2018 ኦክቶበር 27, ቅዳሜ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን!

↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️

1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር
  ሀ. ድጓ፣ጾመ-ድጓ እና መዋስዕት
  ለ. ቅኔ፣አቋቋም እና ዕጣነ-
  ሐ. ዋዜማ፣ስብሐተ-ነግህ እና አርያም
  መ.ግእዝ፣ዕዝል እና አራራይ


✅መ

2⃣ በሥርዓተ ክርስትና ወቅት፡በተጠማቂው ተገብቶ ጸሎተ ሃይማኖትን የሚያደርሰው ማን ነው?
  ሀ. ወላጅ አባት ወይም እናት
  ለ. ክርስትና አባት ወይም እናት
 ሐ. መምህረ-ንስሐ
 መ. በክርስትናው ጸሎት የተሰበሰበው ምዕመን

✅ለ

3⃣ «ክርስቶስ ተንሥአ እምሙታን/እሙታን» ለሚለው ሰላምታ ምላሽ የሚሆነው፡
  ሀ. አሠሮ ለሰይጣን
  ለ. በአማን
  ሐ. በዐብይ ኃይል ወሥልጣን
  መ. አግአዞ ለአዳም

✅ሐ

4⃣ የዐብይ ጾም የመጀመሪያው እሁድ ምን በመባል ይታወቃል?
  ሀ.ቅድስት
  ለ. ብርሃን
  ሐ. ዘወረደ
  መ.ምኩራብ

✅ሐ

5⃣ በቤተክርስቲያን ሻማ ምሳሌነቱ ምንድን ነው?
  ሀ. ለመንግስተ-ሰማያት ብርሃን
  ለ. ለእግዚአብሔር ብርሃን መሆን
  ሐ. ለቅዱሳን ሕይወት
  መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
.
✅መ

6⃣ ኢየሱስ የሚለው ስም ትርጓሜው ምንድን ነው?
  ሀ. መሲሕ
  ለ. ንጉሥ
  ሐ.ጌታ
  መ. መድኃኒት
.
✅መ

7⃣ ዐራቱ ወንጌላውያን ከአርባዕቱ (ዐራቱ) እንስሳት በተጨማሪ በዐራቱ ወቅቶች ይመሰላሉ።ከነዚህ መካከል በበጋ ወቅት የሚመሰለው ማን ነው?
  ሀ. ቅዱስ ማቴዎስ
  ለ. ቅዱስ ማርቆስ
  ሐ. ቅዱስ ሉቃስ
  መ. ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሀ መቅድመ ወንጌል

8⃣ ከሚከተሉት ውስጥ የመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ያልሆነው የትኛው ነው?
  ሀ. ርግብ
  ለ. ነፋስ
  ሐ. እሳት
  መ. በግ

✅መ

9⃣ ወንጌል የሚለው ቃል ሲተረጎም፡
  ሀ. ቃለ እግዚአብሔር ማለት ነው።
  ለ. የክርስቶስ ሕይወት ማለት ነው።
  ሐ. ግብረ ሐዋርያት ማለት ነው።
  መ. የምሥራች/መልካም ዜና ማለት ነው።

✅መ

1⃣0⃣ ዕጣን በቤተክርስቲያን ያለው ምሳሌነት፡
  ሀ. የቅዱሳን ጸሎት መዓዛ ነው
  ለ. የእመቤታችን ምሳሌ ነው
  ሐ. የተስፋ መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው
  መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ።

✅መ

1⃣1⃣ ኦርቶዶክሳዊ የቤተክርስቲያን ሕንፃ አሠራር የትኛውን ቅርጽ ሊይዝ ይችላል?
  ሀ. ክብ
  ለ. ሰቀላማ/መርከብ ቅርጽ
  ሐ. መስቀል
  መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ።

✅መ

1⃣2⃣ በግእዝ «መምህር« ካለ በዕብራይስጥ ----------------- ይላል።
  ሀ. ቦአኔርጌስ
  ለ. ረቢ
  ሐ. ጣቢታ
  መ. ኤፍታህ

✅ለ

1⃣3⃣ በቅዳሴ ሰዓት ንፍቅ ዲያቆኑ የቅዱስ ጳውሎስን መልዕክት ሲያነብ ፊቱን ወደየት አዙሮ ነው?
  ሀ. ወደ ምሥራቅ
  ለ. ወደ ምዕራብ
  ሐ. ወደ ሰሜን
  መ. ወደ ደቡብ

✅ሐ

1⃣4⃣ ቅዳሴውን ሲጀምር«ልቤ መልካም ነገር አፈለቀ»በማለት ከዳዊት መዝሙር የጠቀሰው ማን ነው?
  ሀ. ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ
  ለ. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
  ሐ. ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
  መ. አባ ሕርያቆስ

✅መ

1⃣5⃣ ጸሎተ ፍትሐት ሰው በሞተ በሦስተኛው ቀን የሚደረገው ለምንድን ነው?
  ሀ. የእግዚአብሔርን ሦስትነት ለማጠየቅ
  ለ. መጽሐፍ «ነገር በሦስት ይጸናል» ስለሚል
  ሐ. ክርስቶስ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ መነሳቱን ለማጠየቅ
  መ. መልስ የለም

✅ሐ

1⃣6⃣ ርዕሰ መነኮሳት በመባል የሚታወቀው አባት ማን ነው?
  ሀ. አባ መቃርዮስ
  ለ. አባ ጳውሊ
  ሐ. አባ እንጦንስ
  መ. አባ ጳኩሚስ

