2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የምዕራፍ 2ት(11ኛ)ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

*_ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

*_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁ??*_

*_የምዕራፍ ሁለት (የ11ኛ) ዙር የቃል ጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል👇_*

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣ንስጥሮስ ወላዲተ ሰብእ ናት ብሎ በእመቤታችን ላይ የተናገረውን የክርደት ትምህርት የገለጠው ቅዱስ አባት ማን ይባላል??

*//መልስ//*👉ቅዱስ ቄርሎስ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 2⃣ አርዮስ እና ተከታዮቹ የተወገዙበት ጉባኤ ___ነው??

ሀ/ ጉባኤ ኒቅያ
ለ/ ጉባኤ ኤፌሶን
ሐ/ ጉባኤ ቁስጥንጥንያ
መ/ ሁሉም

*// መልስ//*👉መ ሁሉም ነው መልሱ 1ኛ👉 በ325 ዓ.ም የኒቂያ ጉባዬ ፦  አሪዮስ የተወገዘበተ

2ኛ👉381 ዓ.ም ቁስጥንጥንያ፦ የዚህ ጉባየ አላማ የነበረው የመንፈስ ቅዱስ ፍፁን አምላክነት ለካደው ለመቅድንዮስ ምላሽ ለመስጠት ነበር።

3ኛ👉431 ዓ.ም ኤፌሶን ጉባዬ ፦ ክርስቶስ ሁለት አካል ሁለት ባህሪይ የሚለውን የሐሰት ትምህረት በመቃወም ቅዱስ ቄርሎስ። የረታበት ጉባኤ ናቸው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 3⃣ ለመናፍቃን መልስ ከሰጡ ታላላቅ ቅዱሳን አባቶች መካከል ሦስቱን ጥቀስ/ ጥቀሽ??

*//መልስ//*👉አባ አትናቴዎስ፣ቅዱስ ቄርሎስ፣ ጎርጎርዮስ ዘእንዚዙ/ነባቤ መለኮት/፣
✍ጥ ተራ(ቁ)4⃣ ከኤፌሶን ጉባኤ በኋላ የተደረጉትን ጉባኤያት አምስቱ/5ቱ/ እኅት የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት እንዴት ያዩታል??

ሀ/ አይቀበሉትም
 ለ/ ይቀበሉታል
 ሐ/ እንደሁኔታው ይለያያል
መ/ ሁሉም

*//መልስ//*👉ሀ) አይቀበሉትም።

✍ጥ ተራ(ቁ) 5⃣በብሉይ ኪዳን ዘመን የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ያልሆነው የትኛው ነው??

ሀ/ የኖህ መርከብ
 ለ/ የአሳ ማጥመጃ መረብ ሐ/ ደብረ ሲና
መ/ የሙሴ ደብተራ ድንኳን

*//መልስ//*👉ለ) የአሳ ማጥመጃ መረብ

✍ጥ ተራ(ቁ)6⃣በሐዲስ ጌታችን ካስተማራቸው ትምህርቶች ውስጥ ስለጥቀስ ቤተክርስቲያን በምሳሌነት ከሚጠቀሱት መካከል ቢያንስ ሦስቱን /ጥቀሽ??

*//መልስ//*👉የአሳ ማጥመጃ መረብ/ማቴ. 13፥47/

👉ታላቅ የስንዴ አዝመራ /ማቴ.13፥24/

👉የከበረ ዕንቁ/ማቴ. 13፥45/

👉የሰናፍጭ ቅንጣት /ማቴ. 13፥31፣/ሉቃ. 13፥18/

👉የሠርግ ቤት/ ማቴ. 22፥1-10፣ዮሐ. 2፥1/

👉ሙሽራ /ኤፌ. 5፥21-33፣ራእ.21፥9-14 ወ.ዘተ ናቸው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 7⃣እንደ ቤተክርስቲያን ስዕራት   መሰረት ስንት አይነት ስግደት አለ??

ስግደት በ 3 ይከፈላል
1. የአምልኮ (የባህርይ ስግደት )ይህ ስግደት ለፍጡር ሳይሆን ለፈጣሪ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ብቻ የሚሰገደው ስግደት ነው፡፡
2.የፀጋ ስግደት ፡-ይህ ስግደት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለቅዱሳን መላእክት ፡ ለጻድቃን ሰማዕታትን የምንሰግደው ስግደት ነው፡፡
3.የአክብሮት ስግደት ፡-ይህ ደግሞ እርሰበርሳችን የምንለዋወጠው አክብሮታዊ ሰላምታ ነው፡፡
ከነዚ ሶስቱ የስግደት ዓይነቶች ቀጥለን የምንመለከተው በሁለተኛ ተራ ቁጥር ላይ የገለጥነውን የጸጋ ስግደት ነው፡፡

✍ጥ ተራ (ቁ)8⃣ የአራቱ/4ቱ/ አበይት ነብያት የትንቢት መጽሐፎች ስንት ምዕራፍ ቁጥር  አሏቸው??

