2018 ሜይ 4, ዓርብ

የምዕራፍ ሦስት መጨርሻል የ30ኛ ዙር ጥያቄና መልስ ውድድር

#✝በስመ #አብ #ወወልድ #ወመንፈስ #ቅዱስ #አሃዱ #አምላክ #አሜን

#↪የምዕራፍ #ሦስት #መጨረሻ #የ30 #ዙር #የጠቅላላ #እውቀት ^የቃል #መንፈሳዊ #ጥያቄና #መልስ #ውድድር

↪ጥ.ተራ ቁ.✍1⃣ትንሳኤ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በየመልኩ በየአይነቱ ሲተረጎም 5ክፍሎች አሉት ምን ምን ናቸው??

#መልስ#

1)አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው ፡፡ይህም ማለት ተዘክሮተእግዚአብሔርነው፡፡
2)
ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና
ነው ፡፡የዚህም ምስጢሩ ቃለእግዘብሔርንመስማትና በንስሐእየታደሱበሕይወት መኖር ነው፡፡
3)
ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜው
የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል ፡፡ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡
4)
አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ
በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን
አድርጎ መነሣት ነው፡ ፡

5) ዐምስተኛውና የመጨረሻው«
የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ
ድልአምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን
ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ»
መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ »
ነው፡፡ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላሰውሁሉ እንደየሥራው ለክብርናለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔበአንድነት የሚነሣው የዘለዓለምትንሣኤ ይሆናል፡፡
ዘጉባኤወደተነሣንበት ዐላማ ስንመለስየትንሣኤበዓል በቃሉም ምስጢርበይዘቱምስለሚመሳሰሉ ጥላውምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎይጠራል፡፡

↪ጥ.ተራ.ቁ✍2⃣ ጴራቅሊጦስ ማለት የግሪክ(የጽርህ ቃል) ሲሆን 5ትርጉሞች አሉት ምን ምን ናቸው??


#መልስ 1.ናዛዚ=የሚያረጋጋ መንፈስ ማለት ነው
2.ከሳቲ=ገላጭ/ምስጢር ገላጭ/ማለት ነው
3.መንቅሂ=የሚያነቃቃ//መንፈስ ማለት ነው
4.መጽንኢ=የሚያጸና /የሚያጠነክር/መንፈስ ማለት ነው
5.መስተስፍሂ=ደስ የሚያነሳሳየሚያሰኝ መንፈስ ማለት ነው።

↪ጥ.ተራ.ቁ✍3⃣ስንት አይነት ሞት አለ??

#መልስ#
➡አራት አይነት ሞት አለ እነሱም ሞተ  ሥጋ(
 ሞት) እርደተ መቃብር ነው ሥጋ ወደ መሬት ነፍስ ወደ ሰማይ መ መክ 12÷7
➡ሞተ ነፍስ (የነፍስ ሞት) እሱን የማትሰማ ነፍስ የሥጋትሞታለች
ዘዳ 18÷15
ሀዋ 3÷23
➡ሞተ ሀጢአት(የሀጢአ ያት ሞት)የሀጢያት ደመወዝ ሞት ነውና ሮሜ 6÷23 ቆላ 1÷22
➡ሞተ ህሊና (የህሊና ሞት) ናቸው።

↪ ጥ.ተራ ቁ.✍4⃣የእናታችን የድንግል ማርያምን ስም ያስተዋወቀ ማን ነው??

#መልስ# ✍ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ነው።

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍5⃣ መንፈሳዊ ውበት ከሚባሉት ውስጥ ቢያንስ 5 ጥቀስ???

#መልስ#↪
➡እግዚአብሔርን መፍራት በፈሪሀ እግዚአብሔር መገዛት
➡ትህትና ትሁት መሆን ነው
➡ቅንነት
➡ንፁህ ልብ ነው
➡ለፅድቅ መጨከን የእግዚአብሔርን ቃል ላለማፍረስ መጠንከር ውበት ነው
➡ይቅርታ
➡ማስታረቅ.ወ.ዘተ


↪ ጥ.ተራ.ቁ.✍ ህገ ወንጌል ማለት ከማን እስከ ማን ያለው  ዘመን ነው?

#መልስ#✍
➡ክርስቶስ በሥጋ ከተገለጠበት እስከ እለተ ምጽዓት አሁን የያዝነው ዘመን ጨምሮ ያለው ነው።

↪ጥ.ተራ ቁ✍7⃣. ሙሴ ግብፃውያንን ገድሎ እስራኤላውያንን ነፃ አወጣ ወደ ክርስቶስ ታሪክ። ቀይሩ??

#መልስ#✍
➡ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ።ዲያብሎስን ግድሎ እኛን ከዲያብሎስ ባርነት በደሙ ልጆቹን ነፃ አወጣን።

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍8⃣በብሉይ ኪዳን የሰመረ የአማረ ለእግዚአብሔር መስዋዕት ካቀረቡ አበው መካከል የ8 አባቶችን ስም ዘርዝሩ ??

