*በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫*
_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ?? ሰላማችሁ ይብዛ!!_
_፨የምዕራፍ ሁለት/17ኛ/ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
_↪ ጥ.ተራ (ቁ)1⃣✍ ቅዱስ ሉቃስ ስንት መጻህፍት ጽፏል ❓_
_፨መልስ፨ መልስ ሁለት የሉቃስ ወንጌል እና የሐዋሪያት ስራ።✅_
_↪ጥ.ተራ (ቁ)2⃣✍ ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈው ለማን ነው❓_
_፨ መልስ ፨ለቅዱስ ቴዎፍሎስ_✅
_↪ጥ.ተራ (ቁ) 3⃣✍ለመጀመርያ ጊዜ ስዕለት የተሳለ አባት ማን ይባላል❓_
_፨መልስ፨ አባታችን ያዕቆብ ነው ዘፍጥረት 28፥20_✅
_↪ጥ.ተራ (ቁ)4⃣✍ ሄኖክ ማለት ምን ማለት ነው?? መጽሐፈ ሄኖክስ በስንት ዓ.ም ተጠረዘ❓_
_፨መልስ ፨ሄኖክ ማለት አዲስ ማለት ነው።ሲሆን መጽሐፈ ሄኖክ በ4014 አመተ አለም ቅድመ ልደት ክርስቶስ ነው የተፃፈው። የተፃፈበት ቦታ ደብረ ቅዱስ ይባላል ይህ ቦታ ከገነት ትዮዩ የሆነ ቦታ ነው።_✅
_↪ጥ.ተራ (ቁ) 5⃣✍ከሚከተሉት ከ፲፪(ከአስራ ሁለቱ)የሐዋርያት ወገን የቱ ነው❓_
ያልሆነውሀ) ጳውሎስ
ለ) ጴጥሮስ
ሐ) በርተሎሜዎስ
መ) ዮሐንስ
_፨መልስ፨ ሀ) ጳውሎስ ✅_
_↪ ጥ.ተራ (ቁ)6⃣✍ሐዋርያ ማለት ምን ማለት ነው❓_
ሀ) የተላከ
ለ) ልዑክ
ሐ) ሂያጅ
መ) ሁሉም መልስ ነው
፨መልስ፨መ) ሁሉም መልስ ነው ✅_
_↪ጥ.ተራ (ቁ)7⃣✍ቅዱስ ሉቃስ ማነው❓_
_ሀ. ወንጌላዊ ነው_
_ለ. ሰአሊ ነው_
_ሐ. ሀኪም ነው_
_መ. ከ 72 አርድት መካካል ነው_
_ሰ. ሁሉም መልስ ነው_
፨መልስ፨.........መ)
_↪ጥ.ተራ(ቁ)8⃣✍ የብሔረ ብፁሀንን ታሪክ የፃፈው አባት ማን ይባላል ❓_
_የፃፈው ቅዱስ አባትስ ከብሔረ ብፁሀን ሲመለስ ምን አጋጠመው❓_ያጋጠመው
፨ መልስ፨
ቅዱስ ዞሲማስ ነው። ሲመልስ
ከሰራዊቱ ጋር ሁኖ ሲመለስ ዲያቢሎስ የብሔረ ብፁሀንን ታሪክ መጽሐፍንም ሊወስድበት ከጀለ ነገር ግን በእግዚአብሔር እና በመላእክትናን ተራዳኝነት ሰይጣንን ድል አድርጓል። ✅
_↪ ጥ.ተራ(ቁ)9⃣✍በኃጢአያት የሚያደርገን ምንድነው❓_
_ሀ/ ምክንያተኝነት_
_ለ/ ለመንፈሳዊ ነገሮች ያለንን ከበሬታ መቀነስ_
_ሐ/ ወደ ኃጢአያት የሚመራንን ነገር አለማቑረጥ_
_መ/ ሁሉም መልስ ነው_ዳዊት
_፨መልስ፨ መ/ ሁሉም ነው።✅_
_↪ ጥ.ተራ (ቁ)🔟✍ከአብረሀም እስከ ያለው ዘመን ምን ይባላል❓_
_ሀ/ ዘመነ አበው ይባላል_
_ለ/ ዘመነ ነቢያት ይባላል_
_ሐ/ መልሱ የለም_
_፨መልስ፨ ሀ/ ዘመነ አበው ይባላል።_✅
_↪ጥ.ተራ(ቁ)1⃣1⃣✍በሙሴ ስም ከሚጠሩት ቅዱሳንይ መካክል የምታውቀውን ጥቀስ/ሽ❓_
_፨መልስ፨_👇
1-ሊቀ ነቢያት ሙሴ
2-አቡነ ሙሴ ዘድባ
3-አቡነ ሙሴ ዘገርአልታ
4-ሰማዕቱ አቡነ ሙሴ
5-አቡነ ሙሴ ዘትግራይ
6-አቡነ ሙሴ ጸሊም
7-አቡነ ሙሴ ዘቡልጋ
8-አቡነ ሙሴ ዘገዳመ ሲሐት
_↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣2⃣✍ዮሴፍ የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ ድንግል ማርያምን አላወቃትም፤ ሲል ምን ለማለት ነው❓_
_፨መልስ፨_👇
_ _፦ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን_ _ትመስላለች:: ብርሌ_
_የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ_ _ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ_
_ይቀያየራል:: እመቤታችንም_ _ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ_
_መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ_ _አብሮ ሲለዋወጥ እያየ_
_ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::_
_+'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ። __ያለውስ ማን ነው?' _እያለ_
_ይጨነቅ ነበር:: ጌታን_ ከወለደች_ _በሁዋላ ግን አንድ_
_ሕብረ መልክ ሆናለችና::_ _አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች_
አላወቀም::_
_+አሁን ግን ልጇ አምላክ_ _ዘበአማን: እርሷም ወላዲተ_
_አምላክ መሆኗን አወቀ ማለት ነው።✅_
_↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣3⃣✍_
_በታምረ ማርያም ፀሎት ላይ 3_ _ጊዜ እሰግድ ለኪ(3)!_
_ብለን እንሰግዳለን፣ይህንን_ _ሰግደት ያሰተማረን ቅዱስወርቅ አባት_ _ማን ይባላል❓_እንዴትስ ተጀመረ❓
_፨መልስ፨_✍
_ዮሀንስ አፈ አሀዛብን በሚያስተምርበት ወቅት የእመቤታችን ስዕል አፍ አውጥታ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች… እርሱም ታጥቆ 3 ጊዜ የሰገደላትን ለማስታወስ ነው።_✅
_↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣4⃣✍የሚስጥረ ትንሳኤ ሙታን አፈፃፀም ከመፃፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱስ ጳውሎስ ከፃፈው ሁለቱን ጥቀሱ ❓_
_፨መልስ፨_👉ወደ ኤፊ_ 2፥1 በበደላችሁና _በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ በእነርሱም በዚህ አለም እንዳለው ኑሮ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሰራው መንፈስ አለቃ እንደኮነው በአየር ላይ ስልጣን እንዳለው አለቃ ፍቃድ በፊት ተመላለሳችሁባቸው_
_ሮሜ 1፥4_
_ይህም ወንጌል በስጋ ከዳዊት_ _ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና_ _መንፈስ ግን ከሙታን መነሳት_ _የተነሳ በሀይል የእግዚአብሔር_ _ልጅ ኮኖ ስለተገለጠ ስለ ልጁ_ _ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ_ _ክርስቶስ ነው።_
_ሮሜ 1 ፥3-4ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን_ _ከሙታንሥራው መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ_ _ክርስቶስ ነው።_
_2ኛ ቆሮ 1፥9 ወዘተ..._✅
_↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣5⃣✍እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥ በቀድሞ መጀመሪያ…ከጥንቱ *ከዘላለም* ጀምሮ_ *_ተሾምሁ* ፤ ምድር _ከመፈጠርዋ_ አስቀድሞ።_
