2017 ኖቬምበር 21, ማክሰኞ

የምዕራፍ ሁለት(የ14ኛ) ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

https://youtu.be/jvZkoEIE4Zs

*_በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

_ፍፁም የእግዚአብሔር ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን!_

*ይህ የ14ኛ ዙር/የምዕራፍ ሁለት👉 የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ መልስ👇 ።*
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨


✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 1⃣ ↪ በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ በሰማያትም  ላሉት እርቅን ሰላምን አደረገላቸው። የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ  ቅዱስ ክፍል ይገኛል ምዕራፍና ቁጥሩስ???

*//መልስ///*👉ወደ ቆላስያስ  [1፥18]

✍ጥያቄ ተራ(ቁ)2⃣↪መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በስራው ምክንያት የተሰጡት ስሞች ስንት ናቸው ማን ማን??


*//መልስ//*👇👇

1ኛ👉ነብይ
2ኛ👉ካህን
3ኛ👉መጥምቅ
4ኛ👉መምህር
5ኛ👉ጻዲቅ
6ኛ👉ሰማዕት
7ኛ👉ሐዋርያ

*የሚሉ ናቸው*👆🏻

✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 3⃣↪ሰባቱ ዓውዶች  የሚባሉት ምን ምን ናቸው???
*//መልስ//*👇

/ሰባቱ ዓውዶች የሚባሉት፦👉 👉ዓውደ እለት በየሰባቱ ቀን የሚመላለሰው

👉ዓውደ ወርኅ በ30 ቀኑ የሚመላለሰው

👉ዓውደ ዓመት በጨረቃ 354 ቀን በፀሐይ በ365 ቀን እንዲሁም በከዋክብት በ364 ቀን የሚመላለስ

👉ዓውደ አበቅቴ በ19 ዓመቱ በ/19 ዓመት አንድ ጊዜ ፀሐይና ጨርቃ ጉዞአቸውን በጋራ የሚጀምሩበት/ ተራክቦየሚያደርጉበት/

👉ዓውደ ጳጉሜ በዐራት ዓመት የሚመላለስ /በዐራት ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜ 6/የሚሆንበት እንዲሁም በ600ዓመት አንድ ጊዜ ጳጉሜ ሰባት ትሆናለች።

👉ዓውደ ማኅተም በ76 ዓመት የሚመላለስ ሲሆን በ76 ዓመት በወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ አበቅቴው ደግሞ በ18 ይሆናል።

👉ዓውደ ቀመር ይህ በ5 ዓመት የሚመላለስ ሥርዓት ነው፤ በዚህ ዓውድ ሁሉ ነገሮች ይገጣጠማሉ።
ኢትዮጵያ በእነዚህ ዐውዶች ዘመን ትቆጥራለች።


✍ጥያቄ ተራ (ቁ) 4⃣↪ከመስከረም 17-25 ያለው ሳምንት ምን በመባል ይታወቃል??


*//መልስ//*👇
ከሰኔ 26-እስከ መስከረም 25 ዘመነ ክረምት እየተባለ የሚጠራ ሲሆን እንዲሁም ከመስከረም 17-25 ስለ ነገረ መስቀሉ የሚነገርበት/የሚሰበክበት፣ የሚ ዘመርበት በመሆኑ ዘመነ መስቀል እየተባለ ይጠራል።

✍ጥያቄ ተራ(ቁ)5⃣↪መስፍን ኢያሱ በሌውያን ካህናትን ታቦተ ጽዮንን አስከትሎ የአንዲት ከተማን ግንብ 7/፯ ጊዜ ሲዞር ያቺ ከተማ በ7/፯ኛው ፈረሰች፣ ይቺ ከተማ ማን ትባላለች??የከተማዋ ስም ትርጉሙስ ምን ማለት ነው??

