#አፊያ ሁሴን
#(ክፍል ፩)
#©ፀሐፊ ማራማዊት ገብረ መድሕን
_________________________
#እውነተኛ የህይወት ታሪክ ነው ተከታታይ ክፍል አለው #ተከታተሉ ለሁላችንም ትምህርት አለው
________________________
የሥራ መግቢያና መውጫ ሰዓት ላይ የአዲስ አበባ አውራ ጎዳናዎች የሚፈጥሩት ድባብ ሲበዛ አስደናቂ ነው፡፡ የታክሲ ግፊያና ወረፋው፣ የእግረኛ ጥድፊያው፣ የተሽከርካሪው መጨናነቅ፣ የታክሲ ረዳቶችና የተራ አስከባሪዎች እሰጥ አገባ...ምኑ ቅጡ፡፡ ዋና ዋና መንገዶችና አደባባዮች በየዕለቱ የዚህ ትዕይንት ማስተናገጃ መድረኮች ናቸው፡፡ ሜክሲኮ፣ ስታድየም፣ መገናኛ፣ ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፣ ቄራ፣ ሳሪስ..ወዘተ፡፡ ሁሉም ጠዋትና ማታ በሰው ጎርፍ ይጥለቀለቃሉ፡፡ እያንዳንዱ ተጓዥ እያንዳንዱ ተጣዳፊ የራሱ ዓላማ፣ ተልዕኮና ግብ አለው፡፡ በነፋስ እንደሚገፋ ጉም በከንቱ አይጓዝም፣ በዘፈቀደም አይናጥም፡፡ የየጎዳናውን ወፈ ሰማይ ሕዝብ ከአንድ ከፍታ ሥፍራ ሆኖ ቢመለከቱት ግን ከቅላዥ እንደሚፈላ ፍል ያለ አንዳች ምክንያት የሚርመሰመስ ይመስላል፡፡
እኔም የዚህ ግዙፍ ትርምስ አካል ሆኜ ሃያ ሁለት አደባባይ ጋር ወደሚገኘው ጎላጉል ታወር እጣደፋለሁ፡፡ ከቦሌ ብራስ አካባቢ የተሳፈርኩት የወዳጆች መኪና አደባባዩ ጋር ሊደርስ ትንሽ ሲቀረው ስላወረደኝ ጥቂት መንገድ በእግሬ መጓዝ ነበረብኝ፡፡ እናም መንገዱን ተሻግሬ የህንፃውን ሳይድ ያዝኩና ከመኪናው ትርምስ ወደ እግረኛው ትርምስ ተዛወርኩ፡፡ እግረኛው መንገድ ላይ የተነጠፉት ጡቦች ለቸኮለ ሰው አይሆኑም፡፡ የተዛነፈው አነጣጠፋቸው ለዓይን ካለመሳቡም በላይ አንዳንዶቹ ሲረግጧቸው ከሥር ያቋሩትን ጭቃ ሽቅብ ይረጫሉ፡፡ ነገረ ሥራቸው እንደ ኤሊ ወይም እንቁራሪት የሚተናኮላቸውን የሚከላከሉበት ሲስተም ያዳበሩ ነው የሚመስሉት፡፡ ስለሆነም እግርን ከእንቅፋት ልብስን ከጭቃ ለመጠበቅ በጥንቃቄ መራመድ ያስፈልግ ነበርና መሬት መሬት እያየሁ ስጓዝ ከአንድ ሰው ጋር ከመላተም ለጥቂት ተረፍኩ፡፡ ቀና ስል በሙሉ ጥቁር የሙስሊም አባያ ከላይ እስከ ታች የተሸፈነች ሴት ነበረች፡፡ sorry ብዬ ተቃራኒውን አቅጣጫ ስይዝ እርሷም ተመሳሳዩን አቅጣጫ ይዛ ኖሮ እንደገና ልንጋጭ ሆነ፣ በፍጥነት አቅጣጫ ለመለወጥ ስሞክርም እርሷም ያንኑ ስታደርግ ለ3ኛ ጊዜ ተገጣጠምን፡፡ ይሄኔ የሚታይ ፊት ባይኖራትም ወደፊቷ አቅጣጫ በፈገግታ እያየሁ ክንዷን ያዝ አድርጌ በጎን በኩል አልፌ ሄድኩ፡፡ ወዲያው ግን "ሜሪ" የሚል የማውቀው ድምፅ ተሰማኝና ዞርኩ፡፡ ባለ ጥቁር አባያዋ ሴት ወደ እኔ ዞራ ቆማለች፡፡ እንደፈገግሁ ጠጋ አልኩ፣ ሴቲቱ ከራሷ ጀምሮ ወደ ፊቷ የወረደውን ኒቃብ ወደ ላይ ስትገልጠው እጅግ በጣም ከማውቀው ፊት ጋር ተፋጠጥኩ፡፡ "እኔ አላምንም ... ኤፊ" ብዬ ተጠመጠምኩባት፡፡ አፊያ ነበረች፡፡ አፊያ ሁሴን፡፡ ልብሷ እንደ ልብ ለመተቃቀፍ አላመቸንም፡፡ ቢሆንም በጥልቅ ስሜት ተሳስመን ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ጥቂት ቆመን አወራን፡፡ መንገዴን የዘጋችብኝ አውቃ እንደሆነ እየሳቀች ነገረችኝ፡፡ ከብዙ ጊዜ አንዴ ሁሉም መንገደኛ ላይ የሚከሰተው ግጥምጥሞሽ እንደመሰለኝ እንጂ ፈፅሞ የኤፊ ተንኮል ይሆናል ብዬ አልጠበኩም አልኳት፡፡ በኋላ እኔ ወደ ሥራ እርሷ ወደ ሱቅ እንደምንሄድ ተነጋግረን፣ ስልክ ቁጥራችንን እንደ አዲስ ተለዋውጠን ሞቅ ባለ ሰላምታ ተሰነባበትን፡፡
አፊያን የማውቃት ባህዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ግቢ ውስጥ አንድ ዶርም የተጋራን ጊዜ ነው፡፡ ቀይ፣ ቆንጆና እጅግ የሚማርክ የጉንጭ ሥርጉዳት(ዲምፕል) ያላት ለግላጋ ልጅ ናት፡፡ ፍረሽ እያለን አንድ ዶርም ውስጥ ባንሆንም የመኝታ ክፍላችን አንድ ብሎክ ውስጥ ነበር፣ ክላሳችንም አንድ ነበርና በመጀመሪያ በዓይን መተያየት ቀጥሎ የአንገት ሰላምታ መለዋወጥ ጀመርን፡፡ በኋላ ግን አፊያ የክፍሉን ተማሪ ሁሉ በሳቅ ያፈረሰ አንድ አስደናቂ ነገር ፈፀመች፡፡ developmental economics የሚባል አንድ ኮርስ እንወስድ ነበር፡፡ የኮርሱ አስተማሪ በግሩፕ እንድንሰራው የሰጠንን ፕሮጀክት ሰርተን ያመጣን ቢሆንም ለአስተማሪውና ለተማሪዎች ገለፃ የማድረግ ግዴታ ነበረብን፡፡ አብዛኞቻችን በዕድሜ ለጋ ከመሆናችንም በላይ የእንግዳነት ጭንቀት (tension) የሚያንገላታን ነበርን፡፡ ይሁን እንጂ ሁለት ግሩፖች በጥሩ ብቃት ገለፃ አድርገው ተቀመጡ፡፡ ቀጣዩ አቅራቢ የእነ አፊያ ግሩፕ ነው፣ ስለሆነም ስድስቱ የግሩፑ አባላት ወጥተው በተማሪው ፊት ተደረደሩ፡፡ አፊያ ከአስተማሪው በተቃራኒ ያለውን የመጨረሻ መስመር ይዛ ቆመች፡፡ ፊትለፊቷ የተቀመጥነውን ተማሪዎች ላለማየት አንዴ ኮርኒሱን አንዴ ወለሉን ስታይ ቆየችና የገለፃ ተራዋ ሲቃረብ እግሯ ሁሉ መንቀጥቀጥ ጀመረ፡፡ መምህሩ "አፊያ ቀጥይ" ሲላት ወደ ኋላ በመዞር ጀርባዋን ለተማሪው በመስጠት ቆመች፡፡ ተማሪው ኳስ ጨዋታ ላይ ጎል ሲገባ የሚሰማውን ዓይነት የአድናቆት ጩኸት አሰማ፡፡ ሳቅና ሁካታው በረድ ሲል መምህሩ በቁጣም በማግባባትም ፊቷን ወደ ተማሪው መልሳ እንድታዞር ካደረጋት በኋላ "አይዞሽ ስምሽን ብቻ አስተዋውቀሽ ግቢ" አላት፡፡ እርሷ ግን መሬት መሬት እያየች እግሯ መንቀጥቀጡን ቀጠለ፡፡ አስተማሪው "በያ ስምሽንማ ንገሪን እንጂ" ሲላት እንደ ህፃን ልጅ በክንዷ አይኖቿን ሸፍና አንድ ጊዜ ለቅሶዋን ለቀቀችው፡፡ ያን ጊዜ የተፈጠረውን ሳቅና የተማሪውን ሁኔታ በቃላት መግለፅ ይቸግራል፡፡ መምህሩ ሆዱን ይዞ እየሳቀ የግሩፑን አባላት ይዘዋት እንዲገቡ እየገፋ "ግቡ...ግቡ...ግቡ" አለና በረንዳ ላይ ወጥቶ ሳቁን ለማቆም ይታገል ጀመር፡፡
