2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የ3ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

*በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!የእግዝአብሔር ፍፁም ሰላም ይብዛላችሁ ይብዛልን_

*ሦስተኛ(3ኛ) ዙር የጠቅላል እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር* _እንደሚከተለው ነው_

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣"አንቺ ሴት ከአንች ጋር ምን አለኝ"? በሚለው ኃይለ ቃል ውስጥ ሴት የሚለው ቃል....ነው??

ሀ/ በእስራኤላውያን የትሕትና አነጋገር ነው።

ለ/ የቁጣ አነጋገር ነው።

ሐ/ ሥጋሽ ከሥጋዬ አጥንትሽ ከአጥንቴ ማለት ነው።

መ/ ሀ እና ሐ መልስ ነው።

*//መልስ//*

መ/ ሀ እና ሐ መልስ ናቸው።
1ኛ👉 በእስራኤላውያን የትሕትና አነጋገግ ነው።

2ኛ 👉አጥንትሽ ካጥንቴ ሥጋሽ ከስጋዬ ማለት ነው። ዘፍ 2፥23 ላይ ማየት ይላልቻ።።

 ጌታችንም  ድንግል ማርያምን አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋሽ ስጋን ከነፍስሽ ነፍስን ነስቼ አካልሽን አካል ባህሪሽን ባህሪ አድርጌ ሰው ሆኛለሁና ማለቱን የሚያመለክ የአክብሮትና የፍቅር ሐይለ ቃል እንደሆነ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን  ያስተምራሉ።

✅ጥ ተራ (ቁ) 2⃣ሃይማኖት ማለት ምን ማለት ነው? ሃይማኖት ከማን የተሰጠ ሥጦታ ነው??

*//መልስ/*

“ሃይማኖት ወይም እምነት” አምነ አመነ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ዘር ወይም ስም፤ ፤ ሲሆን ትርጉሙም አንድን እውነት መቀበል፤ በአንድ ክፍል ላይ ተስፋ ማድረግ ወዘተ ማለት ነው።
ስለ እምነት ወይም ሃይማኖት ምሥጢራዊ ትርጉም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚከተለው በግልጽ አስቀምጦታል፡
👉 “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው” ዕብ.11፡1 በዚህ ቃል መሠረት እምነት ተስፋ የምናደርገው ነገር ሁሉ እርግጠኛ ስለመሆኑ፤ የማናየውንም ነገር የሚተርክ የሚያስተምር ነው።

በመቀጠልም ሐዋርያው “ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደተዘጋጁ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን” ዕብ.11፡3 ይላል ። በመሆኑም እምነት ስለፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር ያለውን
እውነት እንዲሁም ከእርሱ ዘንድ ያለውን ተስፋችንን
የሚያስረዳ፤ የሚያረጋግጥልን እውነት፤ ሁሉንም የምናይበት የልብ መነጽር ነው። ስለዚህ መንፈሳዊውን  ለማወቅና የአምላክን  ለመሳተፍ ማመን እጅግ ተፈላጊና መሠረታዊ ነገር ወይም ምሥጢር ነው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 3⃣ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ  ኢትዮጵያ ከሚለው መጠርያ ስሟ ሌላ ማን ማን እየተባለች ትጠራ ነበር??

*//መልስ//*
1ኛ👉የካም ልጅ ፉጥ በኢትዮጵያ ምድር ስለሚኖር #ፉጥ ተብላለች

2ኛ👉 ቶኔቶር ትባል ነበር ቶኔቶር ማለት ሀገረ እግዚአብሄር ማለት ነው።

 3ኛ👉ሊቀ ነብያት ሙሴ ኢትዮጵያን የኩሽ ምድር እያለ ይጠራት ነበር

4ኛ👉ኢትዮጲስ ተብላለች

5ኛ👉ሳባ የተባለ የኩሽ ልጅ ይኖርባት ስለነበር የሳባ ምድር ትባል ነበር

6ኛ👉ሰብታ ወይም አቢስ ይኖርባባት ስለነበር አቢሲኒያ ተብላለች

✅ጥ ተራ (ቁ) 4⃣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሀገረ ሥብከታቸው የት የት እንደሆነ አስረዳ/ጂ??

*//መልሱን በድምፅ /ከቭዲዮመስዋት/ኦ/ አዳምጡ*

✅ ጥ ተራ (ቁ) 5⃣ በቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ የኦሪት  የሚሰዋባቸው አብያተ ክርስቲያናትን ጥቀስ/ጥቀሽ??

