2017 ኦክቶበር 29, እሑድ

ድንግል ሆይ፤ ስደትሽ

https://youtu.be/SwwiaieJtD0

♥አጭር መነባንብ♥
////////////////////////

ድንግል ሆይ፤ ስደትሽ
እመብርሃን ሆይ የአምላክ እናት
ከልጅሽ ጋር ሆነሽ ወጣሽ ለስደት
ውሃ ጥም ረሀቡ የአሸዋው ግለት
ሳይገባሽ አየሽ ብዙ እንግልት።
ስቃይሽ ብዙ ነው የደረሰብሽ
በግብፅ በረሃ እንባ እያፈሰስሽ
ልጅሽን እንዳይገሉት አዝለሽው ሸሸሽ
በሄድሽበት ሁሉ ፊት እየነሱሽ
የአምላክ እናት ስትሆኝ ሰዎች ግን ጠሉሽ
ልባቸው ደንድኖ ጠላት አውሮት
በአንቺና በልጅሽ አበዙ እንግልት
የተዓምራት ጌታ ሁሉን እየቻለ
ከእናቱ ጋራ ስደት ተካፈለ

////////////////////////
አንች ሶሎሜ ሆይ እስኪ ተናገሪ
እንዴት እንደነበር ስለ ስደቱ አውሪ
////////////////

ሶሎሜ፦
ያኔማ እንዲህ ነበር ታሪኩ ይዘከር
ድንግል ልጇን አዝላ በግብፅ በረሃ
በየሰው ሁሉ ደጃፍ ስትል ተጠማሁኝ ውሃ።
ጠላት ቀድሞ በልባቸው ገብቶ
ያስነቅፋት ነበር አፋቸውን ከፍቶ
እንባዋ ይፈሳል ቆሞ አያውቅም ከቶ።
ልጄን ይገሉታል እያለች በፍርሃት
እንጓዝ ትላለች በረሃ በረሃ ዳገት ቁልቁለት
ተከታትሎ ሄሮድስ ልጇን እንዳይገልባት።
ከዓኗ እንደሰን ውሃ እንባዋ ይፈሳል
ልቧ በጥልቅ ሐዘን እጅጉን ተጨንቋል
የሄሮድስ ጭካኔ የሰዉ ክፋት
ከበረሃው ጋራ ብዙ አንገላታት
ግብፅ በረሃ ላይ ሲፈፀም ትንቢት
ወደምስራቅ ዞሮ ኢትዮጵያን አያት
በአምላክነቱ በእጁ ባረካት
ልጄ ሆይ ምንድናት ይህች ሀገር
ብላ ጠየቀችው ተገርማ ድንግል
እናቴ እኔና አንቺን ስትቀድስ እምትኖር
ቅድስት ሀገር  አለች ኢትዮጵያን  እምትባል
በደመና ተጭና ኢትዮጵያን ባረከች
አስራት አርጎ ሰጣት ድንግል ተደሰተች
ጌታ ሆኖ ሳለ የሰው ስጋ ለብሶ
ብዙ ተንገላታ ስለእኛ ዐብሶ
የነቢያትን ትንቢት ለመፈፀም ወዶ
ከሰማየ ሰማይ ከድንግል ተወልዶ
ለ42 አውርሃ በግብፅ ተሰዶ
ነጻ አወጣን አምላክ የሰውን ልጅ ወዶ።.
////////////
ድንግል ሆይ፤ በስደትሽ ስደታችንን ባሪኪልን አሜን፫

@ተፃፈ በትዝታ አስፋው

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...