2017 ኖቬምበር 22, ረቡዕ

የምዕራፍ ሁለት(የ15ኛ)ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ ውድድር

https://youtu.be/AAClj-P7IAM

*በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫*

_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ?? ሰላማችሁ ይብዛ!!_

_፨የምዕራፍ ሁለት/15ኛ/ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር_*

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

↪ጥ. ተራ (ቁ)1⃣➡✍ከሚከተሉት ውስጥ የራእይ መጽሐፍ የሆነው የትኛው ነው????

ሀ)፨ፍካሬ ኢየሱስ
ለ)፨ራእይ ሲኖዳ
ሐ)፨መጽሐፈ ሳቤላ
መ)፨ገድለ ፊቅጦር
ሠ)፨ሁሉም የራእይ መጽሐፍቶች ናቸው


*//መልስ//*👇

✍ሠ,፨ ሁሉም የራእይ መጽሐፍቶች ናቸው።

↪ጥ.ተራ(ቁ) 2⃣✍ኤልዛቤል ኤልያስን ልትገድል ታሳድደው ነበር፤ ኤልያስም ከኤልዛቤል ሸሽቶ በ፩/አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ አለና ____ሲል/ ተናገረ???


*//መልስ//*👇
✍ከቀደሙ አባቶች አልበልጥምና ነፍሴን ውሰዳት። 1ኛ ነገሥት [19፥4]

↪ጥ.ተራ (ቁ)3⃣✍ሙሴ በሲና ተራራ 40 ቀንና ሌሊት እንደቆየ ሁሉ አንድ(፩)ነብይም እንዲሁ በኮራት ዋሻ ውስጥ 40 በቀንና ሌሊት ቆይቷል፤ ይህ ነብይ ማን ይባላል???

ሀ)፨ ነቢዩ ኤልያስ

ለ)፨ነቢዩ ኤልሳዕ

ሐ)፨ነቢዩ ዮናስ

መ)፨ መልስ የለም።



*//መልስ//*👇
✍ሀ,፨ ነቢዩ ኤልያስ ነው። 1ኛ ነገሥት [19፥8]

↪ጥ.ተራ.(ቁ)4⃣✍የአካአብ ልጅ አካዝያስ 50 ወታደሮችን ወደ ኤልያስ ላከ፤ ወታደሮችም ኤልያስን በንቀት ና ንጉሡ ይጠራሃል አሉት፤ ከዚያስ ኤልያስን የናቁት ወታደሮች ምን ሆኑ??
*/መልስ//*👇
 ✍ኤልያስን በንቀት የተናገሩት 50 አለቆች እሣት ከሰማይ ወርዳ በላቻቸው፤ ኤልያስን አክብሮ የሰገደው ነቢይም ሕይወቱን አተረፈ። 2ኛ ነገሥት [1፥9]

↪ጥ.ተራ.(ቁ)5⃣✍አበ ብዙሃን አብርሃም ልጁን ይስሐቅን የሰዋበት የሞሪያ ተራራ ሌላ ስሙ ምን ይባላል??
*/መልስ/*👇

የጽዮን ተራራ ነው። ጽዮን ማለት አንባ መጠጊያ ማለት ነው፤ 2ኛ ዜና [3፥1]

↪ጥ.ተራ(ቁ)6⃣✍ጣዖት የማምለክና ከንቱነቱ የገዛ ልጁን መሰዋዕት አድርጎ ማቅረብ ነው፤ የራሳቸውን ልጅ ለጣዖት መስዋዕት አድርገው ካቀረቡት ሰዎች ውስጥ ፫ቱን ጥቀስ/ሽ/
*//መልስ//*👇

የሕዝቅያስ አባት ንጉሥ አካዝ፣ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴና መስፍኑ ዮፍታሔ ልጃቸውን ለጣዖት መሰዋዕት አድርገዋል። 2ኛ ዜና [28፥3] 2ኛ ነገሥት [21፥6]

↪ጥ.ተራ.(ቁ) 7⃣✍በቅደም  ተከተል ከብሉይ ኪዳን..እስከ ሐዲስ ኪዳን ቤተ መቅደስን የሰሩት ፫ቱ ነገሥታት እነማን ናቸው??