✅ሐ

1⃣7⃣ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታት ድርሰቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ምን በማለት ጠርቷታል?
  ሀ. የመላዕክት እኅት
  ለ. የሰማዕታት እናት
  ሐ. የጻድቃን እመቤት
  መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣8⃣ የቤተክርስቲያን ዶግማ ስንል፡
  ሀ. የሚሻሻል የሚለወጥ ሥርዓት ማለት ነው።
  ለ. የማይሻሻል የማይለወጥ ትምህርተ ሃይማኖት ማለታችን ነው።
  ሐ. ቀኖና ማለታችን ነው።
  መ. ትውፊት ማለታችን ነው።

✅ለ

1⃣9⃣ ሰብአ ሰገል ( የጥበብ ሰዎች) ለጌታችን ካመጧቸው ስጦታዎች መካከል በፍቅር የሚመሰል የትኛው ነው?
  ሀ. ወርቅ
  ለ. ዕጣን
  ሐ. ከርቤ
  መ. መልስ የለም

✅ሐ

2⃣0⃣ በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት ካህኑ የማቴዎስን ወንጌል ካነበበ በኋላ «ሰማይ እና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም አለ ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ» ይላል።የማርቆስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ የሚባለው የቱ ነው?
  ሀ. ኦሪት እና ነብያት ከተናገሩት አንዲት ከምታልፍ ሰማይ እና ምድር ቢያልፉ ይቀላል
  ለ. ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ
  ሐ. በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይወት አለው
  መ. መልስ አልተሰጠም

✅ለ

🖊ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል💐
ቻናላችን ለመቀላቀል
saramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ 5 የ45ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

Watch "የምዕራፍ አምስት (፭) የ45ኛዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃል ጥያቄና መልስ ውድድርhttps://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8V" on YouTube
https://youtu.be/Lrf4stF7NSE

https://youtu.be/Lrf4stF7NSE
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን!

↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 45ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️

1⃣.መጠመቅ ያለብን በማን ስም ነው?
ሀ/ በኢየሱስ
ለ/ በእግዚአብሔር አብ ስም
ሐ/ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መ/ በአብ ፡በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም

✅መ

2⃣.ከጌታችን መድኃኂታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ልደት አስቀድሞ የሚመጡ ሦስት እሑዶች ስያሜያቸው ምንድን ነው?
ሀ/  ስብከት ፡ኒቆዲሞስ ደብረ-ዘይት
ለ/  ቅድስት፡ ዘወረደ፡ መፃጉዕ
ሐ/ ስብከት፡ ብርሃን ፡ኖላዊ
መ/ ምኩራብ ፡ገብርሔር፡ ብርሃን

✅ሐ

3⃣.የሰው ልጅ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ መፈጠሩ ግልጽ ሲሆን ዕድሜውም እንዲሁ በዐራት ደረጃዎች የተከፈለ ነው።በዚህም መሠረት ከሃያ እስከ ዐርባ ዓመት ያለው ጌዜ የትኛውን ባሕርይ ያመለክታል?
ሀ/ የነፋስ
ለ/ የእሳት
ሐ/ የውኃ
መ/ የመሬት

✅ለ

4⃣.ስለስንበተ-ክርስቲያንና ስለ ዕለተ ምጽአት የሚናገረው ቅዳሴ?
ሀ/ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
ለ/ ቅዳሴ ማርያም
ሐ/ ቅዳሴ አትናቴዎስ
መ/ ቅዳሴ ባስልዮስ

✅ሐ

5⃣.ቅዱስ ቅባት በመቀባት ከሥጋም ከነፍስም ደዌ የምንድንብት ምሥጢር የትኛው ነው?
ሀ/ ምሥጢረ ሜሮን
ለ/ ምሥጢረ ቀንዲል
ሐ/ ምሥጢረ ተክሊል
መ/ ምሥጢረ ቁርባን

✅ለ

6⃣.የሥርዓተ ቅዳሴ ዋነኛው ዓላማ፣
ሀ/ በኅብረት መጸለይ
ለ/ ወንጌል  መማር
ሐ/ ቅዱስ ቁርባን
መ/ ሁሉም

✅መ

7⃣.በላሕም/ላም/ የሚመስለው ወንጌላዊ ማነው?
ሀ/ ቅዱስ ማቴዎስ
ለ/ ቅዱስ ማርቆስ
ሐ/ ቅዱስ ሉቃስ
መ/ ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሐ

8⃣.የቤተክርስቲያን የውስጥ ክፍሎች ምን ምን ተብለው ይታወቃሉ?
ሀ/መቅደስ ፡ቅደስትና ቅኔ ማኅሌት
ለ/ ደጀ ስላም ፡ቤተልሔምና መቅደስ
ሐ/ ቅድስተ- ቅዱሳን መቅደስና ቤተልሔም
መ/ መልሱ አልተስጠም

✅ሀ

9⃣.ከሚከተሉት በቅዳሴ ሰዓት የማይነበብ ምንባብ የትኛው ነው?
ሀ/ ወንጌል
ለ/ ትንቢተ ኢሳይያስ
ሐ/ ከሐዋርያት ሥራ
መ/ ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክታት

✅ለ

🔟.ምሥጢረ ቁርባን
ሀ/ ኀብስቱ ወደ ሥጋ መለኮት ወይኑ ወደ ደመ መለኮት የሚለወጥበት ምሥጢር
ለ/ ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የሚመደብ ነው
ሐ/ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሊሳተፍበት የሚገባ ምጢር ነው
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣1⃣.ከሚከተሉት በዕለቱ የተጋደሉትን ቅዱሳን ታረክ የምናነብበት መጽሐፍ የትኛው ነው?
ሀ/ መጽሐፍ ስንክሣር
ለ/ ገድለ ሐዋርያት
ሐ/ ድርሳነ ስንበት
መ/ ዜና አበው

✅ሀ

1⃣2⃣.በሥርዓተ ቅዳሴ ሊደረግ የማይገባው ድርጊት የትኛው ነው?
ሀ/ የግል ጸሎት መጸለይ
ለ/ ወሬ ማውራት
ሐ/ መሳቅ
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

✅መ

1⃣3⃣.ከሚከተሉት ስለ ንስሐ ትክክል እና ገላጭ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ/ ኃጢታትን ይቅር የሚልና የሚያስተስርይ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ለ/ የሠሩትን ኃጢያት ማመን ለመምህረ- ንስሐ መንገር እና ዳግም ላለመስራት መወስን ፡ንስሐ መግባትነው።
ሐ/ ንስሐ መግባት ያለብን በየጊዜው  ነው
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣4⃣.ከትንሣኤ ጀምሮ ለሃምሳ ቀናት የሚቀደስው የትኛው ቅዳሴ ነው?
ሀ/ ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
ለ/ ቅዳሴ ሐዋርያት
ሐ/ ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
መ/ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ

✅መ

1⃣5⃣.ምሥጢረ ጥምቀትን የሚፈጽመው ማነው?
ሀ/ ዲያቆን
ለ/ ቄስ
ሐ/ ጳጳስ
መ/ ለእናሐ መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣6⃣.ከዐቢይ ጾም እሑድ ስያሜዎች የማይመደበው የትኛው ነው?
ሀ/ ዘወረደ
ለ/ ምኲራብ
ሐ/ ኖላዊ
መ/ ገብርሔር

✅ሐ.

1⃣7⃣.አንቀጸ አባግዕ/የበጎች አንቀጽ/በመባል የሚታውቀው ክፍል የትኛው ነው?
ሀ/ ማቴ.5
ለ/ ማር.1
ሐ/ ሉቃ.18
መ/ ዮሐ.10

✅መ

1⃣8⃣.ከአሥራ ዐራቱ ቅዳሴያት ጸሐፊዎች መካክል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለ/ ቅዱስ ባስልዮስ
ሐ/ ቅዱስ ኤፍሬም
መ/ ቅዱስ ጎርጎርዮስ

✅ሐ

1⃣9⃣.ምሥጢረ ክህነትን የሚፈጽመው ማን ነው?
ሀ/ ዲያቆን
ለ/ ቄስ
ሐ/ ጳጳስ
መ/ ማንኛውም ክርስቲያን

✅ሐ

2⃣0⃣.ዲያቆኑ ክቡር ደሙን ለምዕመናን የሚያቀብልበት ንዋየ-ቅዱስ ምን ተብሎ ይጠራል?
ሀ/ ጻሕል
ለ/ አጎበር
ሐ/ እርፈ መስቀል
መ/ ማኀፈድ

✅ሐ

ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላለ ከስተቴ እረሙኝ
saramareyama.890@gmail.com

2018 ኦክቶበር 2, ማክሰኞ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ44ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

https://youtu.be/ceehMHSXFek

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
@Teyakaenamels
የ2011 ዓ.ም የምዕራፍ አምስት(፭) የ44ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ
💛💛💛💛💛💛💛
@ምንጭ 👉420 ጥያቄዎችthanks  እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
💛💛💛💛💛💛💛

1⃣✏ከሚከተሉት  የእመቤታችን ምሳሌ የሆነው የትኛው ነው❓
ሀ// የታተመ ፈሳሽ
ለ// ዕፀ ሳቤቅ
ሐ// ታቦት
መ// ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

2⃣✏የቤተ ክርስቲያን የጸሎት መፅሐፍ በመባል የሚታወቀው የትኛው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው❓
ሀ// ትንቢተ ኢሳያስ
ለ// መዝሙረ ዳዊት
ሐ// የሉቃስ ወንጌል
መ// የዮሐንስ ራእይ

✅ለ

3⃣✏አንድ ሰው ሞቶ  በሚቀበርበት ጊዜ ፊቱን ወዴት አዙሮ ነው❓

ሀ// ወደ ምስራቅ
ለ// ወደ ምዕራብ
ሐ// ወደ ሰሜን
መ// ወደ ደቡብ

✅ሀ

4⃣✏ከሚከተሉት የመንፈስ ቅዱስ መጠሪያ ያልሆነው የትኛው ነው ❓
ሀ// ጰራቅሊጦስ
ለ// አፅናኝ
ሐ// የእግዚአብሔር እስትንፋስ
መ//ጰንጤ ቆስጤ

✅ሐ

5⃣✏ምስጢረ ሥጋዌ ምንድን ነው ❓
ሀ// የእግዚአብሔርን አንድነት እና ሦስትነት የምናይበት ምስጢር ነው
ለ// አምላክ ሰው የሆነበት ምስጢር ነው
ሐ// የቁርባን ምስጢር ነው
መ// ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅ለ

6⃣✏ከጌታችን ዐበይት በአላት የማይመደበው የትኛው ነው ❓
ሀ// ቃና ዘገሊላ
ለ// ብስራት
ሐ// ልደት
መ// ጥምቀት

✅ሀ

7⃣✏የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ የሆነው የትኛው ነው ❓
ሀ// በእርሻው መካከል ዘር የዘራው ሰው
ለ// እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ሐ// መልካምን ዕንቁ የሚሻ ነጋዴ
መ// ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

8⃣✏ክርስቶስ በተሰቀለጊዜ ግራ ጎኑን የወጋው ወታደር ማን ነበር❓
ሀ// በርባን
ለ// ጥጦስ
ሐ// ዳክርስ
መ// ለንጊኖስ

✅መ

9⃣✏ክርስቲያን ስንት ልደቶች አሉት❓
ሀ// አንድ
ለ// ሁለት
ሐ// ሦስት
መ// አራት

✅ለ

🔟✏ስግደት በምን አይነት ይከፋፈላል❓
ሀ// የአምልኮ እና የጸጋ
ለ// የጸጋ እና የአክብሮት
ሐ// የአክብሮት የጸጋና የአምልኮ
መ// መልሱ አልተሰጠም

✅ሐ

1⃣1⃣✏በቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና መሠረት ስንት አፅዋማት አሉ❓
ሀ// 3
ለ// 5
ሐ// 7
መ// 9

✅ሐ

1⃣2⃣ከመንፈስ ፍሬዎች መካከል ቀዳሚነትን የሚይዘው የትኛው ነው❓
ሀ// ትዕግስት
ለ// እምነት
ሐ// ደስታ
መ// ፍቅር

✅መ

1⃣3⃣ቤተ ክርስቲያን ስንል ምን ማለታችን ነው❓
ሀ// የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ የሚፈተትባት ቦታ
ለ// የክርስቲያኖች ኅብረት
ሐ// እያንዳንዱ ክርስቲያን የተባለ ወገን
መ// ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣4⃣✏ ጌታችን አምላክነቱን በደብረ ታቦር በገለጠ ወቅት ሙሴ እና ኤልያስ ያነጋግሩት ነበር ሙሴና ኤልያስ በምድር ላይ በነበሩበት ወቅት ሁለቱም ከእግዚአብሔር ጋር የተነጋገሩበት ተራራ የትኛው ነበር❓
ሀ// የታቦር ተራራ
ለ// የሞርያ
ሐ// ኮሬብ(የሲና ተራራ)
መ// የአራራ ተራራ

✅ሐ

1⃣5⃣✏ከሚከተሉት የመዝሙር ንዋያተ ቅዱሳት የእመቤታችን ምሳሌ የሚሆነው የትኛው ነው ❓
ሀ// ጸናጽል
ለ// በገና
ሐ// መሰንቆ
መ// ከበሮ

✅ሐ

1⃣6⃣✏ከዐራቱ ወንጌላውያን በስዕሉ ላይ አንበሳ ከጎኑ ሆኖ የሚሳለው ማን ነው❓
ሀ// ቅዱስ ማቴዎስ
ለ// ቅዱስ ማርቆስ
ሐ// ቅዱስ ሉቃስ
መ// ቅዱስ ዮሐንስ

✅ለ

1⃣7⃣✏ቤተ ክርስቲያንን የትኛው ይገልጻታል❓
ሀ// የድህነት መርከብ
ለ// የክርስቶስ ሙሽራ
ሐ// የክርስቶስ አካል
መ// ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣8⃣✏ተመሳሳይ (ሲኖፕቲክ) ወንጌል በመባል የሚታወቁት የትኞቹ ናቸው ❓
ሀ// የማቴዎስ ፣ማርቆስ እና ዮሐንስ ወንጌል
ለ// የማቴዎስ ፣ማርቆስ እና ሉቃስ ወንጌል
ሐ// የማርቆስ ፣ ሉቃስ እና ዮሐንስ ወንጌል
መ// የማቴዎስ እና የዮሐንስ ወንጌል

✅ለ

1⃣9⃣✏ሚስጢረ ሜሮን .....❓
ሀ// ድህነት ያገኘንበት ምስጢር ነው
ለ// ይቅርታ ነው
ሐ// የመንፈስ ቅዱስ ማህተም ነው
መ// ከሥጋ ደዌ የምንድንበት ሚስጢር

✅ሐ

2⃣0⃣የፍጥረት መጀመሪያ ዕለት ማን ናት❓
ሀ// ሰኞ
ለ// ማክሰኞ
ሐ// ዓርብ
መ// እሁድ

saramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ አምስት የ43ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ ውድድር

https://youtu.be/jY1O9jzyS_I
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
@Teyakaenamels
የ2011 ዓ.ም የምዕራፍ አምስት(፭) የ43ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
@ምንጭ 👉420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

1⃣🖊ከሚከተሉት ውስጥ ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የማይመደበው የትኛው ነው?

ሀ/ምሥጢረ ሥላሴ
ለ/ምሥጢረ ጥምቀት
ሐ/ምሥጢረ ሜሮን
መ/ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን

✅ሐ
2⃣🖊ስናማትብ ምን ማመላከታችን ነው??

ሀ/በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ማመናችን
ለ/አጋንንትን ማራቃችን
ሐ/ መስቀል አርማችን መሆኑን
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

3⃣🖊ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማይስማማ አገላለፅ የቱ ነው??