*መልስ*

 (1ኛ)መርጡ ለማርያም

 (2ኛ)ተድባባ ማርያም

(3ኛ)አክሱም ፅዮን

 (4ኛ)ብርብር ማርያም

 (5ኛ)ጣና ቂርቆስ ናቸው

✅ጥ ተራ ( ቁ) 6⃣የጌታችን የመድኃኒታችን 9ኙ ባዕላት የምንላቸው ምን ምን ናቸው??

*//መልስ/፦*

1ኛ👉�ፅንሠት
2ኛ 👉�ልደት
3ኛ👉�ጥምቀት
4ኛ👉� ደብረ ታቦር
5ኛ👉� ሆሳህና
6ኛ👉� ስቅለት
7ኛ👉� ትንሳኤ
8ኛ👉� እርገት.ክርስቲያን
9ኛ👉�ጲራቅሊጦስ ናቸው።

✅ጥ ተራ ( ቁ) 7⃣ቤተ  ክርስቲንያን ስንት ክፍሎች አሏት?? ምን ምን??

*//መልስ//*

1ኛ 👉መቅደስ
2ኛ 👉ቅድስት
3ኛ👉 ቅኔ ማህሌት

✅ ጥ ተራ (ቁ) 8⃣ ሰባቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተናራቸው ነገሮች(ሰባቱ አፅረሃ መስቀል የሚባሉት ምን ምን ናቸው??

*//መልስ/*👇

1,,, ኤሉሄ ኤሉሄ ለማ ሰብቅታኒ /አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ,,,, ማቴዎስ 27፥40

2,,,አባት ሆይ የሚያደርገትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ....ሉቃስ 23፥39..

3,,, ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ። ሉቃስ 23፥39

4,,, አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ሉቃስ 23፥46...

5,,, እነሆ ልጅሽ...እነሆ እናትህ....ዮሐንስ 19፥26...

6,,,ተጠማሁ፣...ዮሐንስ እና፥28...

7,,,ተፈፀመ...ዮሐንስ 19፥30....

✅ጥ ተራ (ቁ) 9⃣ የቤተ ክርስቲያን አስራ አራቱ/14/ ቅዳሴዎች ምን ምን ናቸው???

*//መልስ//፦*

1ኛ፦ ቅዳሴ ሐዋርያት
2ኛ፦ ቅዳሴ እግዚእ.
3ኛ፦ ቅዳሴ ማርያም
4ኛ፦ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጎድ
5ኛ፦ ቅዳሴ ሰለስቱ
6ኛ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ
7ኛ፦ ቅዳሴ ባስልዮስ
8ኛ፦ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
9ኛ፦ ቅዳሴ ኤጲፋንዮስዲዮስቆሮስ

10ኛ፦ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ
11ኛ፦ ቅዳሴ ቄርሎስ
12ኛ፦ ቅዳሴ ያዕቆብ
13፦ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
14ኛ፦ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ

✅ጥ ተራ (ቁ) 🔟 ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ ሆሳዕና  በአህያ ላይ ለምን ተቀመጠ? ለምንስ በፈረስ ላይ አልተቀመጠም??

*//መልስ//*👇
👉�ትንቢትና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይልበሽ። አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልእል በይ እነሆ ንጉስሽ ጻድቅና አዳኝ ነው። ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመልጣ (ዘካ 9፥9) እንዲል።

•ተንኮለኛ ናት ለጠላትዋም ፈረስ አውድቃ ረግጣ ትገድላለች
•ረጋ ብላ መሄ አችልም ትቸኩላለች
•ልትወጣባት ስትልም ታስቸግራለች አትመችም ተነጣጥረህ ነው የምትወጣባት
•ጌታ የወደደውና በትንአምላክ አህያን መረጠ፡፡

በአህያ መቀመጡ
እደተገለጸው•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝብለው ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ መእመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡
•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ  ነው የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ፤እኛ በትእቢት ተይዘን ነው እንጂ በየዋህነት ብንመላለስ እሱ ያድርብን ነበር፡፡ እኛ የእግዚአብሔር ማደርያ ነንና፡፡

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣ጌታችን በመጣ ጊዜ የምንጠየቃቸው "6"ቃላተ ወንጌል የምንላቸው ምን ምን ናቸው??

*//መልስ//*
 👉ተርቤ አላበላችሁኝምምዕራፍ

👉ተጠምቸ አላጠጣችሁኝም

👉 የማቴዎስ ወንጌል  25፥33 -46 ላይሙሉውን መመልከት ይቻላል።

✅ ጥ ተራ (ቁ)1⃣2⃣ በ186 ዓ.ም በፍቼ የተወለዱና ከኢትዮጵያ የመጀምርያ አራት ጳጳሳት አንዱና የምሥራቅ ኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት። በኋላም ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም በኢትዮያ ላይ የግፍ ጦርነት ባነሳ ጊዜ እምቢ ለሃገሬ ለሃይማኖቴ በማለታቸው ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በፋሽስት ኢጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት ታላቅ አባት ማን ይባላሉ??