ይህ ሁኔታ አፊያን በግቢው ውስጥ በአንዴ ታዋቂ አደረጋት፡፡ እስከ ብዙ ጊዜ ድረስ "ፕሬዘንቴሽን ላይ ያለቀሰችው ልጅ የቷ ናት?" እያሉ ዶርሟ ድረስ ሊያይዋት የሚመጡ በርካቶች ነበሩ፡፡ በዕለቱ መሬት መሬት እያየችና በገለፃ አባላቷ ታጅባ ወደ ዶርሟ ከገባች በኋላ ወደ ክፍሏ ሄጄ እቅፍ አድርጌ አሳሳኳት፣ አበረታታኋት፣ ሌሎች ተማሪዎችም ተጨምረው የኃይስኩልና የፕሪፕ ተመሳሳይ ገጠመኞችን እያነሳን ብዙ አወራን፡፡ አመሻሽ ላይ ጉዳዩ ለአፊያ መሳቀቂያ መሆኑ ቀርቶ መሳሳቂያ እስከመሆን ደረሰ፡፡ በዚህ ሁኔታ እኔና ኤፊ ይበልጥ እየተግባባን መጣን፡፡ ይባስ ብሎም አንደኛ ዓመት እንደጨረስን በተጫሩ ተማሪዎች የሚፈጠረውን ክፍተት ለመሙላት በሚደረግ ሽግሽግ መኝታዋ ወደ እኛ ዶርም ተዛወረ፡፡ ለአንድ ዓመት ከ 6 ወራት ያህልም አንድ ክፍል እየተማርን፣ አንድ መኝታ ክፍል እያደርንና አብረን እየዋልን የልብ ወዳጅ እስከመሆን ደረስን፡፡ ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ ልንመረቅ 6 ወር ሲቀረን አፊያ ተገቢውን ውጤት ማሟላት ተሳናትና ከዩኒቨርስቲው ተባረረች፡፡ ጥቂት ጊዜ ስንደዋወል ነበር፡፡ በኋላ ግን እምጥ ትግባ ስምጥ ሳይታወቅ ተሰወረች፡፡ ሞባይሏም ከአገልግሎት ውጭ ሆነ፡፡ ይኸው ከአራት ዓመታት በኋላ በዚህ ሥፍራና በዚህ ሁኔታ ተገናኘን፡፡
አፊያ አይነ ግቡ ከሆነው የተዋበ መልኳና ዲምፕሏ ባሻገር ሁልጊዜም ለመሳቅ የተዘጋጀ ገፅታ ይነበብባታል፡፡ ፈገግታ ሆቢዋ ነው ማለት ይቀላል፡፡ መጨናነቅ የማትወድ ፈሪና ድንጉጥም ናት፡፡ ቤተሰቦቿ ጠንከር ያለ የኢኮኖሚ አቅም ስላላቸው ከመሃላችን በየጊዜውና በርካታ ብር የሚላክላት እርሷ ናት፡፡ ስለሆነም ከዶርማችን ውስጥ አንድም ቀን ካፌ ሳትጋፋ ውጭ በመመገብ የግቢ ቆይታዋን ያጠናቀቀች ብቸኛ ልጅ እርሷ ነበረች፡፡ እንደ አብዛኛዎቹ ወገኖች እስልምናን ከቤተሰቦቿ የወረሰች፣ በዚያው ሥነ-ልቡናና የአኗኗር ዘይቤ ያደገች ሙስሊም ነች፡፡ ይሁን እንጂ ግቢ ከመጣች በኋላ አንድም ቀን ሂጃብ ወይም አባያ አድርጋ አይቼያት አላውቅም፡፡ ስትሰግድም አላየኋትም፡፡
