ረቡዕ 25 ኤፕሪል 2018

የይሁዳ ጉዞ ጭውውት

የይሁዳ ጉዞ

ይሁዳ ሆይ ጉዞህ የሞት ሆኖብሃል
በንስሐ ታጥበህ ተመለስ ይልሃል
እድሜውን ጸጋውን አምላክህ ሰጥቶሃል
እውቀቱንም ቢሆን ከጌታ እግር ስር ብዙ ተምረሃል
ታዲያ መች ጠቀመህ ይህ ሁሉ ልፋትህ
ፍቅረ ነዋይ ዐይንህን አውሮብህ
ጉዞህ ፍጻሜው ሞት ነው ያውም የሞት ሞት
አሳልፈህ ስትሸጠው ውስጥህ ቢነድም በጸጸት
አልተመለስህም አልበቃህም ለንስሐ
ይልቅ ይህ ገንዘብ መውደድ አረገህ የመንፈስ ድሃ
ጌታህን ስትሸጥ በ30 ዲናር
ይህ እንዲመጣ አላወቅህም ነበር
የሰጠህን አትረፍርፎ ብዙ ጸጋ
አንተ ግን አቃለልከው አረከስከው ያለዋጋ
ይልቅ በምሴተ ሐሙስ ሚስጥር ተካፍለህ
ክቡሩን ቁርባን አብሮ መግቦህ
ምነዋ ታዲያ እርኩሱ መንፈስ አደረብህ
ታዘዝክለት ጌታህን ልትሸጥ ተስማማህ
ይሁዳ ያንተ ጉዞ የሞት ሞት ነው
የንስሐ እንባ ያላጠበ ያልጎበኘው
የገንዘብ ፍቅር አውሮት የህይወትን ምንጭ የናቀ
ከገዳዮቹ ተባብሮ ጌታውን በመሳም አሳልፎ የሰጠ
ጅማሬው አምሮ ነበር በክብር ከጌታ ጋር ሲመላለስ
ምን ዋጋ አለው ፍጻሜው ግን የሞት ሞት ነው ...
ያውም በገዛው መሬት የገዛ ደሙ ሲፈስ
የይሁዳ ጉዞ ምንም አልጠቀመው
ይልቅ ከእርስቱ ከዘላለም ቤቱ
ለይቶ አስቀረው እንዲሁ በከንቱ
ሁልጊዜ ይሁዳን ስንወቅስ ኖረናል
እኛስ ህይወታችን እንዴት እንደሆነ መች አስተውለናል
ከይሁዳ ከፍተን ጌታችን ስንት ጊዜ እኛስ ሸጠነዋል?
ውስጣችን እንመርምር ጉዟችንም ይቅና
የይሁዳ ጉዞ የሞት ሞት ነውና
እሱንም መውቀሱ አይጠቅመንምና
በንስሐ እንባ ከአምላክ ፊት ወድቀን
ስለ እናቱ ብሎ ስለቅዱሳን
እንደቸርነትህ ማረን ማረን እንበል
ለፍርድ የመጣ ለት በግራ እንዳንቆም
እንጽና በቤቱ እንኑር አአምላክ ጋር ፤
በህይወት መዝገብ ላይ ዘላለም ተጽፈን።
@tibebe11
@tibebe11
@tibebe11sara mareyama.890@gmail.com

1 አስተያየት:

  1. የመድኃኒት ንግድ ሥራዬን ለማስፋፋት በተጠቀምኩበት ብድር ለመርዳት ሚስተር ቤንጃን ከሚያስፈልጓቸው በላይ አልፈዋል ፡፡
    እነሱ ለመስራት ወዳጃዊ ፣ ባለሙያ እና ፍጹም ዕንቁዎች ነበሩ ፡፡ እኔ ለማነጋገር ብድር የሚፈልግን ማንኛውንም ሰው እመክራለሁ ፡፡ Lfdsloans@outlook.com.WhatsApp ... +19893943740.

    ምላሽ ይስጡሰርዝ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...