇

✍1ኛ ዕፀ መብል-እንዲበሉት የተፈቀደላቸው ምግብ

✍2ኛ ዕፀ በለስ -እንዳይበሉ የተዘዙት ነው።

✍3ኛ ዕፅ ሕይወት--እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ የሚመገቡት የዘለዓለም ሕይወትን የሚሰጥ ምግብ ነው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣2⃣እግዚአብሔር ሌሎች ፍጥረታትን አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳም አቀንቶ ለምን ፈጠረው??

*//መልስ//*

✍ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን ለምን አቀንቶ ፈጠረው?፦

👉እርሱ ገዥ እናንተ ተገዥ ናችሁ ሲል ነው፣ እንዲሁም እናንተ ፈርሳችሁ በስብሳችሁ ትቀራላችሁ እርሱ ግን ትንሳኤ ሙታን አለው ሲል አቃንቶ ፈጠረው።

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣3⃣በሐዋርያት ጊዜ የነበሩት ዲያቆናት ስንት ናቸው እነማን ናቸው???
ዲያ/መልስ/*

✍ሰባት (፯) ናቸው እነርሱም

1ኛ ቅዱስ እስሲፋኖስ

2ኛ ቅዱስ ጰርሜናን

3ኛ ቅዱስ ጵሮኮሮስን

4ኛ ቅዱስ ኒቃሮናን

5ኛ ቅዱስ ጢሞናን

6ኛ ቅዱስ ኒቆላዎስን

7ኛ ቅዱስ ፊልጶስን ናቸው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣4⃣መጽሐፈ መነኮሳት የሚባሉት ስንት ናቸው ስማቸውስ??

*//መልስ//*

✍መፅሀፈ መነኩሳት የባሉት ሦስት ናቸው ፦ከምንኩስና በፊትና ከምንኩስና በኋላ የሚነበቡ መፅሀፍት ሲሆኑ እነርሱም ሶስት ናቸው (1ኛ)ፊልኪስዩስ (2ኛ)ማሪስሀቅ እና(3ኛ)አረጋዊ መንፈሳዊ ናቸው።

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣5⃣የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወይም ወንጌል ከፃፉት ቅዱስ ማቴዎስና ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት እንዲሁም ቅዱስ ሉቃስ እና ቅዱስ ማርቆስ ከአርድእት የሆኑበት ምክንያት ምንድን ነው??ለምስ ከሐዋርያት ብቻ ወይም ከአርድእት ብቻ አልፃፉትም??

*//መልስ//*

✔አራቱ ወንጌላውያን ሁለቱ ከአርድእት ሁለቱ ከሐዋርያት መሆናቸው (1ኛ)ስለአርድእት ክብር፦ሐዋርያት ጨርህገ ቢፅፉት አርድእት ለማስተማር በወጡ ጊዜ እኚህማ የውጭ ሰዎች ናቸው የውስጥ ሰዎች ቢሆኑማ ድርጊቱን ህገ ወንጌልን ይፅፉ ነበር ብለው አይሁድ ትምህርታቸውን  እንዳይከለከሉ (2ኛ)ስለወንጌል ክብር፦አርድእት ጨርሰው ቢፅፉት ይህችማ ተርታ ህግ ከመቀበልናት ድርጊቱማ  ሚስጥረ ተዓምራቱን በቤተ ኢያኢሮስ ሚስጥረ ፀሎትን በጌቴ ሰማኔ ሚስጥረ መንግስቱን በደብረ ታቦርሚስጥረ ምፅአቱን በደብረ ዘይት ባዩ ሐዋርያት ልብ ቀርታለች እያሉ አይሁድ ደገኛይቱን ወንጌል ከመቀበል እንዳይከለከሉ

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣6⃣ማቴ 2፥5-6" ..አንቺ ቤተልሔም የይሁድ ምድር ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም ሕዝቤ እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣል"" ተብሎ ሚኪያስ(5፥2) የተነገረው ትንቢት በሐዲስ ኪዳን ከጌታችን ልደት ጋር ያለው ሚስጢራዊ ንፅፅር ምንድን ነው??

