#አፊያ #ሁሴን #ክፍል 5
#ማርያማዊት #ገብረ #መድኅን
አንባቢ #ገብረ #ሚካኤል
አፊያ ሁሴን (ክፍል ፭)
በዚህ ሁኔታ አምስት ወይም ስድስት አስጨናቂ ደቂቃዎች አለፉ፡፡ እኔም እንዳቀረቀርኩ እርሱም እንዳተኮረብኝ ያቺ ቀዥቃዣ ታናሽ እህቴ እየሮጠች፣ እየዘለለችና እየጮኸች ገባች፡፡ ኡፍ...እንዴት እንዳሳረፈችኝ አትጠይቂኝ፡፡ ሳሎኑ ውስጥ ረብቦ የነበረውን ቀፋፊ የዝምታ ጥላ በቅጽበት ገሰሰችው፡፡ "አባቢ.." ብላ ተጠመጠመችበት፡፡ እያገላበጠች እየሳመችው የቆጥ የማገሩን ለፈለፈች፡፡ ቀጥሎ ደግሞ "ኤፊ... ቆንጆዋ እህቴ" ብላ ለወራት ያልተያየን ይመስል ትስመኝ ጀመር፡፡ ነገረ ስራዋ እያሳቀኝ በቅጽበት ከገባሁበት የጭንቀት ማጥ ተመንጭቄ ወጣሁ፡፡ እርሷም አንዳንዴ ከአባቴ እግር ስር ምንጣፉ ላይ እንደገና ደግሞ ከጎኑ ሶፋው ላይ እየተቀመጠች፣ ሁመይድ ያወራልንን የተለያዩ ታሪኮች እየተረከች በወሬ ጠመደችው፡፡ በመሐል በመሐሉም "ኤፊ..የት ሀገር ነበር ያለን?" "ቁጥራቸው ሥንት ነበረ ያለን?" እያለች እንዳስታውሳት ትጠይቀኛለች፡፡ እኔም አንዳንዴ በምልክት አልፎ አልፎም በዝግታ ድምፅ ስነግራት ቆየሁ፡፡ አጋጣሚውም አባቴን በደንብ እንዳስተውለው ረዳኝ፡፡ ብርቱ ድካምና መታከት ይታይበታል፡፡ ፊቱ የገረጣ፣ ከሌላው ጊዜ ይልቅም የገረጀፈ መስሎ ታየኝ፡፡ ብቻችንን ሆነን እንኳን በድፍረት ሊያናግረኝ ሞራል ማጣቱ ሊያስደስተኝ ሲገባ ሆድ ሆዴን ይበላኝ ጀመር፡፡ የማስተናግደው ቅጥ አምባሩ የጠፋ ስሜት ለራሴም ግራ አጋብቶኛል፡፡ ያም ሆኖ አባቴን እንዲህ ሆኖ ከማየው ከእነ ኃይለኛነቱ፣ ከእነ አስፈሪነቱና ከእነ ቁጣው ብጋፈጠው ይሻለኝ ነበር፡፡
ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ዓርብ ምሽት ቤት ውስጥ ተሰብስበን ሳለ አባቴ ከሌላኛው ቤቱ ሆኖ ስልኬ ላይ ደወለልኝ፡፡ ተነስቼ ወደ ሌላ ክፍል ሄድኩና "አቤት አባቴ.." አልኩት፡፡ ነገ ከሰዓት እንደሚፈልገኝና አንድ ቦታ አብረን እንደምንሄድ ነገረኝ፡፡ እሺ ብዬ ስልኩን ከዘጋሁ በኋላ በልዩ ልዩ ሃሳብ ተጠመድኩ፡፡ ራት ሲበላም ሆነ ቤተሰቡ ሲያወካ መሃላቸው የነበረው አካሌ ብቻ ነበር፡፡ የት ሊወስደኝ እንደሚችል በፍፁም መገመት አልቻልኩም፡፡ ምናልባት ዋናው ሼኽ ጋር ሊወስደኝ ይሆን? ወይስ የኡለማዎች ሕብረት ከሚባሉ የሙስሊም ሊቃውንት ጋር ወስዶ ሊያጋትረኝ ነው? እያልኩ ሳውጠነጥን አመሸሁ፡፡ መቼም አባቴ ነው፣ ምንም ቢሆን ለክፉ ነገር አሳልፎ አይሰጠኝም እያልኩ ለሕሊናዬ ስነግረው ቆየሁ፡፡ የአሁኑን አያርገውና ለአባቴ ያለኝ ፍቅር፣ እርሱም ለእኔ ያለው ውዴታ ሌላ ሰው የሚቀናበት ነበር፡፡ ከምንም የሚሻለው ጸሎት ነው አልኩና ወደ ክፍሌ ገብቼ ያለ አቅሜ ረዥም የሚባል ጸሎት አደረግሁ፡፡ ጸሎቴ ስልት ያለው አልነበረም፡፡ ነገር ግን ልቤንም እምባዬንም በእግዚአብሔር ፊት አፈስ ነበር፡፡ መድኃኔዓለም እንዲጠብቀኝ፣ የአባቴንም ልብ እንዲያራራው፣ በማንም ፊት ብቆም ሞገስን እንዲሰጠኝ፣ የሰጠኝን ሰላምና እርጋታ እንዳይወስድብኝ፣ ያለሁት ቀናው መንገድ ላይ ከሆነ እንዲያፀናኝ፣ ተጣምሜ ከሆነ ደግሞ እንዲያስተካክለኝ ስወተውት አመሸሁ፡፡
በማግስቱ ለማንኛውም ብዬ አባቴ አንድ ቦታ እንሄዳለን ብሎ እንደቀጠረኝና 6 ሰዓት ላይ እንደሚመጣ ለእናቴ ነገርኳት፡፡ እንደጠበኩትም ጥቁር ኒሳን መኪናውን እያሽከረከረ መጣ፡፡ ከመኪኖቹ ውስጥ ለግብዣና በእርሱ ግምት ትላልቅ ወደሚባሉ ፕሮግራሞች ሲሄድ የሚመርጠው መኪና እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ እርሱ ደግሞ ሙሉ ነጭ የሙስሊም ቀሚስና ጥቁር ጫማ አድርጓል፡፡ እኔም የዚያን ዕለት ላስከፋው ስላልፈለኩ ፀጉሬን በነጭ ሻሽ ከሂጃብ አስተሳሰር ጋር በሚቀራረብ ሁኔታ አስሬ ሸፈንኩት፡፡ ረዘም ያለ ቀሚስና ክፍት ሹራብ አድርጌ ለመሄድ ተሰናዳሁ፡፡ ግቢው ውስጥ እንደቆመ እናቴ በሥጋት "ወዴት ነው የምትሄዱት?" ስትል ጠየቀችው፡፡ የመኪናውን ጎማ በእግሩ ረገጥ ረገጥ እያደረገ "አንድ ቦታ ደርሰን እንመጣለን" ሲል መለሰላትና ወደ እኔ ዞሮ "እንሂድ" አለኝ፡፡ "እሺ" ብዬ ሞባይሌን ለማምጣት ወደ ቤት ገባሁ፡፡ በዚያች ቅፅበት ባልሰማቸውም ከእናቴ ጋር አንድ ሁለት ቃላት ተለዋውጠዋል፡፡ ግቢውን ለቀን እንደወጣን የመገረም ገፅታ እያሳየ "እናትሽ አንዳንድ ጊዜ አባትሽ መሆኔን ትዘነጋዋለች መሰለኝ" አለኝ፡፡ ምንም ልል ስላልቻልኩ ፀጥ አልኩኝ፡፡ ወደየት እንደምንሄድ እንኳ ልጠይቀው አልሞከርኩም፡፡ ከአባቴ ጋር እንዲህ ተቀራርበን ከተቀመጥን አንድ ዓመት አልፎናል፡፡ ለወትሮው የተለያዩ ሥፍራዎች አብሬው ለመሄድ ከልጆቹ ሁሉ ተመራጯ እኔ ነበርኩ፡፡ በእርሱ በኩል ባለው መስኮት ወደ ውጭ የማይ አስመስዬ ሰረቅ አድርጌ አየሁት፡፡ የአባትነት ርኅራኄና ላሕይ ገፅታውን አልብሶት ያየሁት መሰለኝ፡፡ ውስጤ በማላውቀው ስሜት ርብሽብሽ አለና እንባዬ በአይኖቼ ግጥም አለ፡፡ እንባዬ እንዳይታይ ከፍተኛ ትንቅንቅ ባደርግም አልተሳካልኝም፡፡ ላፍነው በጣርኩ ቁጥር ይበልጥ ገነፈለና ቀሚሴ ላይ ዱብ ዱብ አለ፡፡ ገልመጥ ብሎ አየኝና በፀጥታ ማሸከረከሩን ቀጠለ፡፡