ሀ/የእግዚአብሔር አብ አንድያ ልጅ
ለ/ የሰው ልጅ
ሐ/የእግዚአብሔር ቃል
መ/ፍጡር

✅መ
4⃣🖊ከሐዋርያት መካከል "እንደ አምላኬ ሳይሆን ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ"  በማለት በሰማዕትነት ያለፈው ማን ነው?

ሀ/ቅዱስ ጳውሎስ
ለ/ቅዱስ ቶማስ
ሐ/ቅዱስ ጴጥሮስ
መ/ ቅዱስ ጢሞቴዎስ

✅ሐ
5⃣🖊ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ትክክል ያልሆነው አገላለፅ የቱ ነው?

ሀ/ሥላሴ በአካል ሦስት መሆናቸው
ለ/በአገዛዝ አንድ መሆናቸው
ሐ/ሥላሴ-በሕልውና ሦስት መሆናቸው
መ/በከዊን፦አብ ልብ፣ ወልድ ቃል፣ መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ መሆናቸው

✅ሐ
6⃣🖊ከሚከተሉት ውስጥ የማይደገመው የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር የቱ ነው??

ሀ/ ጥምቀት
ለ/ሜሮን
ሐ/ተክሊል
መ/ሁሉም

✅መ

7⃣🖊የጌታችን ዐበይት በዓላት ስንት ናቸው?

ሀ/ 7
ለ/8
ሐ/9
መ/10

✅ሐ

8⃣🖊ከሚከተሉት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ/ፊትን ወደ ምሥራቅ አዙሮ መጸለይ
ለ/የቅዱሳንን አማላጅነት ማመን
ሐ/መንፈሳዊት በዓላትን ማክበር
መ/መልስ አልተሰጠም

✅መ

9⃣🖊መዳንና ጽድቅ የሚገኘው .?

ሀ/በእምነት ብቻ ነው
ለ/በበጎ ተግባር ብቻ ነው
ሐ/በእምነትና በበጎ ተግባር ነው
መ/መልስ የለም

✅ሐ

🔟🖊የቤተክርስቲያንናችን ትምህርት የሆነው የትኛው ነው?

ሀ/እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው
ለ/መንፈስ ቅዱስ የሰረጸ ከአብ ብቻ ነው
ሐ/እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ናት
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

1⃣1⃣🖊ሦስቱ የክህነት ደረጃዎች የትኞቹ ናቸው??

ሀ/ኤጲስ ቆጶስ፣ቄስ፣ዲያቆን
ለ/ፓትርያርክ፣ሊቀ ጳጳስ፣ቆሞስ
ሐ/የነፍስ አባት፣የንስሀ አባት፣ ቄስ ገበዝ
መ/መልስ የለም

✅ሀ
1⃣2⃣🖊ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ የሚለን ለምንድን ነው??

ሀ/ የማያውቁንና የምናውቃቸው ሰዎች ቤተክርስቲያን መሔዳችንን አውቀው እንዲያመሰግኑ
ለ/ የጠፉ ዘመዶቻችን ስለምናገኝ
ሐ/አብሮ መዘመሩ ስለሚያስደስተንና የመዝሙር ፍላጎታችን ስለምናረካ
መ/በዐይን በሚታይና በጀሮ በሚሰማ የአምልኮት እግዚአብሔር አገልግሎት አማካይነት በዐይን የማይታይና በእጅ የማይዳሰስ የእግዚአብሔርን ጸጋ ስለምናገኝ

✅መ

1⃣3⃣🖊በቤተክርስቲያን ላይ በሚተከለው መስቀል ላይ የሚቀመጠው ምንድን ነው??

ሀ/የዓሳ ምልክት
ለ/የሰጎን እንቁላል
ሐ/የጦር ምልክት
መ/ምንም አይቀመጥም

✅ለ

1⃣4⃣🖊መንበረ መንግስት ስንት ስም አሏት

ሀ/1
ለ/ 2
ሐ/4
መ/3

✅መ

1⃣5⃣🖊ቅዱሳን መላእክ____?

ሀ/ይራዱናል
ለ/ይጠብቁናል
ሐ/ያማልዱናል
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ
1⃣6⃣🖊በቀን ውስጥ የታወቁት የጸሎት ጊዚያት ስንት ናቸው??

ሀ/1
ለ/3
ሐ/5
መ/7
✅መ
1⃣7⃣🖊የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ምንጮች የሆኑት የትኞቹ ናቸው??

ሀ/የብሉይ ኪዳንና የሐዲስክ ኪዳን መጽሐፍት
ለ/በየጊዜው የተደረጉ የቤተክርስቲያን ጉባኤዎችና ውሳኔዎች
ሐ/የቤተ ክርስቲያን አባቶች የጻፏቸው የታሪክ መጽሐፍት
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

1⃣8⃣🖊ስለ ቤተ ክርስቲያን ትክክል ያልሆነው አባባል የትኛው ነው?

ሀ/ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ቅድስት፣ዓለም አቀፋዊትና ሐዋርያዊት ናት።
ለ/የቤተ ክርስቲያን መሪ መንፈስ ቅዱስ ነው
ሐ/የክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ይባላል
መ/መልስ አልተሰጠም
✅መ
1⃣9⃣🖊ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን የማይመደበው የቱ ነው??

