2018 ኦክቶበር 2, ማክሰኞ

የምዕራፍ አምስት የ43ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ ውድድር

https://youtu.be/jY1O9jzyS_I
✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
@Teyakaenamels
የ2011 ዓ.ም የምዕራፍ አምስት(፭) የ43ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
@ምንጭ 👉420 ጥያቄዎች እስከ መልሶቻቸው ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

1⃣🖊ከሚከተሉት ውስጥ ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት የማይመደበው የትኛው ነው?

ሀ/ምሥጢረ ሥላሴ
ለ/ምሥጢረ ጥምቀት
ሐ/ምሥጢረ ሜሮን
መ/ምሥጢረ ትንሳኤ ሙታን

✅ሐ
2⃣🖊ስናማትብ ምን ማመላከታችን ነው??

ሀ/በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ማመናችን
ለ/አጋንንትን ማራቃችን
ሐ/ መስቀል አርማችን መሆኑን
መ/ ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

3⃣🖊ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማይስማማ አገላለፅ የቱ ነው??

ሀ/የእግዚአብሔር አብ አንድያ ልጅ
ለ/ የሰው ልጅ
ሐ/የእግዚአብሔር ቃል
መ/ፍጡር

✅መ
4⃣🖊ከሐዋርያት መካከል "እንደ አምላኬ ሳይሆን ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ"  በማለት በሰማዕትነት ያለፈው ማን ነው?

ሀ/ቅዱስ ጳውሎስ
ለ/ቅዱስ ቶማስ
ሐ/ቅዱስ ጴጥሮስ
መ/ ቅዱስ ጢሞቴዎስ

✅ሐ
5⃣🖊ስለ ምሥጢረ ሥላሴ ትክክል ያልሆነው አገላለፅ የቱ ነው?

ሀ/ሥላሴ በአካል ሦስት መሆናቸው
ለ/በአገዛዝ አንድ መሆናቸው
ሐ/ሥላሴ-በሕልውና ሦስት መሆናቸው
መ/በከዊን፦አብ ልብ፣ ወልድ ቃል፣ መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ መሆናቸው

✅ሐ
6⃣🖊ከሚከተሉት ውስጥ የማይደገመው የቤተ ክርስቲያን ምሥጢር የቱ ነው??

ሀ/ ጥምቀት
ለ/ሜሮን
ሐ/ተክሊል
መ/ሁሉም

✅መ

7⃣🖊የጌታችን ዐበይት በዓላት ስንት ናቸው?

ሀ/ 7
ለ/8
ሐ/9
መ/10

✅ሐ

8⃣🖊ከሚከተሉት ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ/ፊትን ወደ ምሥራቅ አዙሮ መጸለይ
ለ/የቅዱሳንን አማላጅነት ማመን
ሐ/መንፈሳዊት በዓላትን ማክበር
መ/መልስ አልተሰጠም

✅መ

9⃣🖊መዳንና ጽድቅ የሚገኘው .?

ሀ/በእምነት ብቻ ነው
ለ/በበጎ ተግባር ብቻ ነው
ሐ/በእምነትና በበጎ ተግባር ነው
መ/መልስ የለም

✅ሐ

🔟🖊የቤተክርስቲያንናችን ትምህርት የሆነው የትኛው ነው?

ሀ/እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው
ለ/መንፈስ ቅዱስ የሰረጸ ከአብ ብቻ ነው
ሐ/እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ናት
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

1⃣1⃣🖊ሦስቱ የክህነት ደረጃዎች የትኞቹ ናቸው??

ሀ/ኤጲስ ቆጶስ፣ቄስ፣ዲያቆን
ለ/ፓትርያርክ፣ሊቀ ጳጳስ፣ቆሞስ
ሐ/የነፍስ አባት፣የንስሀ አባት፣ ቄስ ገበዝ
መ/መልስ የለም

✅ሀ
1⃣2⃣🖊ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ የሚለን ለምንድን ነው??

ሀ/ የማያውቁንና የምናውቃቸው ሰዎች ቤተክርስቲያን መሔዳችንን አውቀው እንዲያመሰግኑ
ለ/ የጠፉ ዘመዶቻችን ስለምናገኝ
ሐ/አብሮ መዘመሩ ስለሚያስደስተንና የመዝሙር ፍላጎታችን ስለምናረካ
መ/በዐይን በሚታይና በጀሮ በሚሰማ የአምልኮት እግዚአብሔር አገልግሎት አማካይነት በዐይን የማይታይና በእጅ የማይዳሰስ የእግዚአብሔርን ጸጋ ስለምናገኝ

✅መ

1⃣3⃣🖊በቤተክርስቲያን ላይ በሚተከለው መስቀል ላይ የሚቀመጠው ምንድን ነው??

ሀ/የዓሳ ምልክት
ለ/የሰጎን እንቁላል
ሐ/የጦር ምልክት
መ/ምንም አይቀመጥም

✅ለ

1⃣4⃣🖊መንበረ መንግስት ስንት ስም አሏት

ሀ/1
ለ/ 2
ሐ/4
መ/3

✅መ

1⃣5⃣🖊ቅዱሳን መላእክ____?

ሀ/ይራዱናል
ለ/ይጠብቁናል
ሐ/ያማልዱናል
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ
1⃣6⃣🖊በቀን ውስጥ የታወቁት የጸሎት ጊዚያት ስንት ናቸው??

ሀ/1
ለ/3
ሐ/5
መ/7
✅መ
1⃣7⃣🖊የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ምንጮች የሆኑት የትኞቹ ናቸው??

ሀ/የብሉይ ኪዳንና የሐዲስክ ኪዳን መጽሐፍት
ለ/በየጊዜው የተደረጉ የቤተክርስቲያን ጉባኤዎችና ውሳኔዎች
ሐ/የቤተ ክርስቲያን አባቶች የጻፏቸው የታሪክ መጽሐፍት
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

1⃣8⃣🖊ስለ ቤተ ክርስቲያን ትክክል ያልሆነው አባባል የትኛው ነው?

ሀ/ቤተ ክርስቲያን አንዲት፣ቅድስት፣ዓለም አቀፋዊትና ሐዋርያዊት ናት።
ለ/የቤተ ክርስቲያን መሪ መንፈስ ቅዱስ ነው
ሐ/የክርስቲያኖች ህብረት ቤተ ክርስቲያን ይባላል
መ/መልስ አልተሰጠም
✅መ
1⃣9⃣🖊ከሰባቱ ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን የማይመደበው የቱ ነው??

ሀ/ ጥምቀት
ለ/ተክሊል
ሐ/ቀንዲል
መ/ትንሳዔ ሙታን

✅መ

2⃣0⃣🖊ከሚከተሉት የቅዱሳት ሥዕላት ጥቅም የትኛው ነው?

ሀ/ለትምህርት
ለ/ለጸሎት
ሐ/ለተግሣጽ
መ/ሁሉም መልስ ይሆናል

✅መ

saramareyama.890@gmail.com

3 አስተያየቶች:

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...