ብሥራተ ገብርኤል አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታችን ተነስተን ሜክሲኮንና መስቀል አደባባይን ስናቋርጥ ወደየት ይዞኝ እንደሚሄድ ግራ ተጋባሁ፡፡ ወዲያው ግን ወደ ግራ ታጥፎ የአራት ኪሎን መንገድ ያዘና ብዙም ሳይቆይ ወደ ቀኝ በመጠምዘዝ አዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በር ላይ ገጭ አለ፡፡ ፍተሻውን አልፈን ወደ ውስጥ ዘለቅን፡፡ ከመኪና ወርደን ወደ ምግብ ቤቱ አዳራሽ ስንሄድና እየተመገብን ሁሉ አባቴ አንዳች ዘና የማለት ስሜት አደረበት መሰለኝ ስለ ሥራ፣ ስለ ንግድ እንቅስቃሴውና ማህበራዊ ጉዳዮች ሲያወራኝ ቆየ፡፡ ከአሁን አሁን የሆነ የቀጠረው ሰው ይመጣ ይሆናል ብዬ ብጠባበቅም ብቅ የሚል ሰው አልነበረም፡፡ ከምግቡ በኋላ ወደ መናፈሻው ሥፍራ ወጥተን እኔ ስፕራይት እርሱ ውሃ ይዘን ተቀመጥን፡፡ ወደ ጉዳዩ ለመግባት ነው መሰለኝ ፊት ለፊቴ ሆኖ ትኩር ብሎ ሲያየኝ አይኖቼ እንደገና በእንባ ተሞሉ፡፡ በዕለቱ እንባዬን መቆጣጠር ለእኔ በአየር ላይ የመንሳፈፍ ያህል ፍፁም የማይቻል ነገር ሆነብኝ፡፡ ትናንት ምሽት ጌታ ሞገስን እንዲሰጠኝ አጥብቄ ለምኜ ነበር፡፡ ነገር ግን በዕለቱ ከአባቴ ጋር ባለኝ ቆይታ ስነፈርቅ ነበር የዋልኩት፡፡ የተመጠኑ ንግግሮቼም በሳግ የተቆራረጡ ነበሩ፡፡ ለምን ሆደ ባሻ እንደሆንኩና በሆነው ባልሆነው ስለምን እንባ እንደሚቀድመኝ ፈፅሞ ሊገባኝ አልቻለም፡፡ አባቴ ቢቸግረው ከፊት ለፊቴ ወደ ጎኔ ተዛወረና አቅፎ ሊያባብለኝ ሞከረ፡፡ በእጆቹ እንባዬን ሲጠርግልኝም ይባስ ፈነቀለኝና እጁን ይዤ እየተንሰቀሰቅሁ አለቀስሁ፡፡ እርሱም ጎንበስ ብሎ "ልጄ ዛሬ እዚህ ይዤሽ የመጣሁት ልሰማሽ ስለፈለግሁ ነው፡፡ አውቃለሁ ተናድጄ ከመቆጣት በቀር እንደ አባት ሃሳብሽን የመስማት ዕድል አልሰጠሁሽም፡፡ አሁን ችግርም ካለብሽ እንደ አባትና ልጅ እንድናወራ ነው የምፈልገው...ተረጋጊ" አለና በቀልድ መልክ ገፋ አድርጎኝ ተነሳ፡፡