_ቀላያት ገና ሳይኖሩ እኔ_ _*ተወለድሁ* ፥ የውኃ ምንጮች ገና ሳይፈልቁ… ተራሮች ገና_ _ሳይመሠረቱ፥ ከኮረብቶች በፊት_ _*እኔ ተወለድሁ፥* የሚለውን ቃል *እግዚአብሔር ወልድ* ከተጥንት ከአባቱ ከእግዚአብሔር አብ_ _*መወለዱን* በመንፈስ ቅዱስ የገለፀለት ቅዱስ ማን ይባላል❓_
_፨መልስ፨_......ንጉሥ ሰሎሞን ነዉ።
መፅሀፈ ምሳሌ ምዕ8:22—23
_↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣6⃣✍*1*/, ነብዩ ኤርሚያስ አገልጋዩን ጠርቶ ለንጉስ ኢዮአቄም ትንቢቱን እንዲያነብለት አዘዘው፤ይህ የኤርሚያስ አገልጋይ ማን ይባላል ?ንጉስ ኢዮአቄምስ ትንቢቱን ሰምቶ ምን አደረገ❓_
_ፍንጭ ኤር(36፤23)_
_፨መልስ፨_👇
_~የኤርሚያስ አገልጋይ ባሮክ ሲሆን ንጉሱም ትንቢቱን ሰምቶ በእሳት አቃጠለው ፤እሱም ተቀሰፈ_
_ባሮክም ትንቢቱን ከኤርሚያስ እንደገና ፃፈው_✅
_↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣7⃣✍በአንድ ወቅት የሶርያው ንጉስ በብዙ ሺ ሠራዊት እስራኤልን ከበበ ፤የኤልሳ ደቀመዝሙር የነበረው ግያዝም የሰራዊቱን ብዛት አይቶ ጌታዬ ዛሬስ መጥፋታችን ነው ! እያለ ጮህ ይህን ግዜ ኤልሳ ለግያዝ ምን አለው ? ልባምላክ ዳዊትስ ይህን በተመለከተ በመዝሙሩ ላይ ''ይትዓየነን መልአክ እግዚአብሔር አውዶሙ ልእለ ይፈርሆ ወይአድሃኖሙ'' ብሎ ዘመረ ምን ማለት ነው❓_
_ፍንጭ 2ኛ ነገስት (6፤16)፣(መዝ 33፤7)_
_፨ መልስ፨_👇
_ከእኛ ጋራ ያሉት ከነርሱጋር_ _ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ_
_1ኛ ነገስት (6፤16)_✅
_↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣8⃣✍እኛ ከየት ይሆን የተጠራነው እንደ ኤርሚያስ ከማሀፀን ? ወይስ ከአለም እቅፍ ?ከሀጢያት ባሀር ወይስ ከሞት አፋፍ ? ከአፈር እና _ከትብያ ላይ ወይስ ከምን_ _ይሆን የተጠራንው_
_ሙሴ እና ዳይት_ _ከእረኝነት፤ጴጥሮስን እና_ _እንድርያስን ከአሣ አጥማጅነት_ _የጠራ እግዚአብሔር ኤልሳዕን_ _ከምን ነበር የጠራው ?_በሬ _ጳውሎስ እና ሙሴ ፀሊምንስ❓_
_፨መልስ፨_
_ኤልሳዕን 12 ጥማድ እያረሰ ፤_
_ጳውሎስን ካሳዳጅነት ፤ሙሴ_ _ጸሊምን ከሽፍታነት_
_↪ ጥ.ተራ (ቁ)1⃣9⃣✍በቅዳሴ ላይ እንዲህ እያልን_ እናመሰግናለን_ _ሱራፌልይጸርውሁ ይሰግዱ_ _ሎቱ ወክሩቤል ይሴብሕዎ _ _እንዘይበሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ_ _እግዚአብሔር ,,,ይሄንን_ _ምስጋና በመፃፍ ቅዱስ የትኛው ምእራፍ ላይ እናገኘዋለን ❓_
_፨መልስ፨_👇
_በትንቢተ ኢሳያስ ምእራፍ 6 ላይ ነው ፤ወንጌሉ እና ቅዳሴው እርስ በራሳቸው ይናበባሉ ለእያንዳዱ የቅዳሴ ዜማ እራሱን የቻለ የመፃፍ ቅዱስ ጥቅስ አለው።_
_↪ጥ.ተራ (ቁ)2⃣0⃣✍ዲያቆናቱ በቅዳሴ ላይ ስለዝናብ እንማልዳለን ፣ስለተጨነቀች ነፍስ እንማልዳለን ፣ስለታመሙ እና ስለድዊያን እንማልዳለን ---እያሉ ይጸልያሉ ፤ንጉስ ሰለሞን ቤተክርስቲያንን ከሰራ ቡሀላ እራሱ እንደ ዳቆን ሆኖ ይህንን ፀሎት ጸልዮ ነበር ፣እግዚአብሔር ለዚህ ጸሎት የሰጠው ምላሽ ምን ነበር ❓_
_ፍንጭ 1ኛ ነገስት (8፤35)፤_ _1ኛ ነገስት (9፤3)_
_፨መልስ፨_👇
_በፊቴ ያቀረብከውን ልመናና ፀሎት ፤አይኖቼ እና ልቤ ዘወትር ወደ ሰራከው ቤተመቅደስ ይሆናሉ 1ኛ ነገስት (9፥3)_✅
.890@gmail.com
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