*//መልስ//*👇
/ኢያሪኮ ስትሆን የኢያሪኮ ሰዎች  ስለሚያመልኩ። ከተማቸውን ኢያሪኮ ብለው ጠሯት፣:ኢያሪኮ ማለት፦ የጨረቃ ከተማ ማለት ጨረቃነው ።

✍ጥያቄ ተራ(ቁ)6⃣↪ የመስፍን ኢያሱ የመጀመሪያ ስሙ ማን ይባላል?? ኢያሱ ብሎ ስም ያወጣለት ማን ነው?? ኢያሱ ማለትስ ምን ማለት ነው???

*//መልስ//*👇

/ የመጀመሪያ ስሙ አውሴ ሲሆን ኢያሱ ብሎ ስም ያወጣለት ነብዩ ሙሴ ነበር፤ ሙሴ ማለት የተወለደ ማለት ሲሆን ኢያሱ ማለት ደግሞ መድኅኒት ማለት ነው። (ዘኀልቁ 13፥16)

✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 7⃣↪መጽሐፍ ቅዱስ 6/፮ መሳፍንት አሉ፤ እነርሱም፦ጎቶንያል፣ናፆድ፣ጌዲዮ፣ ዮፍታሔና ሶምሶም ሲሆኑ ብቸኘዋ ሴት መስፍን ማን ትባላለች????

*//መልስ//👇*

/ዲቦራ ናት፤ ዲቦራ ማለት ንብ ማለት ነው።.


✍ጥያቄ ተራ (ቁ) 8⃣↪እኔ ማን ነኝ ? የመጀመርያ ስሜ አውሴ ነው፤ በወጣትነቴ የግብጽን ባርነት የቀመስኩ፣  የኤርትራ ባሕር ሲከፍል በዓይኔ ያየሁ፣ከካሌብ ጋር ምድረ ርስትን የሰለልኩ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ የሙሴ  አገልጋይ የነበርኩ እኔ ማን ነኝ???

*//መልስ//*👇

ኢያሱ ነኝ/ነው።


✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 9⃣↪ምድረ ርስት ከንዓንን የወረሱት ሁለቱ ሰዎች ማንና ማን ናቸው??

*//መልስ//*👇

//ኢያሱና ካሌብ//

✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 1⃣0⃣↪መስቀል ማለት የቃሉ ትርጉም ምን ማለት ነው???

*//መልስ//*👇

/መስቀል ማለት ሰቀለ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም " የተመሳቀለ መስቀለኛ ማለት ነው።


✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 1⃣1⃣↪ቅድስት ዕሌኒ የጌታችን መስቀል ለማውጣት ወደ ኢየሩሳሌም በስንት አመተ ምህርት ነው የሄደችው?? ልጇ ቆስጠንጢኖስ አምኖ የተጠመቀው በስንት አመተ ምህረት ነው???

*//መልስ//*👇

ቅድስት ዕሌኒ ወደ የጌታችን መስቀል ለማውጣት በ327 የሄደች ሲሆን ልጇ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ አምኖ የተጠመቀው በ352 ዓ.መ ነው።

✍ጥያቄ ተራ (ቁ) 1⃣2⃣↪እነ ኢያሱ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ዮርዳኖስን ሲሻገሩ ወንዙ ሞልቶ ነበር፤  ይህም የሆነው ከአንድ ተራራ ላይ ከሚቀልጠው የበረዶ ግግር ምክንያት ሲሆን እመቤታችንም ስትወለድ ይህ ተራራ እንደ ችቦ ከሩቅ ያበራ ነበር፤ ይህ ተራራ ስሙ ማን ይባላል???

*//መልስ//*👇
የሊባኖስ ራስ የአርሞንኤም ተራራ ነው።


✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 1⃣3⃣↪ የሳሙኤል እናት ሐና የወለደችው 6 ልጆችን ብቻ ነው፤ ነገር ግን 1ኛ ሳሙኤል [2፥5]ላይ መካኒቱ 7 ወለደች ብላ የዘመረችው ለምን ይሆን???