አጠገቤ ወዲያ ወዲህ ሲንጎራደድ ቆየ፡፡ እኔም ቢቸግረኝ "ጌታ ሆይ እባክህ እርዳኝ" እያልኩ እንባዬን ለማቆም ታገልኩ፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ እንደምንም ለቅሶዬን ገትቼና ፊቴን ጠራርጌ ቀና ብዬ ተቀመጥኩ፡፡ እርሱም ጥቂት ከተንጎራደደ በኋላ እንደ ቀድሞው ፊት ለፊቴ ተቀመጠ፡፡ "ልጄ ምንድነው የገጠመሽ ችግር? ምንድነው የሚያስጨንቅሽ? ንገሪኝ እስቲ፣ እኔ አባትሽ ነኝ" አለኝ፡፡ "እኔ ምንም ችግር የለብኝም፡፡ የሚያስጨንቀኝ ነገርም ከባለፈው ሕመሜ ጋር አልፏል፡፡ እንደውም እንደ አሁኑ ሰላም ተሰምቶኝ አያውቅም" አልኩት ጠረጴዛውን እያየሁ፡፡ "ቆይ እስቲ በደንብ ግልፅ ሁኚልኝ..ክርስቲያን የወንድ ጓደኛ ይዘሻል?፣ ፍቅር ይዞሻል? ንገሪኝ አይዞሽ" "አይ እንደርሱ አይደለም አባቢ" "ታዲያ ምንድነው? ካልነገርሽኝ እንዴት ልረዳሽ እችላለሁ?" ስንባባል ቆየን፡፡ እንደምንም አቅሜን አሰባስቤ "ቆይ አባቢ.. እኔና አንተ በሃሳብ ተለያይተን አባትና ልጅ መሆን አንችልም?" ስል ጠየኩት፡፡ "ለምን አንችልም?" አለኝ ከአፌ ላይ ነጥቆ፡፡ "ሁሉ ሰው መጠኑ ይለያይ እንጂ በሃሳብ ይለያያል፡፡ አባትና ልጅ ስለተዋለዱ ብቻ በሁሉ ነገር አንድ ዓይነት አስተሳሰብ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ስለዚህ ይሄ የልዩነት ምክንያት በፍፁም አይሆንም" አለኝ፡፡ "ታዲያ..." ብዬ ልል የፈለኩትን አንጠልጥዬ ተውኩትና አየሁት፡፡ ንግግሬን ያልጨረስኩት አውቄ ነበር፡፡ እርሱም ለማለት የፈለኩት እንደገባው ያስታውቃል፡፡ ወደ እኔ አንገቱን ሰገግ አድርጎ "ይኸውልሽ አፊያ..እኛ ሙስሊሞች ነን፡፡ እስልምናን ከሃይማኖቶች ሁሉ መርጦ የሰጠን አላህ ነው፡፡ እናም ሙስሊም መሆን በራሱ ትልቅ ዕድልና መመረጥ ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው በእስልምና ውስጥ መኖር በእስልምና ውስጥ መሞት ነው፡፡ ይሄ አስተሳሰብ ሳይሆን እምነት ነው" አለኝ፡፡ እያንዳንዱ እምነት አስተሳሰብ ላይ እንደሚመሰረት ግልፅ ነው፡፡ ፈጣሪ አንድ ነው ወይም አምላክ ሁሉን ቻይ ነው ብሎ ለማመን አስቀድሞ ይህንኑ ነገር ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ይሄ የታወቀ ነገር ቢሆንም በዚህ ጉዳይ ከአባቴ ጋር መሟገት ጥቅሙ አልታይ ስላለኝ ተውኩት፡፡
