2018 ሴፕቴምበር 25, ማክሰኞ

እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ አደረሳችሁ አደረሰን

#መስቀሉ_አበራ

እዮሐ አበባዬ    መስከረም ጠባዬ (2)
መስከረም ሲጠባ ተተክሎ ደመራ
ህዝበ ኢትዮጵያን እዩት ችቦውን ሲያበራ
በታላቁ ብርሃን በመስቀል ደመራ (2)

#በኃጢአት_ጨለማ  አበራ መስቀሉ  ለእኛ አበራ
#ተውጠን_ሳለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የክርስቶስ_መስቀል  አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ብርሃን_ሆነልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ትምህርተ_መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ሆኖን_ላመንነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በቃሉ_ለምንድን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የእግዚአብሔር_ኃይል_ነው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀል ባንዲራችን
   የነጻነት አርማችን (2)

#በኢየሩሳሌም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አይሁድ_አብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ያዳናቸውን_አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አናውቅም_ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የድሉን_መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ከመሬት_ቀብረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስሏቸው_ነበር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ውጦ_የሚያስቀረው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በቀራንዮ ጎልጎታ
   ጠላታችን ድል ተመታ (2)

#ንግሥቲቷ_እሌኒ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በጣም_የታደለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ደመራን_አቁማ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ፍለጋ_ጀመረች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀለ_ክርስቶስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ወዴት_ነው_እያለች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በጣን_ጢስ_ተመርታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀሉን_አገኘች አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በመስቀል መከታ
   ቆስጠንጢኖስ ድል ተመታ (2)

#ነገር_ግን_መስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተቀብሮ_አልቀረም አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተራራ_አፍርሶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ጠላት_አሳፈረ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀል_ሲወጣ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ታላቅ_ሁካታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ድውይ_ሲፈወስ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አንካሳው_ዳነ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ሙታን_ተነሱ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ይመስገን_ጌታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ
    ክርስቲያኖች እልል በሉ (2)

#መስቀል_መከታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ይሁን_ጋሻችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#እንዳይደፈር_አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ዳር_ድንበራችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ኢትዮጵያ_ኑሪ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በእምነት_ፀንተሽ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ጌታ_በመስቀል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የባረከሽ_አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀሉ አበራ
    እንደ ፀሀይ ጮራ (2)

#መስቀሉን_አምነን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተሳልመነዋል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ከክብሩ_ዙፋን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በእርሱ_ባርኮናል አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#እንሰግድለታለን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የፀጋ_ስግደት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በእርሱ_ላይ_ስላለ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ኃይለ_መለኮት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀል የእኛ ጋሻ
    የዲያብሎስ ድል መንሻ (2)

#የኢትዮጵያን መኩሪያ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ኑ_ተመልከቱልን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የመስቀሉን_ብርሃን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ነፀብራቁን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#እፀ_መስቀሉ _ው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የእኛ_መከታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የተሰጠን_ለእኛ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ምልክታችን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

በመስቀል እንመካለን
    እንድንበታለን (2)

#የዳዊት ልጅ ያዕቆብ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የሀገራችን ኩራት አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የኢትዮጵያ ንጉሥ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ጌታን የሚፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ሀገሪቱን ሲዞር አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ድካሙን ሳይፈራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀል ተሸክሞ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ብርሐን እያበራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

የመስቀሉ ፍቅር
   በእኛ ላይ ይደር (2)

#መናገሻ_እንጦጦ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የረር አምባ አመራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ሲፈለግ_ሰንብቶ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የመስቀል_ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ጊሸን ላይ አገኘ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የአምባሰል_ተራራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ግማደ_መስቀሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አርፏል_ከዚያ_ስፍራ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

መስቀል መስቀላችን
   የክርስቲያን ኃይላችን (2)

#የመስቀል_ለታ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#የደመራው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ኢትዮጵያውያን አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተደስተው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በሀገር_ልብሳቸው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#አምረው_ደምቀው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#በአደባባዩ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ተሰብስበው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#ይዘምራሉ አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ
#መስቀል_ብለው አበራ መስቀሉ ለእኛ አበራ

የመስቀሉ ደመራ
    በኢትዮጵያ ሲያበራ (2)
Watch "የመስቀል ኮሌክሽን መዝሙሮች" on YouTube
https://youtu.be/_YnPAwv1sZE

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...