*//መልስ//*👇

አንድም ታላቁ ሳሙኤል እንደ ሁለት ልጅ ስለሚቆጠር ነበር ሐና 6 ወልዳ ሳለ መካኒቱ 7 ወለደች ብላ 1ኛ ሳሙ.[ 2፡21] የዘምመረችው።

አንድም በቤተ ክርስቲያን 7 ቁጥር ሙሉ ቁጥር ስለሆነ ሐናም እግዚአብሔር ፍፁም ሙሉ ነገርን ሰጠኝ ስትል መካኒቷ ሐና ሰባት ወለደች አለች።

✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 1⃣4⃣↪ልብ አምላክ ቅዱስ ዳዊት 150 መዝሙራትን ሲዘምር ልጁ ሰሎሞን ስንት ምሳሎዎችን ተናገረ??

*//መልስ//*👇

3ሦስት ሽ ምሳሌዎችን ተናገረ። [1ኛ ነገስት 4፥32]


✍ጥያቄ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣↪የሙሴ ተከታይ ኢያሱ ሲሆን የኤልያስ ተከታይ ማን ነው?? የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር  ጢሞቴዎስ ከሆነ የኤልሳዕ ደቀ መዝሙር ማነው??


*//መልስ//*👇

  የኤልያስ ተከታይ  ኤልሳዕ ሲሆን የኤልሳዕ ደቀ መዝሙር  ግያዝ ነው።


✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 1⃣6⃣↪ንጉሥ አክአብ የናቡቴብን ርስት እጅግ ተመኝቶ ሲጠይቀው ናቡቴ ምን ብሎ መለሰለት??

*//መልስ//*👇

የአባቶችን ርስት አልሰጥም አለው፤1ኛ ነገስት.[21፥3.


✍ጥያቄ ተራ(ቁ)1⃣7⃣↪ቅዱስ ዳዊት የመረጣቸው 3/፫ቱ ሌዋዊያን የመዘምራን አለቃ እነማን ናቸው??
*//መልስ//*👇

አሳፍ፣ኤማንና ኤዶታም ናቸው። [1ኛ.ዜና.25፡1]

✍ጥያቄ ተራ(ቁ)1⃣8⃣↪መናፍቃን ቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ብቻ ነው መጸለይ ያለብን ይላሉ፤ የኢዮብ ወዳጆች በበደሉ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ነበር ያላቸው???

*//መልስ//*👇

እንደ በደላችሁ እንደ አይከፍላችሁ ወደ ባሪያዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እርሱ ስለእናንተ ይጸልያል፤  እኔም ጸሎቱን እሰማለሁ።
.መናፍቃን ቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ብቻ ነው የምንፀልየው ሲሉ እግዚአብሔር ግን እንደ በደላችሁ እንዳይከፍላችሁ ወደ ቅዱሳን ሂዱ፤ እነሱ ይጸልያሉ፤ እኔም ጸሎታቸውን እሰማለሁ ይላል። ኢዮብ[42፡8]



✍ጥያቄ ተራ (ቁ)1⃣9⃣↪ ሰው እውቀትን ሲጨምር ኃዘንን ይጨምራል ያለው ንጉሥ ማን ነው???

*//መልስ//*👇

ጠቢቡ ሰሎሞን ነው፤ መጽሐፈ መክብብ[1፡18]


✍ጥያቄ ተራ(ቁ) 2⃣0⃣↪3/፫አመት በኢትዮጵያ በእግሩ የሄደው ነብይ ማን ይባላል??

*//መልስ//* ነብዩ ኢሳይያስ ነው። ኢሳ[20፥3] ላይ ይገኛል።

ወስብኃት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

2 አስተያየቶች:

  1. ቃለ ህይወት ያያሰማልን እህታችን ሳራ ፀጋውን ያብዛልሽ በቤቱ ያፅናሽ አሜን

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  2. ቃለ ህይዎት ያሰማልን አሪፍ ነው።

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...