"አንድ የደበቅሽኝ ነገር አለ፡፡ እዚያ ዩኒቨርሲቲ እያለሽ አዕምሮሽን የበረዘ ክርስቲያን የወንድ ጓደኛ እንዳለሽ ነው የምገምተው" ብሎ ቅድም ያነሳውን ሃሳብ ደገመው፡፡ "አይ...እንደርሱ አታስብ አባቢ፡፡ እኔ የወንድ ጓደኛ የሚባል ነገር የለኝም" አልኩት ጠንከር አድርጌ፡፡ እርሱም "ታዲያ ምንድነው ችግሩ? ያደግሽበትን ሃይማኖት ገሸሽ እንድታደርጊ የሚገፋሽ ችግር ምንድነው?" ሲል ጠየቀኝ ጠበቅ አድርጎ፡፡ እንዴት እንደሆነ ሳላውቅ "ችግር እንኳ አይደለም... ነገር ግን እኔ ኢየሱስን እጅግ በጣም እወደዋለሁ" አልኩት፡፡ ትኩር ብሎ ሲያየኝ ቆየና "ታዲያ ይሄ ምን ችግር አለው? እኛ ሙስሊሞችስ እንወደው የለ እንዴ፣ ኢሣ (አለህይ ሰላም) የተከበረ የአላህ መልዕክተኛ እኮ ነው፡፡ እንደውም የእኛን ያህል የሚወደው የለም" አለ፡፡ የንግግሩ ቃና ከአባትነት ወደ መምህርነት ያዘነበለ መሰለ፡፡ "እኔ ግን ያልኩህ ቁራን ላይ ስለተጠቀሰው ኢሣ ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰበከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡ ወይም ደግሞ መድኃኔዓለምን ማለቴ ነው" አልኩት ግልፅ ለማድረግ ፈልጌ፡፡ "ሃ ሃ ሃ ሃ ሃ አይ የልጅ ነገር" ብሎ ሳቀና "አንድ ናቸው እኮ፡፡ ክርስቲያኖች ኢየሱስ የሚሉትና እኛ ኢሣ የምንለው አንድ ሰው እኮ ነው፣ የስም ልዩነት ብቻ ነው" አለኝ፡፡ ንግግሩ ከልቡ እንደሆነ ያስታውቃል፡፡
ቀስ ብዬ "አባቢ..መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለው ኢየሱስ የተወለደው በረት ውስጥ ነው፣ የቁራኑ ኢሣ ደግሞ ከቴምር ዛፍ በታች እንደተወለደ ተፅፏል፡፡ እሺ ይሄ ብዙ ችግር አይኖረውም እንበል፡፡ የክርስቲያኖቹ ኢየሱስ ተጠምቋል፣ ኢሣ ግን አልተጠመቀም፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ መዳን መከራ ተቀብሏል በመስቀል ላይም ተሰቅሏል፣ የቁራኑ ኢሣን ግን ጫፉን የነካው የለም፡፡ ክርስቶስ ስለ ሰዎች ሲል ሞቷል በ3ኛው ቀንም ተነስቷል፣ ኢሣን ግን አላህ ስላነሳው አልሞተም፡፡ ክርስቲያኖችና መጽሐፋቸው እንደሚሉት ኢየሱስ ሰው ብቻ ሳይሆን ጌታና አምላክም ነው፣ ኢሣ ግን ነቢይና ባሪያ ብቻ ነው፡፡ ኢየሱስ ከማርያም ከመወለዱ በፊትም በሰማያት እንደነበረ ተናግሯል፣ ኢሣ ግን እንደማንኛውም ሰው ከመሬም ሲወለድ ነው ሕልውናው የሚጀምረው፡፡ አባቢ...