*/መልስ/*👇

ንጉስ ሰሎሞን፣ዘሩባቤልና ንጉስ ሄሮድስ ናቸው።

↪ጥ.ተራ.(ቁ)8⃣✍ሰሎሞን ያሰራው ቤተ መቅደስ በባቢሎናዊያን ከፈረሰ በኋላ ከእንደገና እንዲሰራ ያደረገው ሰው ማን ይባላል???

ሀ)፨ ዘሩባቤል

ለ)፨ ሄሮድስ

ሐ)፨  መልስ የለም

መ)፨ ሀ&ለ መልስ ናቸው

*//መልስ//*👇
✍መ,፨ ዘሩባቤል ነው። ዘሩባቤል ማለት የባቢሎን ልጆች ማለት ሲሆን ይህም ዘሩባቤል በባቢሎን ስለተወለደ የተሰጠው ስም ነው። ጌታችንም የመጣው ከዘሩባቤል የዘር ሐረግ ነው። ማቴ [1፥12]

↪ጥ.ተራ(ቁ) 9⃣✍ሐማ የተባለው ሰው በአይሁዳውያን ላይ የዘር ማጥፋት አዋጅ ባስነገረ ጊዜ በጾምና ጸሎት ይህንን አዋጅ ያስቀረችው ታላቅ ሴት ማን ትባላለች??

ሀ)፨ ሐና

ለ)፨አስቴር

ሐ)፨ ሩት

መ)፨ ሁሉም
*//መልስ//*👇

✍ለ,፨የመርዶክዮስ የአጎቱ ልጅ የሆነችው የመጀመርያ ስሟ ሀዳሳ ይባል የነበረ አስቴር ናት።.! አስቴር ማለት፦ኮከብ ማለት ነው። በአሁኑ ወቅት አይሁድ ታሪክ ለማስታወስ "  የአስቴር ጾም"  እያሉ ይጾሙታል።

↪ጥ.ተራ.(ቁ)1⃣0⃣✍የእመቤታችን የስደት ጊዜ ፫/3 ዓመት ከ፮/6 ወር መሆኑን የተገለጸበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው???

ሀ.፨ ማቴ. ፪፥፲፫

ለ.፨ ኢ.ሳ. ፰፥፲፬

ሐ.፨ ራዕ.፲፪፥፲፬

መ.፨ ሉቃ.፩፥፵-፰

*//መልስ//*👇
✍ሀ,፨ ማቴ 2፥13


↪ጥ.ተራ(ቁ) 1⃣1⃣✍በቅዱስ መጽሐፋችን በሴት ስም ከተሰየሙት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ሦስቱን ጥቀስ/ሽ??

*//መልስ//*👇
✍መጽሐፈ አስቴር፣መጽሐፈ ሩት፣ መጽሐፈ ዮዲት፣ መጽሐፈ ሶስና የመሳሰሉት ናቸው።

↪ጥ.ተራ(ቁ) 1⃣2⃣በቤተ ክርስትያናችን በዘመነ ጽጌ ማኅሌት የሚደረሰው ድርሰት ምንድን ነው? ማን ደረሰው? ቁጥሩስ ስንት ነው?

*//መልስ//*👇

✍ማኅሌተ ጽጌ ነው። ድርሰቱን የደረሰው አባ ጽጌ ድንግል ሲሆን  ትውልዱም በስሜን ሽዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ነው።የደረሱት የቁጥር ብዛት 150 ነው።

↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣3⃣✍በእጀ ጠባቤም ላይም እጣ ተጣጣሉ መዝ[22፡18]
ይህ ትንቢት የተፈጸመው መቼ ነበር??

*//መልስ//*👇

✍አይሁድ ጌታችንን ከመስቀላቸው በፊት ነው፤ ጌታችን በመዋዕለ ሥጋዌው ከልጅነቱ ጀምሮ የሚለብሳት ከራሱ እስከ እግሩ ወጥ የሆነች ልብስ ነበረች፤ እርሱ በሥጋ ሲያድግ ልብሱም በተአምር ትረዝም ነበር።ዳዊት ትንቢት  የተነበየላትና አይሁድ እጣ የተጣጣሉት በዚህች ልብስ ላይ ነው።

↪ጥ.ተራ (ቁ)1⃣4⃣✍የጻድቃን መታሰቢያው እስከመቼ ነው?? ጥቅሙስ ምንድነድ??