ሀ/ ጥምቀት
ለ/ተክሊል
ሐ/ቀንዲል
መ/ትንሳዔ ሙታን

✅መ

2⃣0⃣🖊ከሚከተሉት የቅዱሳት ሥዕላት ጥቅም የትኛው ነው?

ሀ/ለትምህርት
ለ/ለጸሎት
ሐ/ለተግሣጽ
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

saramareyama.890@gmail.com

2018 ሴፕቴምበር 25, ማክሰኞ

እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ አደረሰን

#መስቀሉ_አበራ

እዮሐ አበባዬ    መስከረም ጠባዬ (2)
መስከረም ሲጠባ ተተክሎ ደመራ
ህዝበ ኢትዮጵያን እዩት ችቦውን ሲያበራ
በታላቁ ብርሃን በመስቀል ደመራ (2)

#በኃጢአት_ጨለማ  አበራ መስቀሉ  ለእኛ አበራ
#ተውጠን_ሳለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የክርስቶስ_መስቀል  አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ብርሃን_ሆነልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ትምህርተ_መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ሆኖን_ላመንነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በቃሉ_ለምንድን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የእግዚአብሔር_ኃይል_ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀል ባንዲራችን
   የነጻነት አርማችን (2)

#በኢየሩሳሌም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አይሁድ_አብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ያዳናቸውን_አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አናውቅም_ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የድሉን_መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ከመሬት_ቀብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስሏቸው_ነበር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ውጦ_የሚያስቀረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በቀራንዮ ጎልጎታ
   ጠላታችን ድል ተመታ (2)

#ንግሥቲቷ_እሌኒ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በጣም_የታደለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ደመራን_አቁማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ፍለጋ_ጀመረች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀለ_ክርስቶስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ወዴት_ነው_እያለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በጣን_ጢስ_ተመርታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀሉን_አገኘች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በመስቀል መከታ
   ቆስጠንጢኖስ ድል ተመታ (2)

#ነገር_ግን_መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተቀብሮ_አልቀረም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተራራ_አፍርሶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ጠላት_አሳፈረ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀል_ሲወጣ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ታላቅ_ሁካታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ድውይ_ሲፈወስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አንካሳው_ዳነ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ሙታን_ተነሱ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ይመስገን_ጌታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ
    ክርስቲያኖች እልል በሉ (2)

#መስቀል_መከታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ይሁን_ጋሻችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#እንዳይደፈር_አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ዳር_ድንበራችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ኢትዮጵያ_ኑሪ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በእምነት_ፀንተሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ጌታ_በመስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የባረከሽ_አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀሉ አበራ
    እንደ ፀሀይ ጮራ (2)

#መስቀሉን_አምነን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተሳልመነዋል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ከክብሩ_ዙፋን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በእርሱ_ባርኮናል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#እንሰግድለታለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የፀጋ_ስግደት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በእርሱ_ላይ_ስላለ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ኃይለ_መለኮት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀል የእኛ ጋሻ
    የዲያብሎስ ድል መንሻ (2)

#የኢትዮጵያን መኩሪያ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ኑ_ተመልከቱልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የመስቀሉን_ብርሃን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ነፀብራቁን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#እፀ_መስቀሉ _ው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የእኛ_መከታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የተሰጠን_ለእኛ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ምልክታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በመስቀል እንመካለን
    እንድንበታለን (2)

#የዳዊት ልጅ ያዕቆብ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የሀገራችን ኩራት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የኢትዮጵያ ንጉሥ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ጌታን የሚፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ሀገሪቱን ሲዞር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ድካሙን ሳይፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ብርሐን እያበራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

የመስቀሉ ፍቅር
   በእኛ ላይ ይደር (2)

#መናገሻ_እንጦጦ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የረር አምባ አመራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ሲፈለግ_ሰንብቶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የመስቀል_ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ጊሸን ላይ አገኘ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የአምባሰል_ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ግማደ_መስቀሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አርፏል_ከዚያ_ስፍራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀል መስቀላችን
   የክርስቲያን ኃይላችን (2)

#የመስቀል_ለታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የደመራው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ኢትዮጵያውያን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተደስተው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በሀገር_ልብሳቸው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አምረው_ደምቀው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በአደባባዩ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተሰብስበው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ይዘምራሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀል_ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

የመስቀሉ ደመራ
    በኢትዮጵያ ሲያበራ (2)
Watch "የመስቀል ኮሌክሽን መዝሙሮች" on YouTube
https://youtu.be/_YnPAwv1sZE

2018 ሴፕቴምበር 23, እሑድ

መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
@Teyakaenamels
@Teyakaenamels