ታዲያ አንድ ሰው በአንድ ጊዜ እንዴት የተጠመቀም ያልተጠመቀም፣ የተሰቀለም ያልተሰቀለም፣ ሞቶ የተነሳም ያልሞተም፣ አስቀድሞ የነበረም በኋላ የመጣም ሊሆን ይችላል?" አልኩት፡፡ ድንቅ እያለው አገጩን በቀኝ እጁ ደግፎ "እሺ...!" አለኝ ንግግሩን ጎተት እያደረገ፡፡ በሙሉ ዓይኔ ላየው ብፈራም የ"ቀጥይ" ፈቃድ ስለሰጠኝ ጨክኜ ቀጠልኩበት፡፡ "ስለዚህ ትክክል ሊሆን የሚችለው የግድ አንዱ ብቻ ነው፡፡ አንዱ እውነት ሲሆን ሌላው ሐሰት ይሆናል፡፡ አንዱ እውን ሲሆን ሌላው ሕልም፣ አንዱ ተጨባጭ ሲሆን ሌላው ምናብ መሆኑ አይቀርም" ብዬ ቀና አልኩ፡፡ የሚያየኝ መስሎኝ መሬት መሬቱን እየተመለከትኩ ላውራ እንጂ እርሱም ለካ ቁልቁል ጠረጴዛው ላይ አፍጦ ኖሯል፡፡
ትክዝ ብሎ ቆየና "ይሄን ሁሉ ነገር ከየት አገኘሽው?" ሲል ጠየቀኝ ዓይኖቹን ቦዘዝ አርጎ እየተመለከተኝ፡፡ መሬት መሬት እያየሁ ፀጥ አልኩት፡፡ "አንቺ እኮ ሙስሊም ነሽ፡፡ መስማት ያለብሽ አላህና መልዕክተኛውን ብቻ ነው፡፡ በካፊር ትምህርት ልብሽን እየሞላሽ ነው የምትቸገሪው" አለኝ፡፡ በፊቴ የተቀመጠው አባቴ ባይሆን ኖሮ ለዚህ ንግግሩ ተገቢ ምላሽ በሰጠሁ ነበር፡፡ ነገር ግን የልቤ ምኞት ከአባቴ ጋር ሳንጣላ ሃሳቤን እንዲረዳልኝ ስለነበር ይህንንም አስተያየቱን በዝምታ አለፍኩት፡፡ ዝም ባልኩ ቁጥር ንግግሮቹ እየጠነከሩ፣ ፊቱ እየተኮሳተረ፣ እኔን ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ ትዕዛዝና መመሪያ መሳይ ነገር እያስተላለፈ መጣ፡፡ ነገሮች እኔ እንደምፈልገው የመሆናቸው ዕድል እጅግ በጣም ጠባብ መሆናቸውን ባውቅም እንደዚያ መሆን ስላልቻሉ እጅጉን ተከፋሁ፡፡ ወደማይቀረው ብርቱ ፀብና መከፋፋት ውስጥ እየገባን መስሎ ተሰማኝና ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ ከልጅነት ጀምሮ ከአባቴ ጋር የነበረንን ቅርበት፣ እንዴት ያቀብጠኝ እንደነበር፣ ወደ ካምፓስ በገባሁ ጊዜ እስክላመድ ድረስ በየሳምንቱ እየመጣ ያየኝ የነበረው ሁኔታ፣ እንደ ትልቅ ሰው ስለ ሥራው የሚያወያየኝ ነገር ሁሉ ለአፍታ በፊቴ ላይ እየተግተለተለ አለፈ፡፡ እርሱ ግን ወደ ሰሞኑ የጭከና ተግባሩ የተመለሰ መሰለ፡፡ ያመጣቸው የነበሩ ኡስታዞችን እንዳላከበርኩ፣ ከከሚል ጋር የገባሁትን እሰጥ አገባ፣ አላህና መልዕክተኛውን ለማቃለል እንዳላፈርኩ እየገለፀ በወቀሳ ይተገትገኝ ጀመር፡፡ ይህም አልበቃ ብሎት "ምን ያስነፈርቅሻል? ትሰሚያለሽ..