*//መልስ*👉1ኛ 👉የነብዩ ኢሳያስ 66 ምዕራፍ አለው።

2ኛ 👉ነብዩ ኤርሚያስ ነው 52 ምዕራፎች አሉት።

3ኛ👉ሕዝቅኤል 48 ምዕራፎች አሉት።

4ኛ👉ነብዩ ዳንኤል ነው 12 ምዕራፎች አሉት።

✍ጥ ተራ(ቁ) 9⃣ኢየሱስ ክርስቶስን አማኑኤል ብለው ይጠሩት የነበሩት እነማን ናቸው??

*// መልስ//* 👉ነብያትና እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ናች።
ትንቢተ ኢሳይያስ

7:14  ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥  ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
አንገትም
8:8  እየጐረፈም ወደ ይሁዳ ይገባል፤ ወንድእያጥለቀለቀም ያልፋል፥ እስከ  ይደርሳል፤ አማኑኤል ሆይ፥ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች።

የማቴዎስ ወንጌል

1:23  እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥  አማኑኤልይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ስሙንምትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣0⃣ቅዱስ ዮሐንስ ለምን አፈወርቅ ተባለ በምንስ ??

*//መልስ//*  ◆◊◆ “አፈወርቅ” የመባሉም ታሪክ እንዲህ ነው:- አንድ ዕለት
ንስጥሮስ የቁስጥንጥንያ ፓትሪያርክ ሆኖ በተሾመበት ዘመን አንዲት
በሴቶች ከሚደርሰው ግዳጅ ( ከወር አበባዋ) ያልፀዳች ሴት ስለ
ቤተክርስቲያንና ስለ ስጋወ ደሙ ፍቅር ስጋወ ደሙን ልትቀበል ወደ
ካህናት ተጠጋች፡፡ በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ እንደ ጥላ ሲሽሽ ታየ፤
ይህንንም የተመለከተው ንስጥሮስ ወደሷ ቀርቦ “እንዲህ መንፈስቅዱስ
የሽሽው ምን ብትሰሪ ነው?” አላት፡፡ እርሷም “ ስለ ቤተክርስቲያን ፍቅር
ከግዳጄ ሳልነፃ ወደ ስጋወ ደሙ በመቅረቤ ነው” አለች፡፡ በዚህ ጊዜ
ንስጥሮስ ተቆጣ በፊት ያጠናው የነበረውን የምንፍቅና ትምህርት
አምጥቶ ለህዝቡ ሁሉ “ እግዚአብሄር እንዲህ መንፈስቅዱስን
ከሚያሳዝን የሴት ማህፀን ወጣ የሚል የተረገመ ይሁን” አለ፡፡ በዚህም
የክርስቶስን ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክነት ሻረ፡፡ ከማርያም የተወለደው
እግዚአብሄር አይደለም በማለት ፍፁም ክህደትን አስተማረ፡፡ ያቺንም
ሴት እርቃኗን ቁልቁል አሰቅሎ ሁሉም ህዝብ እየመጣ በአንቀፀ ስጋዋ
ላይ ምራቁን እንዲተፋ እያዘዘ የማርያምን ወላዲት አምላክነት እንዲሽሩ
አዘዘ፡፡ ክርስቶስንም ከነቢያት አንዱ ነው አለ፡፡ በዚህ ወቅት አንድ ካህን
የነበረ ስሙ ዮሃንስ የሚባል ወደ ሴቷ ቀረበና “እኔስ እግዚአብሄር ወልድ
እንደ ህፃናት ስርአት በማህፀን ተወለደ ብየ አምናለሁ” በማለት የሴቲቷን
አንቀፀ ስጋ የወር አበባ ያላት መሆኗን እንኳን ሳይፀየፍ ሳመ፡፡ በዚህ ጊዜ
በቤተክርስቲያን የነበረች ስእለ ማርያም አንደበት አውጥታ “አፈወርቅ”
ብላ ጠራችው፡፡
ዳግመኛ በከበረ ስዕሏ ተገልፃ " ሰናይ ተናገርከ ዮሐንስ አፈወርቅ
ዮሐንስ ልሳነወርቅ " ብላ አመስግነዋለች፡፡ አንዳንድ ጹሁፎችም
ከሚያስተምረው የትምህርቱ ጣዕም የተነሣ “አፈወርቅ፣ ጥዑመ ልሳን”
ተብሏል የሚሉ አሉ፡፡
12

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣1⃣በአዲስ  ኪዳን 28 ምዕራፍ ያለው መጽሐፍ የትኛው ነው??

*//መልስ//*👉የሐዋርያት ሥራና የማቴዎስ ወንጌል።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣2⃣ተክለ ሃይማኖት ማለት ምን  ነው?? የተክለ ሃይማኖት እናትና አባት ማን እና ማን  ይባላሉ የትውልድ ሃገራቸውስ???

*//መልስ//*👉ተክለ ሃይማኖት ማለት፦ ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው።  አባቱ ጸጋ ዘአብ እናታቸው እግዚእኅረያ ይባላሉ። ሀገራቸው ቡልጋ ጽላልሽ (ዞረሬ) ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣3⃣የኢየሩሳሌምን የመጀመርያውን  መቅደስ የሰራው ማን ነው?? ያፈረሰውስ ማን ነው??