*//መልስ//*👇

✍አባት ዝክረ ቅዱሳን ይሄሉ ለዓለም" የጻድቃን መታሰቢያ ለዘለዓለም ነው"  ሲል ልጅ ደግሞ "በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው፤ የጻድቃን መታሰቢያ ለበረከት ነው" ይላል። መ.ዝ[111፥6] ምሳ[10፥7]

↪ጥ.ተራ.(ቁ)1⃣5⃣ሄሮድስ  ያስፈጃቸው ሕፃናት ቁጥር ስንት ናቸው?? ሕፃናቱ እንዲሰበሰቡ ያደረገውስ ምን በምን ዘዴ ነው??

*//መልስ//*👇

✍ብዛታቸው 144,000 ሲሆኑ ምግብና ልብስ እሰጣችኋለሁ ብሎ ነው እንዲሰበሰቡ አድርጓል።

↪ጥ.ተራ(ቁ)1⃣6⃣✍ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኔታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ ሆኖ እንደሚወለድ የተነበየው ነብይ ማነው??

*//መልስ//*👇

✍ነቢዩ ኢሳይያስ ሲሆን ትንቢቱም እንዲ ይላል፦ በጨለማ የሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሀን ወጣለት፤ ህፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰቶናልና ስሙም ድንቅ፤  መካር፣ "ኃያል አምላክ" የሠላም አለቃ የዘላለም አባት ይባላን፤ ኢሳይያስ[9፥6]

↪ጥ. ተራ(ቁ)1⃣7⃣✍እስራኤልን ሊወሩ የመጡ ሶርያዊያን በእስራኤል  ንጉስ እጅ ወደቁ ፤ንጉሡም ልግደላቸውን?. ብሎ ኤልሳዕን ጠየቀው? ኤልሳዕ ምን ብሎ መለሰለት..?

*//መልስ//*👇

✍በሰይፍና በቀስት የማረካቸውን ልትገድል ይገባልን? የሚበሉትና የሚጠጡትን አቅርብላቸውና ወደ ጌታቸው ይሂዱ አለው። 2ኛ ነገሥት [6፥22]

↪ጥ.ተራ(ቁ)1⃣8⃣✍በአንድ ወቅት ንጉሥ ሕዝቅያስ ትሞታለህና ቤትህን አዘጋጅ! የሚል ቃል ሰማ፤ ንጉሥ ሕዝቅያስ ምን፦አደረገ?? ይህን ቃል ወደ ንጉሱ ያመጣለትስ ማን ነበር???
*//መልስ//*👇

✍ሕዝቅያስ ፊቱን ወደ ቤተ መቅደስ አዙሮ ጸለዬ፤ 15 አመትም ተጨመረለት። ይህን መልዕክት ያመጣለት ነቢዩ ኢሳይያስ ነበር። 2ኛ ነገሥት [20፥1]

↪ጥ.ተራ.(ቁ)1⃣9⃣✍በአንድ ወቅት ንጉሥ ኢዮርብአም በእግዚአብሔር ሰው ላይ "የያዙት" ብሎ እጁን አመለከተ፤ .....ይህን ጊዜ የኢዮርብአም እጅ  ምን ሆነ.. ከዚያስ ምን ብሎ ለመነ???.........

*//መልስ//*👇👇

ኢዮርብአም የዘረጋት እጁ ደርቃ ቀረች፤  ለነቢዩ እግዚአብሔርን ለምንልኝ አለው፤ ተፈወሰ። 1ኛ.ነገሥት[13፥4]

↪ጥ.ተራ (ቁ) 2⃣0⃣✍ የዚህን ዜማ ግጥም ትርጉም 👉ማርያም ጎየይኪ እምገጸ ሄሮድስ/፪/
ለአርእዮ/፬/ ተአምረ ግፍዕኪ
*//መልስ//*👇

ትርጉም፡- ማርያም ሆይ የግፍሽን ተአምር ለማሳየት
ከሄሮድስ ፊት ሸሸሽ ፡፡

_ወስብኃት ለእግዚአብሔር_saramareyama.890gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...