1ኛ) አምሥቱ(5) አዕማደ ምስጢር የሚባሉት ምን ምን ናቸው?  መልስ፦  ሚስጥረ ሥላሴ
ሚስጥረ ስጋዌ
ሚስጥረ ጥምቀት
ሚስጥረ ቁርባን
ሚስጥረ ትንሳኤ ሙታን ናቸው።
2ኛ) ቤተ ክርስቲያን ስንት ባህሪ አሏት? መልስ፦ቤተ ክርስቲያን  4 ባህሪ አሏት እነሱም 1ኛ፦ በመጀመርያ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ነች።
2ኛ፦ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ነች።
3ኛ፦ቤተክርስቲያን ኩሉውይት ነች።
4ኛ፦ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያት ነች ማለት ነው።
3ኛ) እናታችን ቅድስት አርሴማ  ሰይፍ  ከአረፈባተ በኋላ ለስንት ስዓት ቆመች? የናታችን የአርሴማ ሃገርስ የት ነው? መልስ፦ እናታችን ቅድስት አርሴማ ሰይፍ ከአረፈባት በኋላ ለ3 ስዓት ቁማለች ሃገሯ ደግሞ አርመንያ ነው።
4ኛ)  የእመቤታችን በዓላት ስንት ናቸው? መልስ፦  33 ናቸው።
5ኛ) ማርያም ፊደል የሚለውን ቃል የተናገሩት አባት ማን ናቸው (ማን) ይባላሉ? መልስ፦ አባታችን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ናቸው።
6ኛ) ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ክርስትና የተመለሰው ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርገት በኋላ በስንተኛው አመት ነው?  መልስ፦በ8ኛ አመቱ ነው።
7ኛ) መጽሐፍ ነገስት በስንት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል? መልስ፦በ3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል።
8ኛ) ዜና መዋል ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦ የእለት ዜና ማለት ነው።
9ኛ) ምናሴ ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦  ማስረሻ ማለት ነው።
10ኛ)መስፍን ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦  ፈራጅ፤ አስተዳዳሪ ማለት ነው።
11ኛ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ከዘንዶ አፍ ያዳናት ልጅ ስማ ማን ትባላለች? መልስ፦ ብሩክታይት ትባላለች።
12ኛ) አኬልዳማ ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦  የደም መሬት ማለት ነው።
13ኛ) ፃዲቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ በስንት አመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ? መልስ፦  በ480 ዓ.ም ነው።
14ኛ ከነአን የምን ምሳሌ ናት?መልስ፦የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት።
15ኛ) ላንች የማይገዛ ህዝብና መንግስት ይጠፋል። ይህን ሃይለ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኛዋለን? ምዕራፍና ቁጥሩን? መልስ፦ኢ.ሳ 60፥12 ላይ ነው።
16ኛ)በጨረቃ በከዋክብት ላይ ስልጣን የተሰጠው መላክ ማን ነው? መልስ፦ ቅዱስ ሩፋኤል ነው።
17ኛ) ቁርባን ማለት ምን ማለት ነው? መልስ፦ በሱርስት ቋንቋ መባ፤ስጦታ ማለት ነው።
18ኛ) ደስታ በስንት ይከፈላል? መልስ፦ ደስታ በሁለት(2) ይከፈላል መንፈሳዊ ደስታ እና ሥጋዊ ደስታ ነው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭) የ42ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፫

የምዕራፍ (፭)/የ42ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃልና የጹህፍ ጥያቄና መልስ ውድድር⤵

@ምንጭ ማኅበረ ቅዱሳን 420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ⤵

ማጠቃለያ መልስ🖊
➡1⃣ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዌ በሐዋርያት አጠራር ትርጉሙ "የመጽናናት ልጅ" የሚሆን ስም ተሰጠው። የዚህ ሐዋርያ ስም ማን ነው?

ሀ. ፋሮስ
ለ.እስክንድሮስ
ሐ.አጵሎስ
መ. በርናባስ

✅መ

➡2⃣"ጌታ ሆይ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ ነገር እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎቹ ሰምቻለሁ። በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው።" ተብሎ የተነገረው ስለ ማን ነው?

ሀ. ሐናንያ
ለ.ስምዖን
ሐ.ሳውል
መ.በርስያስን

✅ሐ

➡3⃣የሞት አያት ማን ነው?

ሀ. ኃጢአት
ለ.ተንኮል
ሐ.ምኞት
መ.ቁጣ

✅ለ

➡4⃣አጋቦስ ይባል የነበረው ነቢይ ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ በመውረድ ምን ተነበየ?

ሀ. ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚታሰር
ለ. በምድር ላይ ራብ እንደሚመጣ
ሐ. ኢየሩሳሌም በሮማውያን ወታደሮች ፈጽማ እንደምትጠፋ
መ.ክርስትና በዓለም እንደሚሰበክ

✅ለ

➡5⃣አይሁድን ደስ ያሰኝ ዘንድ በክርስቲያኖች ዘንድ መከራን ያጸናው ንጉሥ ማን ነው?

ሀ. ሄሮድስ አንቲጳስ
ለ. ሄሮድስ ቀዳማዊ አግሪጳ
ሐ.ሄሮድስ ዳግማዊ አግሪጳ
መ.ጲላጦስ

✅ሐ

➡6⃣ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን?" ያለው ሐዋርያ ማን ነው?

ሀ.ፊሊጶስ
ለ.ታዴዎስ
ሐ.ቶማስ
መ.ናትናኤል

✅መ

➡7⃣ከሐዋርያት መካከል  አስቀድሞ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የተናገረው ማን ነው?

ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ. ቅዱስ ቶማስ
ሐ.ቅዱስ ናትናኤል
መ. ቅዱስ ፊልጶስ

✅ሀ

➡8⃣በሁለተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ አብሮ የነበረው ማን ነው?

ሀ.አቂላስ
ለ.ሲላስ
ሐ.ጵርስቅላ
መ.በርናባስ

✅ሐ

➡9⃣በሕልሙ የመቄዶንያ ሰው ለእርዳታ ሲጠራው ያየው ማን ነው?