#መልስ#

➡አዳም
➡አቤል
➡ሄኖክ
➡መልከ ፀዴቅ
➡አብረሀም
➡ይስሀቅ
➡ያዕቆብ
.
↪ጥ.ተራ.ቁ.✍9⃣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዬሐንስ በእስር ቤት እያለ ወደ ጌታ የላካቸው ደቀ መዛሙርቶች ስንት ነበሩ?  ጌታስ የላከለት መልስ ምን የሚል ነበር?

#መልስ#↪ሁለት ናቸው። ጌታ የላከለትም መልእክት ዕውሮች ያያሉ፣ አንኮች ይሄዳሉ፣ ለምፃሞች ይነፃሉ። (ማቴ 11፥26)

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍, ጌታ መስቀል ላይ እያለ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተቀዷል፡፡ ለመሆኑ ምስጢሩ ምንድን ነው??

#መልስ፡- በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ያለው የጠብ ግድግዳ ፈረሰ ማለት ነው፡፡ ማቴ.27÷51።

↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣1⃣ አዲስ ኪዳን ማለት ምን ማለት ነው ?የተመሰረተው መቼ ነው? ዕለቱስ??

#መልስ፡-አዲስ ውል/ ስምምነት/ ማለት ነው፡፡ በጸሎተ ሐሙስ እለት፡፡ ሉቃስ 22÷20. ኤር. 31÷31

↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣2⃣. እንደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት ሁለት  ጥንዶች ሲጋቡ የሚደረግላቸው ሥርዓት…………መጽሐፍም…….በመባል ይታወቃል??

#መልስ፦ ስርዓተ ተክሊልና መጽሐፈ ተክሊል።


↪ጥ.ተራ.ቁ.✍1⃣3⃣እግዚአብሔር ዓለማትን የፈጠረው በስንት ነገር ነው ?ምን ?ምን ናቸው?

#መልስ፦ በዝምታ፣ በመናገር፣ እና በተግባር ነው። ለምሳሌ፦ መላእክትን በዝምታ፣ ፀሐይና ጨረቃን በመናገር፣ሰውን በተግባር ።

↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣4⃣.እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምሮ አዳምና ሔዋን ሲፈጠሩ የስንት ዓመት እድሜ ነበሩ?

#መልስ፦ አዳም የ30 ሄዋን የ15 ዕድሜ ።

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍1⃣5⃣ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን ሦስት ፣ ሦስት ሲሆን አንድ ነው፡፡ ለመሆኑ አንድነቱ በምን በምን ነው? ሦስትነቱስ?

#መልስ፦ አንድነቱ በመለኮት፣በአገዛዝ፣በሥልጣን፣በፈቃድ።
ሦስትነቱ፦በስም፣በአካል፣በግብር ነው።

↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣6⃣ በአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ላይ በተለይ በማቴዎስ ወንጌል ላይ የአብ ፣ የወልድ፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ስም በግልጽ የተጠቀሰው በየትኛው ምዕራፍና ቁጥር ላይ ነው?

#መልስ፦ በማቴዎስ ወንጌል ም.28፥19 ላይ ይገኛል።


↪ጥ.ተራ.ቁ✍1⃣7⃣እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ የተባሉት ምን ምን ናቸው? ከሦስቱ የትኛው ይበልጣል? ምዕራፍና ቁጥሩስ?

#መልስ፦ እምነት፣ተስፋ ፍቅር ጸንተው ይኖራሉ ከሁሉም ፍቅር ይበልጣል። 1ኛ፦ቆሮ 13፥13

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍1⃣8⃣. ነቢዩ ኤርሚያስ ከትንቢተ ኤርሚያስ በኋላ የፃፋቸው 2 መጽሐፍት ምን እና ምን ናቸው ? ትርጓሜያቸውስ?

#መልስ፡- ሰቆቃው ኤርሚያስ / የኤርሚያስ ልቅሶ ወይም ሙሾ/ ማለት ነው፡፡ ተረፈ ኤርሚያስ / ከኤርሚያስ የተረፈ ማለት ነው/፡፡

↪ጥ.ተራ.ቁ.✍1⃣9⃣ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ነገሮችን ያመለክታል ለመሆኑ እነዚህ 3 ነገሮች ምን ምን ናቸው?

#መልስ- 1. ሕንጻው እራሱ ፣2. የክርስቲያኖች ህብረት፣ 3.አንድ አማኝ ብቻውን፡፡

↪ጥ.ተራ.ቁ✍2⃣0⃣. ሳይወለድ የሞተው ወይም ወደመቃብር የወረደው ብቸኛው ሰው ማን ነው??

#መልስ፦ አዳም ነው። ተፈጠረ እንጅ አልተልለደም።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ/ን  ጥያቄና መልሶች የሚተላለፉበት ቻናል

 አስተያየት👇
@saramareyamesara mareyama.890@gmail.com
.
https://t.me/joinchat/AAAAAExg87tr37X8VNFEjA



ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...