2017 ኖቬምበር 22, ረቡዕ

የምዕራፍ ሁለት(የ16ኛ)ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር


*_በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን አላችሁ? ይህ የምዕራፍ ሁለት/16ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር መረሀ ግብር ነው_
፨፨፨፨♥♥፨፨፨፨፨፨⤵

↪ጥ.ተራ/ቁ/ ➡1⃣አቤሜሌክ ኑሃሚንና ሁለቱ ልጆቿ ወደ ሞአብ ምድር የወረዱት በምን ምክንያት ነው???

*//መልስ//*፡-✍ በረሃብ ምክንያት ነው፡፡ መ.ሩት[1፥1]

↪ ጥ.ተራ/ቁ/➡2⃣ ኑሃሚን ሩትን ሄዳ ቃርሚያ እንድትቃርም የላከቻት ወደ ማን እርሻ ነበር?? የእርሻው ባለቤትስ ለኑሃሚን ምኗ ነው??

*//መልስ//*፡- ✍ወደ ቦኤዝ እርሻ፡፡ ለኑሃሚን የባሏ የአቤሜሌክ ዘመድ ነው፡፡

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡3⃣የነቢዩ የሳሙኤል እናትና አባት ማን ይባላሉ?? ሳሙኤል ማለትስ ምን ማለት ነው??
*///መልስ//*፡- ✍አባቱ ሕልቃና ሲሆን እናቱ ሐና ትባላለች፡፡ ሊቀ ካህኑ ዔሊ፡፡ ሳሙኤል ማለት እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው፡፡ 1ኛ ሳሙ.1÷1-21

↪ጥ.ተራ/ቁ/ ➡4⃣ በነቢዩ ሳሙኤል አማካኝነት ተቀብቶ ለመጀመሪያ ጊዜ የነገሠው የእስራኤል ንጉሥ ማን ይባላል??

*//መልስ//*፡-✍ ንጉሥ ሳኦል ነው፡፡ 1ኛ ሳሙ.10÷1

↪ጥ.ተራ/ቁ/ ➡5⃣እስራኤልዊያን በባሊሎን ከተወረሩ በኋላ ህዝበ እስራኤልን ወደ ባቢሎን ፈለሱ፤ጥቂት እስራኤልዊያን ግን በእስራኤል ቀሩ፤ናቡከደ ነጾር በእስራኤል ለቀሩት ህዝብ ንጉሥ ያደረገው ማንን ይባላል??

*//መልስ//*✍ጎልያስ ነው።

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡6⃣በመጽሐፍ ቅዱስ ፈጣኑ የሕግ ፀሐፊ ዕዝራ ነው፤የነቢዩ ኤርሚያስን ትንቢት ቃል በቃል ይጽፍ የነበረው ሰው ማን ይባላል??

*//መልስ//*፦✍ባሮክ ነው። ኤር[36፥329]

↪ጥ.ተራ/ቁ/ ➡7⃣በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ሙት ያስነሳው ነብይ ማን ይባላል???

*//መልስ//*✍ነቢዩ ኤልያስ ነው።

↪ጥ.ተራ/ቁ/8⃣ጽጌ ማለት ምን ማለት ነው???ማኅሌተ ጽጌ ማለትስ ምን ማለት ነው??

*//መልስ//*✍ጽጌ ማለት የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙ አበባ የፍሬ ምልክት ማለት ነው። ማኅሌተ ጽጌ የሚለው በአንድ ሲጠቃለል የአበባ ምስጋና ማለት ነው።
ይህም ድንግል ማርያም የማኅጸኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየተመሰሉ የሚመሰገኑበት ምስጋና ማለት ነው። ማኅሌተ ጽጌን በግጥም /ቅኔ/ ስንኝ በ5 በ5 የተደረሰ ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰቱን ነው።

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡9⃣እኔ ማነኝ ነገሥታቱ ነቢዩ ኤርሚያስን በውሃ ጉድጎድ ውስጥ ሲጥሉት፤
30 ሰዎችን ጠርቼ በአሮጌ ጭርቅ አድርጌ ነቢዩን ከውሃ ጉድጎድ ውስጥ ፤አወጣሁት
 እኔ ማን ነኝ?


*//መልስ//*✍ኢትዮጵያዊ አቤሜሌክ ነው፤ ሰቆቃወ ኤር[38፥7]

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡1⃣0⃣በምርኩ እያለሁ ራዕይ  የምፈታ ትነቢት የምናገር ከአብይት ነቢያት መካከል የነበርሁ ዕብራዊ ነኝ የስሜ ትርጉም እግዚእብሔር ይፈርዳል ማለት ነው በአናብስት ጉድጓድ ተጥዪ አናብስቶች የእግሬን ትቢያ የላሱ እኔ ማንኝ?????

*//መልስ//*✍ዳንኤል ነው። በባቢሎን እያለ ሕልም ይፈታ የነበረውና በአናብስት ጉድጓድ የተጣለው።
        

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡1⃣1⃣እናቴ በአመፃ ፀነሰችኝ በኃጢአትም ወለደችኝ ብየ ስለ እራሴ ታነሺነት የተናገርሁ ከይሁዳ ዘር የተወለድሁ በልጅነቴ ለንግስና የተመረጥሁ እኔ ማነኝ???
      
*//መልስ//*✍ ነብይ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው።

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡1⃣2⃣እኔ ማነኝ,,?
 ከመቶ ሃያ ቤተሰብ የሆንሁ 
ድምሬ ከ36 ቅዱሳት አንስት ያለሁ 
ልጄ ሐዋርያ ምስሉ ዘአንበሳ ቤቴ ቤተ እግዚአብሔር የነበረ 
እኔ ማነኝ ስሜ ማን ይባላል???