ሀ. ቅዱስ ጳውሎስ
ለ.ቅዱስ ቲቶ
ሐ.ቅዱስ ሉቃስ
መ.ቅዱስ ጋይዮስ

✅ሀ

➡🔟ቅዱስ ጳውሎስ በአንድ ከተማ በሚመላለስበት ወቅት ሰዎች "ለማይታወቅ አምላክ" ብለው ጽፈው በመመልከቱ በማዘን ትምህርት አስተምሯቸዋል።
ከተማው የትኛው ነበር?

ሀ. ተሰሎንቄ
ለ.ቆሮንቶስ
ሐ.ኤፌሶን
መ.አቴና

✅መ

➡1⃣1⃣ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር አብረው ድንኳን ይሰፉ የነበሩት ማንና ማን ናቸው?

ሀ.ሲላስ እና ጢሞቴዎስ
ለ.አጵሎስ እና በርናባስ
ሐ. አቂላ እና ጵርስቅላ
መ.ማርቆስ እና ሉቃስ

✅ለ

➡1⃣2⃣ቅዱስ ጳውሎስ ለፊልሞና በጻፈው መልእክቱ ማንን ይቅር እንዲል መክሮታል?

ሀ. አገልጋዩ ግያዝን
ለ.ውሸተኞች ወንድምችን
ሐ. አገልጋዩ አናሲሞስን
መ.መልስ የለም

✅ሐ

➡1⃣3⃣የክፋት ሁሉ ሥር ምንድን ነው?

ሀ. ትዕቢት
ለ.ቁጣ
ሐ.ዝሙት
መ.ገንዘብን መውደድ

✅መ

➡1⃣4⃣የልስጥራን ሰዎች ሁለት ሐዋርያትን ድያ እና ሄርሜን በማለት በአማልክቶቻቸው ስም ሰይመዋቸዋል። ሐዋርያቱ እነማን ነበሩ?

ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ
ለ.ቅዱስ ጢሞቴዎስ እና ቅዱስ ቲቶ
ሐ. ቅዱስ እንድርያስ እና ቅዱስ ታዴዎስ
መ.ቅዱስ በርናባስ እና ቅዱስ ጳውሎስ

✅መ

➡1⃣5⃣ከሐዋ መካከል በሰማዕትነት ያላለፈው ማን ነው?

ሀ. ቅዱስ ጴጥሮስ
ለ.ቅዱስ ያዕቆብ
ሐ. ቅዱስ እንድርያስ
መ.ቅዱስ ዮሐንስ

✅መ

➡1⃣6⃣ቅዱስ ጳውሎስ "የእግዚአብሔር ጦር ዕቃ ብሎ የሰየመው የትኛውን ነው?

ሀ. የእውነትን ቀበቶ
ለ.ለእግዚአብሔር ቃል
ሐ.የእምነት ጋሻ
መ. ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

➡1⃣7⃣በሐዋርያት ስም ዝርዝር የመጀመሪያውን ቦታ ይዞ የሚገኘው ማን?

ሀ. ቅዱስ እንድርያስ
ለ.ቅዱስ ጴጥሮስ
ሐ. ቅዱስ ጳውሎስ
መ. ቅዱስ ፊልጶስ

✅ለ

➡1⃣8⃣ዐበይት ነቢያት የሚባሉት ማን ማን ናቸው?

✅ኢሳያስ፣ ኤርምያስ፣ሕዝቅኤልና ዳንኤል  ናቸው።

➡1⃣9⃣ የተራራው ሥብከት ዐሥሩ ዐበይት ክፍሎች ማን ማን ናቸው??

✅ክፍል አንድ፦ ስለ አንቀጸ ብፁዓን/ማቴ 5፥3-12/

ክፍል ሁለት፦ስለ አንቀጸ ምግባር/ማቴ 5፥13-16

ክፍል ሦስት፦አጽንኦተ ሕግ/ማቴ 5፥17-48

ክፍል አራት፦ ሦስቱ አናቅጸ ምግባራት/ ማቴ 6፥1-8

ክፍል አምስት፦እግዚአብሔርን ማስቀደም እንዲገባ/ማቴ 6፥19-34

ክፍል ስድስት፦ አትፍረዱ/ማቴ.7፥1-6

ክፍል ሰባት፦ እንድንጸልይ መታዘዛችን/ ማቴ.7፥7-12

ክፍል ስምንት፦ቀጭን መንገድ በጠባቡ በር/ማቴ. 7፥13-14

ክፍል ዘጠኝ፦ መልካም ፍሬ ከመልካም ዛፍ/ ማቴ.7፥15-20

ክፍል አስር፦ ጽድቅ በተአምራት ሳይሆን በሥራ ስለመሆኑ/ማቴ 7፥21-29

➡2⃣0⃣በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ በገና፣ዋሽን፣ጸናጽል፣ከበሮ፣እምቢልታ፣ ነጋሪት፣መለከት፣ መሰንቆ ተጽፎ የምናገኘው በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው?

✅በገና፣መሰንቆ፣ነጋሪት፣ጽናጽል 2ኛ.ሳሙ 6፥5
ዋሽንት፣ክራር ት.ዳ. 3፥5/ ዘፍ.4፥21/ከበሮ፣እንቢልታ/ኢሳ.5፥12/ዘዳ.15፥20/መለከት/1ኛ.ነገስት 1፥40/

ወስብሀት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!saramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...