አንድ ቀን ለምን እንዲህ እንደማታደርግ ጠይቄያት የሰጠችኝ መልስ ለብዙ ተከታታይ ውይይት መነሻ ሆነን፡፡ "ለምን ሂጃብና አባያ አትለብሽም?" ስላት "ወይ ሜሪዬ በይ ዝም በይ የእነርሱ ይበቃኛል" ብላ በግቢው ያሉ አንዳንድ ሙስሊሞች እስላማዊ አለባበስን ንቀሻል በሚል ትችትና ነቀፋ እንደሚያቀርቡባት ነገረችኝ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እጅግ ብዙ ውይይት አደረግን፡፡ ስለ አላህ፣ ስለ መሐመድ፣ ስለ ክርስቶስ፣ ስለ ቁራንና ሀዲሳት፣ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስለ ገነትና ሲኦል፣ ስለ መጨረሻው ዘመን፣ ስለ ሴቶች፣ ስለ አጽዋማት፣ ስለ ሕግጋት፣ ስለ ጋብቻ ... ብቻ ያላነሳነው ርዕስ አልነበረም፡፡ ውይይታችን የፍቅር ነበር፣ የጓደኝነት ጥላ ያጠላበት፣ በብዙ የሴትነት ምሥጢራት የታጀበ፣ በለዘብታ ቃል የሚደረግ፡፡ እውነት ለመናገር አፊያ ስለ እስልምና ምንም አታውቅም ማለት ይቻላል፡፡ ስለ ገዛ እምነቷ አብዛኛውን ነገር የምትሰማው ከእኔ ነበር፡፡ በምነግራት የቁራንና የሃዲሳት ዘገባዎች ብዙ ጊዜ ያለ ልክ ትገረማለች፡፡ አንዳንዴ ትስቃለች፡፡ አልፎ አልፎ ለማመን ትቸገራለች፡፡ የሚደንቀው ለማመን ያስቸገራትን ታሪክ ሁሉ በየብሬኩ ወደ ቤተሰብ ስትሄድ ጠይቃ እውነትነቱን አረጋግጣ እንዲያውም ተጨማሪ አስገራሚ ታሪክ ይዛ ትመለስ ነበር፡፡
ከአፊያ ጋር ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ብቻ አልነበረም የምናወራው፡፡ ስለ ቤተሰቦቻችን፣ ስለ አስተዳደጋችን፣ ስለ ጓደኞቻችን፣ ስለ ገጠመኞቻችን ስለምናወራ የልብ ጓደኛሞች ሆነናል፡፡ ስለሆነም አንዳንድ ጊዜ መንፈሳዊ ነገሮችን ለማንሳት ምናልባት አሰለቻት ወይም አስጨንቃት ይሆናል እያልኩ እሳቀቅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህ የእኔ ሥጋት ነበር እንጂ እርሷ እንደዚያ ተሰምቷት አያውቅም፡፡ እንዲያውም ወደ በኋላ ላይ የውይይት ርዕስ የምታነሳው እርሷ ሆና ነበር፡፡ ሁለት ሦሥት ጊዜ የግቢ ጉባዔያት ልዩ ፕሮግራሞች ላይ ወስጃታለሁ፣ በተዘጋጀ መንፈሳዊ ጉዞም ልክ እንደ እኛ ነጠላ በትእምርተ መስቀል አድርጋ የጣና ገዳማትን ጎብኝታለች፡፡ በእነዚህ ሁሉ ድርጊቶች ውስጥ ስትጠይቀኝ አጫጭር ማብራሪያ ከመስጠት በቀር ምንም አልላትም፡፡
ፈተና የጨረስን አንድ የሆነ ቀን ከሰዐት ላይ በየመኝታችን ሳለን መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች፡፡ ከሞባይሌ ላይ ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ 53ን አውጥቼ እንድታነብ ሰጠኋት፡፡ አንድ ጊዜ በሽምደዳ ተወጣችውና ቀና ብላ እያየችኝ "ምን?" አለች፡፡ ወዲያው የሆነ ነገር እንደረሳ ሰው "ቆይ ቆይ" አለችና ወደ ንባቡ ተመለሰች፡፡ ብዙ ቆየችበትና "ምንድነው ሜሪዬ?..ሲከብድ" አለች ፊቷን ክስክስ እያረገች፡፡ "አልገባሽም?" ስል ጠየኳት ስሜቷን ለማጥናት አተኩሬ እያየኋት፡፡ "አዎ...