ይህ የምታለቅሽውን ነገር እኔ ቅብጠት ነው የምለው፣ ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ ምንም አባትሽ ብሆንና የቱንም ያህል ብወድሽ እንደ ሙስሊምነቴ ከአላህና ከመልዕክተኛው በላይ ልወድሽ አልችልም፡፡ አንቺን ብቻ አይደለም ማናችሁንም ቢሆን ከአላህና ከመልዕክተኛው በላይ ላደርጋችሁ አልችልም" በማለት ጮኸ፡፡
እንዲህ ሲናገረኝ የሆነ ነገር መላ ሰውነቴን ነዘረኝ፡፡ እንደ መንቀጥቀጥም አረገኝና ተደፍቼ ከማለቅስበት ጠረጴዛ ቀና አልኩኝ፡፡ እልህና ሳግ ተናነቁኝ፡፡ ዓይኖቼ በእንባ ከንፈሮቼ በገዛ ጥርሴ ንክሻ ማበጥ ጀምረው ነበር፡፡ እንደስካሁኑ መሬት መሬት እያየሁ ሳይሆን ቀጥታ ዓይኖቼን ዓይኑ ላይ ተክዬ መናገር ጀመርኩ፡፡ "አባቢ...አንተ ልብህን ስታደምጥ እርሱ የሚነግርህንም ስታደርግ እኔስ የገዛ ልቤን ማዳመጥ የለብኝም? አንተና መሰሎችህ ልባችሁን ለገዛው ነገር ስትኖሩና ስትሞቱ እኔስ ነፍስና ሥጋዬን ለገዛው ነገር መኖርና መሞት አልችልም? የእናንተ ነፍስ ከእኔ ነፍስ በምን ይበልጣል? የልቤን ምክር ትቼ ሰው ባሰመረልኝ መስመር ለምን ብዬ እሄዳለሁ?? አላህና መልዕክተኛውን ከምንም በላይ መውደድ መብትህ ነው፡፡ እኔ አልተቃወምኩህም፡፡ እኔ ግን ልቤን በፍቅር ለሚገዛው እሰጣለሁ እንጂ በመመሪያና በትዕዛዝ አልወድምም አልጠላምም" ስል "ቆይ ተረጋጊ" ብሎ አቋረጠኝ፡፡ የሚንቀጠቀጥ ሰውነቴን፣ የአይኖቼንና የከንፈሬን ማበጥ፣ ከአንደበቴ የሚወጣውን የሰላ ቃል አስተውሎ እንደ መረበሽ ሳያረገው አልቀረም፡፡ ምናልባትም እንደገና ሊያመኝ መስሎትም ይሆናል፡፡ ረጋ እንደማለት ብሎ "አላህና መልዕክተኛውን ከምንም በላይ መውደድ ስህተት ነው የምትይው?" አለኝ፡፡ "አላውቅም" አልኩት በዚያው እልህ ውስጥ ሆኜ፡፡ "አላውቅም፡፡ እኔ ማንንም አልተቃወምኩም፡፡ ለእራሴ የማውቀው ግን እራሴ ነኝ፡፡ ልቤ ያመለከተኝን ነው የምከተለው፡፡ አላህና መልዕክተኛው የሚያሸነፍ ፍቅር ካላቸው ይሄ ሁሉ ዛቻና ማስፈራሪያ ምን ይሰራል? ልቤን ማሸነፍ፣ ከተቆጣጠረኝ ነገር ነፃ ማውጣት፣ ከሌላ ፍቅር መማረክ አይችሉምን?? ይሄ ሁሉ ተፅዕኖ ምን ይሰራል?? እኔ በተረዳሁት መጠን በክርስቶስ ፍቅር ተማርኬያለሁ...በግድ ሳይሆን በውለታው አስሮኛል" ብዬ ድምፄ እስኪሰማ ድረስ ማልቀሴን ቀጠልኩ፡፡