*//መልስ//*✍የሐዋርያው የቅዱስ ማርቆስ እናት ማርያም ናት።

↪ጥ.ተራ/ቁ/ ➡1⃣3⃣ንጉሥ ሰሎሞን ያሰራው ቤተ መቅደስ ፫/3 ክፍሎች ነበሩት፤ ምን ምን ናቸው??


*//መልስ//*✍ቅድስተ ቅዱሳን፣ቅድስትና የውጪዊው አደባባይ ናቸው። 1ኛ ነገሥት [5፥1]


↪ጥ.ተራ/ቁ/➡1⃣4⃣ንጉሥ ዳዊት ቤተ መንግስቱን፣ ልጁ ሰሎሞንም ቤተ መቅደሱን እንዲሰሩ የዝግባ ዛፍ ሰጥቼያቸው ነበር፤ እኔ ማነኝ??

*//መልስ//*✍ኪራም ይባላል። 1ኛ ነገሥት [5፥5]

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡1⃣5⃣ማቁረርያ ማለት ምን ማለት ነው?? ጥቅሙስ ምንድነው???

መቁረር /መቁረሪት/ሰን/ኩስኩስት
• ማቁረርያ፣ ማብረጃ፣ ማቀዝቀዣ /ማንቆርቆሪያ/ ማለት ነው፡፡ /ፍት. ነገ. ፲፫/፡፡ የተቀደሰ የዘይት ቅባት ይቀባ ነበር፡፡ ዘጸ. ፴፥፲፯–፱፣ ዘጸ. ፵፥፴–፴፪፡፡ በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ከመዳብ ከነሐስ ከብርና ከመሳሰሉት ይሠራል፡፡
• ካህኑ በቅዳሴ ጊዜ እጁን ለመታጠብ ይገለገልበታል። ማንቆርቆሪያ ለቅዳሴ ጠበል መያዣ ያገለግላል፡፡ ጌታችንን አይሁድ ሊሰቅሉት አሳልፈው በሰጡት ጊዜ ጲላጦስ “እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ” በማለት የታጠበበትን ያመለክታል፡፡ ማቴ. ፳፯፥፳፯፡፡

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡1⃣6⃣ኤልሳዕ ነቢዩ ኤልያስን ለመጨረሻ ጊዜ ሲለየው ምን ብሎ ነበር የለመነው??

*//መልስ//*✍ኤልሳዕ ኤልያስን መንፈስህ በዕጥፍ እንዲያድርብኝ ብሎ ለመነው። 2ኛ ነገሥት [ 2፡9]


↪ጥ.ተራ/ቁ/➡1⃣7⃣ካህኑ ዕዝራ የሕጉን መጽሐፍ ለእስራኤልላዊያን እያነበበላቸው በጥሞና ያዳምጡ ነበር፤ እስራኤልላዊያን የዕዝራን ንባብና ትርጓሜ ለመስማት ስንት ሰዓት ይቆሙ ነበር??

*//መልስ//*✍፮/6/ ሰዓት ሙሉ ቁመው ይሰሙት ነበር፤ ነህምያ [8፣3]
 
↪ጥ.ተራ /ቁ/➡1⃣8⃣ሰጎን እንቁላሎቿን የምትፈለፍለው በምድን ነው?? የሰጎን እንቁላል ከቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ የሚቀመጥበት/የሚሰካበት ሚስጢርስ ምንድን ነው???

*//መልስ//*✍ሰጎን እንቁላሎቿን የምትፈለፍለው ትኩር ብላ በማየት ነው። 
ሰጎን  እንቁላሏን ጥላ በዓይኗ ትኩር ብላ ካላየች እንቁላሏ ስለሚበላሽ ዓይኗን ከእንቁላሏ አታነሳም። ልዐል እግዚአብሔርም ይችን አለም እንዱሁ ይብጠቃታል። እኛ ከእርሱ ከተለየን እንጠልለን።። ከእመ፣ ከመላእክት ጻድቃን ሰማዕታት ላይ ዓይኑን አያነሳም ዘወትር የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ጉልላቷን እየተመለከተ ይኖራል።

↪ጥ. ተራ/ቁ/➡1⃣9⃣ነቢዩ ኤልያስ  ለደቀመዝሙሩ ለኤልሳዕ ፪/2/ጊዜ መጎናጸፊያውን ሰጥቶት ነበር፤ መቼና መቼ ነበር?? ኤልሳዕስ መጎናጸፊያውን ምን አደረገው??

*//መልስ//*✍ኤልያስ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገኘው ኤልሳዕ 12 ጥንድ በሬዎችን እያጠመደ ነበር፤ ሁለተኛው ደግሞ ለመጨረሻ ጊዜ ኤልያስና ኤልሳዕ ሲለያዩ ማለትም ኤልያስ በሠረገላ ባረገ ጊዜ እነሆ መጎናፀፊያውን ሰጥቶል፤ ኤልሳዕም በመጎናፀፊያው ዮርዳኖስን ከፍሎበታል።

↪ጥ.ተራ/ቁ/➡2⃣0⃣በአፍሪካ ለመጀመርያ ጊዜ የዜማን ምልእክት የተጠቀመው ማን ይባላል???

*//መልስ//*✍ኢትዮጵያዊ የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ነው።

*ወስብኃት ለእግዚአብሔር*


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...