2018 ጁላይ 3, ማክሰኞ

መንፈሳዊ የእንቆቅልሽ/ህ መረሀ ግብር

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን፫
🌹🌹🌹🌹
እንቆቅልሽ
🌹🌹🌹🌹
👉ምናውቅልሽ

፩///የሰራዊት ጌታን ከፊት አስቀድሞ
መሳሪያ ሳይኖርው እንዲሁ በባዶ
ኃያልነኝ ያለውን በራስ ተመክቶ
ያሸነፈው ማነው  በጠጠር ወርውሮ❓
       
✅ የህዝቡን መርበሽ የንጉሱን ጩኽት
ሲሰማና ሲያይ ሳለ በእረኝነት
የአባቶቹን አምላክ በጸሎት ለምኖ
እደሚያሸንፍም በእግዚአብሔር ተማምኖ
ለሐገር ያስቸገረን ጎልያድን የጣለው
ያትንሽ ብላቴና ቅዱስ ዳዊት ነው።

፪// የተመርጡትን ቅዱሳን ሲያሳድድ
አምላክን ሳይፈራ ድሀን ሲጨፈጭፍ
የበደሉ ብዛት ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ
ጌታም ሊመልሰው አመጣበት መቅሰፍት
በደማርቆስ ተራራ አታሰደኝ ብሎ ጌታ የገሰጸው ማነንነው❓

✅ የጌታ ምርጥ እቃ ተብሎ የተጠራው
አምላኩን በጽናት ሁኖ የተከተለው
ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ መሰእዋት የሆነው
ከአይሁድ ወገን የሆነ  ጳውሎስ ነው።

///፩ ስልጣን አለኝ ብለህ በራስህ አትኩራ
ብሎ የገሰጸው ንጉሱን ሳይፈራ
ፈጣሪን እሚያሳዝን ስራን እዳሰራ
የወንድምህን ሚስት በፍጹም አታግባ
ጌታ ይጠራሀል እባክህ ቃሌን ስማ
ያለው ቅዱስ ሐዋርያ ማነው❓


   ✅ ገና ከናቱ ማህጸን የተመርጠ
በዮወርዳኖስ ባህር ጌታን ያጠመቀ
ለፍጥርቱ ሁሉ ወንጌል የሰበከ
እራሱ ክርስቶስ የመሰከርለት
ቅዱስ ሐዋርያ መጥምቀ መለኮት
ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

፬//መስዋዕት ከፍዬ ለፍቅሬ
ሰባት አመት  ፍየሎች ጠብቄ
ነው የተገኘች ሄዋን አጋሬ

እኔ ማነኝ
✅ ለእስራኤል አባት የሆንኩ ድንቅ ታሪካቸው
በመፃፍ ተከትቤ እስከዛሬ ያለው
እኔ ነኝ ያእቆብ የራሄል ባለቤት
የ አስራሁለቱ ነገድ የዮሴፍ አባት

፭//በብልሃቴ ተጠቅሜ
አምኖንን ከፉ ምክር በመምከሬ
እህቱን እዲያሰነውራት ያደረግኩ
እርሱንም ለሞት የዳረኩ
እኔ ማነኝ

✅አቢናዳብ 2ኛ ሳሙ 13:1-34


፮//የሰባ ሰገልን ስጦታ
በግብጽ የስደት ቦታ፤
አብረን ሳለን ካንዱ ጓዴ
የቀማሁኝ  ወንበዴ፤
ወርቁን ጫማ በመውሰዴ
ተጸጽቼ ባብቶ ሆዴ፤
 መለስኩኝ በፈቃዴ።

እኔ ማነኝ
✅ ይህንን ውለታ ጌታዬ አስቦ
በትንሽ ትልቁ እንደሰው አድጎ
በመስቀል ላይ በዋለ ጊዜ ዓለማውን ፈፅሞ
በዚያ በቀራንዮም ጎልጎታ
አስበኝ አልኩት ለፅድቅ ቦታ
እደበደሌ ሳያይ ለመንግቱ የጠጠራኝ
የቀድሞው ወንበዴ የዛሬው ፊያታዊዘይማ ነኝ

፯// ስንጓዝ ያኔ በግብፅ በረሃ
አውርዶ የመገበን የሰማዩን መና
ከአለት አመንጭቶ ያጠጣን ውሃ
እዳያቃጥለን ፀሃይ ሀሩሩ
የጋረደን በክንፋ የተዋጋልን በሰይፉ
መኑ ከማከ የተባለው ብረሃናዊው መለአክ ማነው
✅ የአፎማያ እረዳት የባህራን ታዳጊ
በክንፎቹ ጥላ ወዳጁን ጠባቂ
ከእያሱ ጋር አብሮ ህዝቡን የመራ
እርሱ ነው ሚካኤል ሁሌ አብሮን የሚኖረው ሁሌ ከኛ ጋራ

፰/ ልዩ ስትሆን ከአለም
ከምድር ማር ከሰማይ ያም
ወስደው ሁለቱን ደምረው
ለስሟ ትርጓሜ የሰጧት
ይቺ ቅድስት ማናት

✅የጣፈጠች ከሁሉ በላይ
ብረሃኗ የሚልቅ ከጨረቃ ከፀሃይ
የወለደች አምላክ አዶናይ
ማርያም ናት።
@Teyakaenamels
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለ ወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
saramareyama.890@Gmail.Com

3 አስተያየቶች:

  1. እግዚአብሔር ፍፃሜአችኁን ያሳምረው በርቱ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  2. የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
    እነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.

    ምላሽ ይስጡሰርዝ
  3. እግዚአብሄር አገልግሎታቹ ይባርክላቹ

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...