2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የምዕራፍ ሁለት(12ኛ) ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የማጣርያ ጥያቄና መልስ

*_✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

_✅የምዕራፍ ሁለት/12ኛ/ ዙር  የማጣርያ የሽልማት የጠቅላላ እውቀት የጥያቄና መልስ ውድድር እንደ ሚከተለው ነው_

*_✍ምድብ አንድ የቅድስት አርሴማ ልጆች👇_*
 *ጥያቄ*

_1⃣➡✍ዲዮቅልጥያኖስ ለጣፆት አንሰግድም ብለው እንቢ ባሉ ክርስቲያኖች ላይ ያወጀው አዋጅ ምን የሚል ነበር ቢያንስ ሦስቱን/3/ጥቀስ/ ጥቀሽ_

*//መልስ//*✍

ሀ. አቢያተ ክርስቲያን እንዲደመሰሱ

ለ. ክርስቲያኖች እርስ በእርሳቸው እንዳይገናኙ

ሐ. ስለ ክርስትና ሃይማኖት የሚናገር መጻፍት ሁሉ እንዲቃጠል

መ. የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነ ሁሉ እንዲወረስ

ሠ. ማንኛውም የሮማ ዜጋ ክርስቲያን ከሆነ ከመንግስት ስራ እንዲወገድ

ረ. ባሮች ክርስትናን ከተቀበሉ ነፃ የመውጣት መብት የላቸውም

ሰ. ክርስቲያን ምንም ሕጋዊ ምክንያት ቢኖራቸውም በማንም ላይ ክስ መመስረትና ስለ መብታቸው መከራከር አይችሉም የሚል ነበር።

_2⃣➡✍ የዓለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ንቅናቄ ማህበር መቼ ተመሠረተ??_

*//መልስ//*✍ በ20/፳ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው።

*_✍ምድብ ሁለት የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች_*👇

   *መልስ*

_1⃣➡✍ቆስጠንጢኖስ ለቤተክርስቲያን ከሰጣቸው መብቶች ውስጥ ቢያንስ ሦስቱን ጥቀስ/ጥቀሽ??_

*//መልስ//*✍
ሀ. ቤተ ክርስቲያን ከግብር ነፃ ናት

ለ. ከመንግስት ገቢ ለቤተክርስቲያን ድርሻ አላት

ሐ. ዕለተ እሁድ/ ሰንበት/ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ውስጥ ሥራ እንዳይሰራባት አወጀ

መ.ከክርስቲያን ወገን በሕይወትንም ሆነ በሞት ንብረቱን ለቤተ ክርስቲያን አወርሳለሁ የሚል ምእመን ካለ ቤተ ክርስቲያን ኑዛዜ የመቀበል፣ ውርስ የመውረስ መብት አላት

ሠ. በክርስቲያኖች መካከል ለሚፈጠሩ አንዳንድ አለመግባባቶች ቢኖሩ ለኤጲስ ቆጶስ የዳኝነት ሥልጣን ሰጥቷል።

_2⃣➡✍የመላው አፍሪካ አብያተ ክርስቲያን  ጽ/ቤት የት ይገኛል ??_

*//መልስ//*  _✍በናይሮቢ ኬንያ ይገኛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዚህ ጊባኤ መሥራችና ቋሚ አባል ናት።_

*_✍ምድብ ሦስት እምነት በስደት የድንግል ማርያም ልጆች_*👇

         *ጥያቄ*

_1⃣➡✍ሐዋርያውያን አበው ከሚባሉት መካከል ሦስቱን ጥቀስ/ጥቀሽ_

*//መልስ//*በርናባስ፣ -ሄርማስ፣ ቀለሚንጦስ ዘሮም፣ ፓሊካርፐስ፣ ፓፒያስና አግናጥዮስ(ምጥው ለአንበሳ) ተጠቃሾች ናቸው።

_2⃣➡✍የአለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት የት ይገኛል??_

*//መልስ//* _✍ በሃንጋሪ ፕራግ በተባለ ከተማ ነው። ጉባኤው በየጊዜው እየተሰበሰበ ቤተ ክርስቲያን ስለ ዓለም ሰላምና ስለ ሰው ልጅ ደህንነት ያላትን አቋም ያሳውቃል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዚህ ጉባኤ ቋሚ አባል ናት።_

*_ምድብ አራት ከተለያዩ ማህበር የመጡ ልጆች_*👇 *ጥያቄ*.

_1⃣➡✍የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ምንጮች ከምንላቸው መካከል ሦስቱን ጥቀስ/ጥቀሽ???_

*//መልስ//* 👉

1ኛ👉የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

2ኛ👉የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት

3ኛ👉በየጊዜው የተደረጉትን የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎችንና ውሳኔዎቻቸው

4ኛ👉የቤተ ክርስቲያን አባቶች የፃፏቸው የታሪክ  መጽሐፍቶች.

5ኛ👉በየጊዜው የሚገኘት የክርስቲያኖች መቃብራት፣ መቅደሶች፣ ሥዕሎች ወ.ዘተ

6ኛ👉መንፈሳውያንም ሆኑ ዓለማውያን ነገስታት በቤተ ክርስቲያን ላይ የደነገጓቸው ልዩ ልዩ ሕግጋት ወ.ዘተ ታሪኮች ናቸው።

2⃣➡✍ቅዱሳን ሐዋርያት እስከ  መጨረሻ በመጽናት ለክርስቶስ ምስክር ለመሆናቸው ዋና ዋና ምክንያቶች ምን ምን ናቸው???_

*//መልስ//*✍

1ኛ👉በአይናቸው አይተውታልና

2ኛ👉በእጃቸው ዳሰውታልና

3ኛ👉ትምህርቱን በጆሮአቸው ሰምተውታልና/ዮሐንስ 1፥2/

4ኛ👉በእርሱ ተልከዋልና/ማቴ 10፥6-4/

5ኛ👉ከትንሣኤው በኋላ አይተውታልና/ዮሐ. 21/

6ኛ👉በስሙ ተአምራት ሲፈጽሙ ኖረዋልና/2ኛ.ቆሮ. 12፥12/

*ውድ ተወዳዳሪዎች ሆይ የጥቄቃው ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ*

*ወስብኃት ለእግዚአብሔር*saramareyama.890@gamail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...