አምስት ስድስት ጊዜ አነበብኩት፡፡ ስለማን ነው የሚናገረው?" አለችና "ሲያሳዝን.." ስትል አከለች፡፡ ይህን ክፍል አንብቦ ተመሳሳይ ጥያቄ የተነሳበት አንድ ኢትዮጵያዊ እንደነበርና ከደቀመዛሙርቱ አንዱ በዝርዝር እንዳስረዳው ጠቅሼ ትንቢቱ ስለ ክርስቶስ የመስቀል መከራ እንደተነገረ ተረኩላት፡፡ ስዕላዊ በሆነ መልኩ የተገለፀውን የጌታን ስነ ስቅለት ከወንጌላት ላይ አነበብን፡፡ "እግዚአብሔር የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ" ሲል ምን ማለት እንደሆነ፣ "የደህንነታችን ተግሳፅ በእርሱ ላይ ነበረ" ሲልስ ምን ለማለት እንደፈለገ፣ "በእርሱ ቁስል እኛ ተፈወስን" የሚለው አገላለጥ ትርጓሜስ ምን እንደሆነ በምችለው መጠን ለማስረዳት ጣርኩ፡፡ አፊያ በፅሞና ነበር የምታደምጠኝ፡፡ ሁኔታዋ ልክ እናቱ ጣፋጭ ታሪክ እንደምትተርክለት ብላቴና ነበር የሚመስለው፡፡ ከዚህ በፊትም ስለ ክርስቶስ ብዙ አውርተናል፡፡
ከሳምንት በኋላ ከተማው ውስጥ ባለ አንድ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብለን ሳለ ድንገት "ሜሪዬ እኔ ኢየሱስን በጣም ነው የምወደው" አለችኝ፡፡ "እውነት?" አልኳትና "ኢሳን ማለትሽ ነው?" ስል ጠየኳት፡፡ በፍጥነት ከአፌ ነጠቅ አርጋ "አይይ...ኢየሱስን..የእናንተን ኢየሱስን" አለችኝ፡፡ እኔም "ኤፊዬ...ኢየሱስ የእኛ ብቻ አይደለም የዓለሙ ሁሉ ነው፣ የአንቺም ነው፣ የእናንተም ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያን የእኔ ብቻ ናት የሚል አለ? የለም፡፡ የእኔም የአንቺም የሁላችንም ናት፡፡ ክርስቶስ ደግሞ ከሀገር ይሰፋል፡፡ ፍቅሩና ምህረቱ ለዓለም ይበቃል ይተርፋልም፡፡ ልዩነቱ እኛ ክርስቶስን እናምነዋለን፣ እናንተ ግን አታምኑትም፡፡ እኛ ስለእኛ መከራ መቀበሉንና መሞቱን እንቀበላለን እናንተ ግን አትቀበሉም፡፡ ይህ ግን እውነታውን አይቀይረውም፡፡ "የማያምኑ ቢኖሩ አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት አያስቀርም" ተብሎ ስለተፃፈ ባታምኑትም እንኳ ስለ እናንተም ጭምር ዋጋ የመክፈሉን እውነት አይቀይረውም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ታማኝ ነውና፡፡ አለማመናችሁ ከህይወትና ከበረከት ውጭ እንዳያደርጋችሁ ግን ያስፈራል" አልኳት፡፡ በክርኗ የተመረኮዘችውን ጠረጴዛ አቀርቅራ ስትመለከት ቆየችና ድንገት "ህቅ..." ብላ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡ ሁኔታዋ ፈፅሞ ያልጠበኩት በመሆኑ በፍጥነት ለማረጋጋት ተሳነኝ፡፡ አቅፌ ባባብላትም በጄ አልል አለች፡፡ ትኩረት ሲበዛብን ሂሳብ ከፍዬ ይዣት ወጣሁና ቀጥታ በአቅራቢያችን ወደሚገኘው ሥላሴ ቤተክርስቲያን ሄድን፡፡ የቤተክርስቲያኑ አፀድ፣ በውስጡ ያለው ፀጥታና ግርማ ሲበዛ አስደናቂ ነው፡፡ ከሰው እይታ ራቅ ብለን አንድ ግዙፍ የፅድ ዛፍ ሥር ተቀመጥንና ፀጉሯን እያሻሸኋት "ኤፊ ቆንጆ... ምንድነው?" አልኳት፡፡ አይኖቿ በእንባ ደመና እየተሞሉ "በቃ ባዶነት ይሰማኛል..