2018 ኦክቶበር 27, ቅዳሜ

የምዕራፍ 5 የ45ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

Watch "የምዕራፍ አምስት (፭) የ45ኛዙር የጠቅላላ እውቀት  መንፈሳዊ የቃል ጥያቄና መልስ ውድድርhttps://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8V" on YouTube
https://youtu.be/Lrf4stF7NSE

https://youtu.be/Lrf4stF7NSE
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን!

↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 45ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️

1⃣.መጠመቅ ያለብን በማን ስም ነው?
ሀ/ በኢየሱስ
ለ/ በእግዚአብሔር አብ ስም
ሐ/ በመንፈስ ቅዱስ ስም
መ/ በአብ ፡በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም

✅መ

2⃣.ከጌታችን መድኃኂታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ልደት አስቀድሞ የሚመጡ ሦስት እሑዶች ስያሜያቸው ምንድን ነው?
ሀ/  ስብከት ፡ኒቆዲሞስ ደብረ-ዘይት
ለ/  ቅድስት፡ ዘወረደ፡ መፃጉዕ
ሐ/ ስብከት፡ ብርሃን ፡ኖላዊ
መ/ ምኩራብ ፡ገብርሔር፡ ብርሃን

✅ሐ

3⃣.የሰው ልጅ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ መፈጠሩ ግልጽ ሲሆን ዕድሜውም እንዲሁ በዐራት ደረጃዎች የተከፈለ ነው።በዚህም መሠረት ከሃያ እስከ ዐርባ ዓመት ያለው ጌዜ የትኛውን ባሕርይ ያመለክታል?
ሀ/ የነፋስ
ለ/ የእሳት
ሐ/ የውኃ
መ/ የመሬት

✅ለ

4⃣.ስለስንበተ-ክርስቲያንና ስለ ዕለተ ምጽአት የሚናገረው ቅዳሴ?
ሀ/ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
ለ/ ቅዳሴ ማርያም
ሐ/ ቅዳሴ አትናቴዎስ
መ/ ቅዳሴ ባስልዮስ

✅ሐ

5⃣.ቅዱስ ቅባት በመቀባት ከሥጋም ከነፍስም ደዌ የምንድንብት ምሥጢር የትኛው ነው?
ሀ/ ምሥጢረ ሜሮን
ለ/ ምሥጢረ ቀንዲል
ሐ/ ምሥጢረ ተክሊል
መ/ ምሥጢረ ቁርባን

✅ለ

6⃣.የሥርዓተ ቅዳሴ ዋነኛው ዓላማ፣
ሀ/ በኅብረት መጸለይ
ለ/ ወንጌል  መማር
ሐ/ ቅዱስ ቁርባን
መ/ ሁሉም

✅መ

7⃣.በላሕም/ላም/ የሚመስለው ወንጌላዊ ማነው?
ሀ/ ቅዱስ ማቴዎስ
ለ/ ቅዱስ ማርቆስ
ሐ/ ቅዱስ ሉቃስ
መ/ ቅዱስ ዮሐንስ

✅ሐ

8⃣.የቤተክርስቲያን የውስጥ ክፍሎች ምን ምን ተብለው ይታወቃሉ?
ሀ/መቅደስ ፡ቅደስትና ቅኔ ማኅሌት
ለ/ ደጀ ስላም ፡ቤተልሔምና መቅደስ
ሐ/ ቅድስተ- ቅዱሳን መቅደስና ቤተልሔም
መ/ መልሱ አልተስጠም

✅ሀ

9⃣.ከሚከተሉት በቅዳሴ ሰዓት የማይነበብ ምንባብ የትኛው ነው?
ሀ/ ወንጌል
ለ/ ትንቢተ ኢሳይያስ
ሐ/ ከሐዋርያት ሥራ
መ/ ከቅዱስ ጳውሎስ መልዕክታት

✅ለ

🔟.ምሥጢረ ቁርባን
ሀ/ ኀብስቱ ወደ ሥጋ መለኮት ወይኑ ወደ ደመ መለኮት የሚለወጥበት ምሥጢር
ለ/ ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የሚመደብ ነው
ሐ/ እያንዳንዱ ክርስቲያን ሊሳተፍበት የሚገባ ምጢር ነው
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣1⃣.ከሚከተሉት በዕለቱ የተጋደሉትን ቅዱሳን ታረክ የምናነብበት መጽሐፍ የትኛው ነው?
ሀ/ መጽሐፍ ስንክሣር
ለ/ ገድለ ሐዋርያት
ሐ/ ድርሳነ ስንበት
መ/ ዜና አበው

✅ሀ

1⃣2⃣.በሥርዓተ ቅዳሴ ሊደረግ የማይገባው ድርጊት የትኛው ነው?
ሀ/ የግል ጸሎት መጸለይ
ለ/ ወሬ ማውራት
ሐ/ መሳቅ
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

✅መ

1⃣3⃣.ከሚከተሉት ስለ ንስሐ ትክክል እና ገላጭ የሆነው የትኛው ነው?
ሀ/ ኃጢታትን ይቅር የሚልና የሚያስተስርይ እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ለ/ የሠሩትን ኃጢያት ማመን ለመምህረ- ንስሐ መንገር እና ዳግም ላለመስራት መወስን ፡ንስሐ መግባትነው።
ሐ/ ንስሐ መግባት ያለብን በየጊዜው  ነው
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣4⃣.ከትንሣኤ ጀምሮ ለሃምሳ ቀናት የሚቀደስው የትኛው ቅዳሴ ነው?
ሀ/ ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
ለ/ ቅዳሴ ሐዋርያት
ሐ/ ቅዳሴ ዘሠለስቱ ምዕት
መ/ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ

✅መ

1⃣5⃣.ምሥጢረ ጥምቀትን የሚፈጽመው ማነው?
ሀ/ ዲያቆን
ለ/ ቄስ
ሐ/ ጳጳስ
መ/ ለእናሐ መልስ ይሆናሉ

✅መ

1⃣6⃣.ከዐቢይ ጾም እሑድ ስያሜዎች የማይመደበው የትኛው ነው?
ሀ/ ዘወረደ
ለ/ ምኲራብ
ሐ/ ኖላዊ
መ/ ገብርሔር

✅ሐ.

1⃣7⃣.አንቀጸ አባግዕ/የበጎች አንቀጽ/በመባል የሚታውቀው ክፍል የትኛው ነው?
ሀ/ ማቴ.5
ለ/ ማር.1
ሐ/ ሉቃ.18
መ/ ዮሐ.10

✅መ

1⃣8⃣.ከአሥራ ዐራቱ ቅዳሴያት ጸሐፊዎች መካክል ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ/ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ለ/ ቅዱስ ባስልዮስ
ሐ/ ቅዱስ ኤፍሬም
መ/ ቅዱስ ጎርጎርዮስ

✅ሐ

1⃣9⃣.ምሥጢረ ክህነትን የሚፈጽመው ማን ነው?
ሀ/ ዲያቆን
ለ/ ቄስ
ሐ/ ጳጳስ
መ/ ማንኛውም ክርስቲያን

✅ሐ

2⃣0⃣.ዲያቆኑ ክቡር ደሙን ለምዕመናን የሚያቀብልበት ንዋየ-ቅዱስ ምን ተብሎ ይጠራል?
ሀ/ ጻሕል
ለ/ አጎበር
ሐ/ እርፈ መስቀል
መ/ ማኀፈድ

✅ሐ

ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላለ ከስተቴ እረሙኝ
saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...