*//መልስ//*

✍(1ኛ)ለጊዜው ህዝቡን የሚጠብቅ መስፍን ዘሩባቤል ነግሶባታል ፍፃሜው ግን ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዷል (2ኛ)ዘሩባቤል አህዛብ ገብረውለታል ለኢየሱስ ክርስቶስም ሰብአ ሰገል ገብረውለታል (3ኛ)ዘሩባቤል በቤተልሔም ድንኳን ተክሎባታል በክርስቶስ ጊዜም የብርሃን ድንኳን ተተክሎባታል ይህ ነው ምስጢራዊ ንፅፅሩ

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣7⃣በብሉይ ኪዳን ለመጀመርያ ጊዜ ስዕል የሳለው ሰው ማን ይባላል የሳለው ስዕልስ ምን ነበር??

*//መልስ//* ✍በብሉይ ኪዳን ዘመን ለመጀመርያ ጊዜ ስዕልን የሳለው ሙሴ ሲሆን   ስዕልም ይህ ነው እግዚአብሔርም ሙሴን አለው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች የሳለውእንደፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤ በሰበርኸቸውም በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ። ዘፀ 34፥1-5 ስታነቡት ሙሉውን ታገኙታላችሁ።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣8⃣መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት(፪) የኤማውስ መንገደኞች እያለ የሚጠራቸው ሰዎች ማን ማን ይባላሉ??

*/መልስ//*

✍ቅዱስ የሉቃስና ቅዱስ ቀለዮጳ (የሉቃ ወንጌል 24፥13_18 )ላይ ይገኛል

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣9⃣ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ከአባቴ ብቻ በቀር ልጅም ቢሆን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የሚያውቅ የለም። ማቴ 24፥ 36 የዚህ ቃል አንድምታዊ ትርጉም አብራራ/አብራሪ)??

"""ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም""" ማቴ24፥36 ይህንን በመጥቀስ ጌታ የሚመጣበትን ቀን አያውቅም ስለዚህ ሁሉን የሚያውቅ ሁሉን የሚችል አምላክ አይደለም የሚሉ መናፍቃን አሉ ነገር ግን ዮሀ ራዕ1፥8'""ያለውና የነበረው የሚመጣው ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ ""' በማለት ሁሉን የሚችል ከእርሱ በላይ ማንም የሌለ መሆኑን ይናገራል በተጨማሪም ጌታ በማቴ24፥1-55 ባለው የምፅአቱን ዋዜማ እንዴት እንደሆነ ግልፅ አድርጎ ተናግሯል ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማወቁ ነው ታድያ ስለምን ልጅም ቢሆን አያውቅም አለ? (ሀ)ቀኒቱን ከአዳም ልጆችና እና ከመላእክት ሲለያት ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለይ አይደለም የሰው ልጅ ብሎ የአዳምን ልጆች ይጠራልና (ለ)አንድም ወልድ ቅድመ ተዋህዶ አላዋቂ የነበረን ስጋ እንደተዋሐደ ለማስረዳት በእውነት ጌታ የሰውን ባህሪ ባህሪው ማድረጉን ሊያስረዳን ፈልጎ ነው እንዲህ ሲባል ከተዋህዶ በኋላ ስጋ አላዋቂ ነው ማለት አይደለም ከመለኮት ጋር አንድ አካል አንድ ባህሪ ከመሆኑ በፊት ያለውን ሲናገር ነው እንጂ (ሐ)አንድም አብ ለልጁ በመስጠት አውቋታል ወልድ ግን በስራ አላወቃትም ይህም  ማለት ጊዜው እስኪደርስ በልቤ አኖራታለሁ በኋላ ግን በቃልነቴ እናገራታለሁ ሲል ነው አብ ልብ ወልድ ቃል መንፈስ ቅዱስ ህይወት ነውና በቃልነቱ በስራ የሚገልፅበትን ሲናገር ነው (መ)አንድም ወልድ ብቻ ያለ አብ አያውቃትም ሲል ነው ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ አያውቃትም በባህሪ በማወቅአንድ ናቸውና ንባቡ '""ወልድም ቢሆን ያለ አብ ብቻውን""' ስለሚል ነው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 2⃣0⃣ ከሐዋርያት ውስጥ ሞትን ያልቀመሰው እና የተሰወረው ቅዱስ ማነው??

*//መልስ//*✍ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

*_ውድ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ እህት ወንድሞቼ ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ በማንኛውም ሰዓትና ጊዜ ለመታረም ዝግጁ ነኝ_*

*✍ወስብኃት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

1 አስተያየት:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...