ባዶ የሆንኩ ነው የሚመስለኝ" ብላ ትከሻዬን ተንተርሳ ለቅሶዋን ቀጠለች፡፡ እስኪወጣላት ፀጥ አልኳት፣ እንባዋም መሬት እንደማይወድቅ አውቅ ነበር፡፡ ስትረጋጋ ጸሎት አንድ ላይ አደረግን፡፡ እስኪጨልምና ረሀብ እስኪሰማን ድረስ ብዙ ነገር ስናወራ ቆየን፡፡ ስለ ቤተሰቦቿ ስፋት፣ በዕውቀት ሳይሆን በልማድ ላይ ስለተመሰረተው የሃይማኖት አጥባቂነታቸው፣ ሴትን ስለሚጨቁነው አጠቃላይ ሃይማኖታዊ ባህል፣ አሁን እርሷ የሚሰማትን ስሜት ለማስተናገድ ያለባትን ሥጋትና ፍርሃት በዝርዝር አወራችኝ፡፡ እኔም በየመሀሉ ጌታ በወጀብና በአውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ እንዳለው፣ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ከቶ ወደ ውጭ እንደማያወጣቸው እየነገርኩ ሳፅናናት ቆየሁ፡፡ በመጨረሻም "አይዞሽ ኤፊዬ...አንቺ ከእግዚአብሔር መንግሥት የራቅሽ አይደለሽም፡፡ ይህ እንባሽ በክርስቶስ ፊት መድረሱ፣ በፍቅር ልቡም መታሰቡ አይቀርም፡፡ በሰማያዊው መንግስት ደግሞ የክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የጂሃዲስት ሚስት ወይም ወይን ጠጅ አሳላፊ ገረድ አትሆኚም" አልኳትና ተያይዘን ወጣን፡፡
ከዚህ ሁኔታ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ውጤት ተለጠፈና አፊያ አንደር(under) ሆነባት፡፡ supplementary exam ወስዳም ልታሟላ አልቻለችም፡፡ ግቢውን ለቃ መሄዷም ቁርጥ ሆነ፡፡ ያን ጊዜ እንደኔ አንጀቱ ያረረ አልነበረም፡፡ የጌታ ፈቃድ ይሁን ብሎ ዝም ከማለት ሌላ አማራጭ ስለሌለ በእንባ ተሰነባበትን፡፡ ልንመረቅ ጥቂት ቀናት እስኪቀረን ድረስ እንደዋወል ነበር፡፡ ስልኳም እርሷም እንደ ዋዛ ከተሰወሩ በኋላ አንድ ቀን እንደምትደውል ተሥፋ ሳደርግ ወራት ተቆጠሩ፣ ዓመታትም ተከተሉ፡፡ ምን ውጧት እንደጠፋች፣ አሁን ያለችበት ሁኔታስ ምን እንደሆነ የምጠይቅበትም የማውቅበትም ሌላ ዕድል በእጄና በፊቴ ላይ አለ፡፡ ምን ትለኝ ይሆን...? ለመደወል ያዘጋጀሁትን ቁጥሯን ተጫንኩት፣ ዘለግ ያለ የጥሪ ድምፅ አሰማ፡፡ ... (ይቀጥላል)
------------- ማርያማዊት ገብረመድኅን -------------
ይቀጥላልsaramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