*//መልስ//*👉የርራው ጠቢቡ/ ንጉስ ሰሎሞን። 👉ያፈረሰው ናቡከደነጾር ነው ።

✍ጥ ተራ (ቁ)1⃣1⃣⃣ከ7ቱ የጸሌት ጊዚያት መካከል የ6ሰዓትና የ3ሦስት ሰዓት ጸሎት ምንን አስመልክቶ ነው??

ጸሎት  ”የስድስት ”  የሚባል ሲሆን። በቀትርከፀሀይ ሙቀት የተነሳ ሰውነት ሲዝልሃሳብ (አእምሮ) ሲበተን  ያንን የመናፍስት ጦርለመከላከል በተለይም ጊዘው

አጋንንትስለሚሰለጥኑ-ሄኖክ ቤተመቅደስ ያጠነበት- ይልቁንም ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስክርቶ ዓለምን ለማዳን ሲልበቀራንዮ አደባባይ  ሠዓትስለሆነ ህማማተ መስቀሉን እያሰብንየምንጸልየው ጸሎት ነው።    ሁለተኛዉ ጸሎት ደግሞ ”ዳንኤል የሦስት ሠዓት” ጸሎት የሚባል ሲሆን ይህን  ስንጸልይ፦ የሁሉ እናት ሄዋንየተፈጠረችበት ሠዓት፣ ነብዩ  በምርኮ በሚኖርበት በባቢጸሎትሎን ሳለበእየሩሳሌም አቅጣጫ ያለዉንመስኮቱን ከፍቶ የጸለየበት ሠዓት፣እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያ ከመላአኩ ከቅዱስ ገብርኤል ሠማያዊ ብስራት የሰማችበት ሠዓት፣ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስክርስቶስ በጲላጦስ ፊት የተገረፈበ ሰዓት ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣እያሱ ጽሐይን ያቆመበት ቦታ ማን  ይባላል??

*//መልስ//*👉በግብፅ በገባኦት ሥፍራ  ላይ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣6⃣ቅዱስ ያሬድ ከጸረ-አርያም በወረደ ጊዜ ለመጀመርያ ያዜመው ዜማ ምን ይባላል??

*//መልስ//*ቅዱስ ያሬድ የመጀመረያ ዜማው አራራይ ዜማ ሲሆን ያዜመውም ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ፣ ሃሌ ሉያ ወመንፈስ ቅዱስ  ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይግብር  ግብራ ለደብተራ/ ይህም ማለት አለም ሳይፈጠር ለነበረና አለምን አሳልፎ ለዘላለም ለሚኖር ለአብ ምስጋና ይገባል፣ ለወልድም ምስጋና ይገባል፣ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል፣ ከጽዮን አስቀድሞ ሰማይን ፈጠረ፤ ዳግመኛም ደብተራ ኦሪትን እንዴት አድርጎ መሥራት እንዳለበት ለሙሴ አሳየው ማለት ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣7⃣ደዊይ በስንት ይከፈላል??

*//መልስ//* ደዌይ በአራት ይከፈላል፦

👉1ኛ 👉ደዌይ ዘሐሰት ኢዮብ የደረደበት መከራ (ኢዮብ 2፥10)

2ኛ👉ደዌይ ዘመቅሰፍት ለምሳሌ ሳኦልና ሄሮድስ የደረሰባቸው የሞት መቅዘፍት
ይባላል
3ኛ👉ደዌይ ዘምጽ ጢሞጢዎስ እና ጳውሎስ የደረሰባቸው ህመም ደዌይ ዘምጽ

4ኛ👉ደዌይ ዘኃጢአት ይህ ማለት እነ መጻጉ 38 አመት አልጋላይ የቆዩት ማለት ነው

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣8⃣ቄርሜሎስ ማለት ምን ማለት ነው??

*//መልስ//*ቄርሜሎስ ማለት ፍሬአማ ተራራ ማለት ነው
በሌላ አነጋገር ደግሞ ይቺ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍሬ የምናፈራበት ማለት ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣9⃣አብርሀምና ሎጥ ያላቸውን ዝምድና ግለፅ/ ግለጭ???

*//መልስ//*👉
የአባታችን አብርሀም የወንድሙ የሃራን  ልጅ ነው። ዘፍ 11፥27 ይገኛል።

✍ጥ ተራ (ቁ) 2⃣0⃣በኖህ ዘመን ሠዎች በንፍሮ ውሃ ለመጥፋታቸው ምክንያት የሆነው ምንድነው???

*//መልስ//*👉 በኖህ ዘመን ሠዎች በንፍሮ ውሃ ለመጥፋታቸው ምክንያት የሆነው የእግዚአብሔር ትዛዝ ዘንግተው በኃጢአት ስለረከሱ ነው።
ዘፍ 6፥11

*_ማጠቃለያ መልስ ይህንን ይመስላል_*

*ወስብኃት ለእግዚአብሔር*saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...