*//መልስ//* 👇

ታሪካቸውን የማንዘነጋው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ናቸው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣3⃣ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "በኩር" የሚባልበት ምክንያት

ሀ/የአብ አንድያ ልጁ ስለሆነ

ለ/ በእስራኤላውያን መጀመርያ ማኅፀን የሚከፍት ልጅ በኩር ስለሚባል

ሐ/ ሞት የማይገዛው ትንሣኤን ለመነሣት እርሱ የመጀመርያ ስለሆነ

መ/ ሁሉም መልስ ነው።

*// መልስ//*

መ/ ሁሉም

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣4⃣እመቤታችን በስደቷ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ ያረፈችበት ቦታ__ይባላል??

*//መልስ//*

በጣና ደሴት ሦስት ወር ከአስር(10)ቀን ቆይታለች

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣የቃል ኪዳኑ ታቦት ከማይነቅዝ እንጨት የተሰራና ከውስጥም ከውጭም  በወርቅ የተለበተ መሆኑን፤ የሚያስረዳን የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል የትኛው ነው??

*//መልስ//*

ዘጸ.25፥1-22 ላይ ይነግረናል።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያትን ትምህርት 81 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምትቀበል ስትሆን ሦስቱን  አብያተ ክርስቲያን ጉባኤያትንም ትቀበላለች። የምትቀበላቸውን የጉባኤያትን ስም ጥቀስ/ጥቀሽ

*//መልስ//*👇
ኒቂያ  ጉባኤ ፣ ቁስጥንንጥንያና አፌሶን ናቸው የነዚህን ጉባኤያት ውሳኔዎቻቸውን ትቀበላለች። ሌሎች ጉባኤዎችን አትቀበልም።

✅1⃣7⃣የሙሴን ሕግ በብዙ ጥንቃቄ እንተረጉማለን የሚሉና ሰውም ሕጉን እንዳይተላለፍ በማለት የራሳቸውን ትእዛዝና ሥርዓት ያወጡ በዘመነ ካህናት ጊዜ የነበሩ የቤተ  ክርስቲያን ጠላቶች ምን ተብለው ይጠራሉ??

ሀ/ ፈሪሳውያን

ለ/ ሰዲቃውያን

/ ኤሲያውያን

መ/ አይታወቁም

*//መልስ//*

ሀ/ ፈሪሳውያን የሐዋርያት 👉 ሥራ 15÷5 ላይ ይገኛል

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣8⃣አስራ ሦስቱ/ 13/ የጌታችን ህማማተ መስቀል የምንላቸው ምን ምን ናቸው??

*//መልስ//*

13ቱ ሕማማተ መስቀል

1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይመውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድመረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋርመላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)ጊዜ

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣9⃣በሐዋርያት ጊዜ  የነበሩ የመጀመርያዎቹ  መናፍቃን ምን ተብለው ይጠራሉ??

ሀ/ ግንስቲኮች

ለ/ ቢጽ ሐሳውያን

/ አርዮሳውያን

መ/ ሁሉም

*//መልስ//*
*ለ/*👉ቢጽ ሐሳውያን ሐሰተኛ ወንድሞች ይባሉ ነበር። እነዚህም መናፍቃን ከአይሁድ ወገን ክርስትናን በመቀበል ካመኑና ከተጠመቁ በኋላ ተመልሰው ወደ አይሁድ ሃይማኖት ያዘነበሉ ናቸው።

✅ ጥ ተራ (ቁ) 2⃣0⃣ የግዝት በዓላት የማባሉት ስንት ናቸው?? ምን ምን ?

*//መልስ//*👉� አምስት (5) ናቸው
 1ኛ👉� የወልድ በዓል ወር በገባ በ29 ቀን
2ኛ👉�የመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓል ወር በገባ በ21
3ኛ👉�የመላአኩ ቅዱስ ሚካኤል በዓል ወር በገባ በ12 ቀን
4ኛ👉�እለተ ቅዳሚት ሰንበት
5ኛ👉�እለተ እሁድ ሠንበት ክርስቲያስቲያን ናቸው።

_ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አረሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ_
.
_ወስብሐት ለእግዚአብሔር_saramareyama.890@gmail.com

2 አስተያየቶች:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...