አባቴ ፍፁም ሌላ ሰው የሆንኩ ነው የመሰለው፡፡ በየመሐሉ "ተረጋጊ እንጂ" ይለኛል፡፡ እኔ ደግሞ በላይ በላዩ ሆድ ይብሰኛል፡፡ "ከዚያ ሁሉ ጭንቅ የታደገኝ ማነው? አዕምሮዬን ባጣሁ ጊዜ፣ መንደሩና ከተማው ሁሉ 'አፊያ አበደች' ብሎ ሲያወራ፣ ጨርቄን ልጥል ጥቂት ሲቀረኝ የደረሰልኝ ማነው? ያ ሁሉ ቁራን ሲቀራ፣ ያ ሁሉ ዱአ ሲደረግ አላህና መልዕክተኛው ደርሰውልኛል? አልደረሱልኝም፡፡ የደረሰልኝ የእማማ አፀደ መድኃኔዓለም ነው፡፡ አንተም ተሥፋ ስትቆርጥ ነው ወደ ጸበል የላከኝ፡፡ እርሳቸውም በአምላካቸው ተወራርደው ማዳኑን አሳይተውኛል፡፡ እና...እና...ለምን ብዬ ነው የነፍሴን ጌታና ባለውለታዬን ረግጬ የምሄደው?? ለምን አሁን በዚች ደቂቃ ድብን አልላትም..በሰው ጫናና ግፊት ልቤ ያመለከተኝን እውነት አልጥልም" አልኩ እየተንዘፈዘፍኩ፡፡ የሰውነቴን መንዘፍዘፍ ልቆጣጠረው አልቻልኩም፡፡ ትከሻዬ እስክስታ እንደሚመታ ሰው በየሰከንዱ ይነጥራል፡፡ የአባቴን ስሜት ማጥናት የምችልበት መረጋጋት ውስጥ አልነበርኩም፡፡ ብቻ ከፊት ለፊቴ ቆሞ በሥጋት ያስተውለኛል፡፡ እንባዬ እንደ አዲስ እየገነፈለና ሳግ እየተናነቀኝ "እኔ አሁን ሙሉ ሰው ነኝ፣ ላንተ ስምና ክብር እንዲሁም ለእናቴ ጭንቀት አስቤ እንጂ ብር ብዬ ወደሆነው ሥፍራ መጥፋት አያቅተኝም፡፡ የትም ቢሆን ለአንድ ራሴ አላንስም" ብዬ ጠረጴዛው ላይ ተደፍቼ መንዘፍዘፌን ቀጠልኩ፡፡ በዚህ ሁኔታ ምን ያህል እንደቆየን አላውቅም፡፡ ብቻ ባሻገር ከሚዝናኑ ሰዎች ውስጥ ሁለት ወጣቶች ወደ አባቴ ቀረብ ብለው "ችግር አለ ፋዘር? የምንረዳዎት ነገር ይኖራል?" ሲሉትና እርሱም "ምንም ችግር የለም ልጆች...አመሰግናለሁ" ሲል ተሰምቶኛል፡፡ ወዲያው ሂሳቦቹን ከፋፍሎ "ነይ ወደ ቤት እንሂድ በቃ" አለኝ፡፡ ዝም ስለው "አፊያ" ብሎ ጠንከር አርጎ ተጣራ፡፡ ቀስ ብዬ ተነስቼ ተከተልኩት፡፡
ወደ ቤት ስናመራ የለቅሶ ብዛት መሰለኝ ከባድ ራስ ምታት እያመመኝ ነበር፡፡ እየቆየሁ እየቆሁም በረዥሙ እየተነፈስኩ የሰቆቃ የሚመስል ድምፅ አሰማለሁ፡፡ አባቴ ቃል ሳይተነፍስ መኪናውን በከፍተኛ ፍጥነት ያሽከረክራል፡፡ መንገድ ላይ ከአንዴም ሁለቴ ከግጭት ለጥቂት ነው የተረፍነው፡፡ ዞር ብዬ ሳየው ፊቱ ተኮሳትሮ እጆቹ በጥቂቱ እንደመንቀጥቀጥ ያደርጋቸዋል፡፡ በሰላም እንድንገባ በልቤ መፀለይ ጀመርኩ፡፡ ቤት ስንደርስ ክላክሱን በረዥሙ አጮኸው፡፡ ወርጄ ለማንኳኳት ሊቃጣኝ ሲል ጥበቃው በሩን ከፈተና ገባን፡፡ ከመኪናው እንደወረድን እናቴ እያፈራረቀች እያየችን "ምን ሆናችኋል? ሁለታችሁም ልክ አትመስሉም" አለችኝ፡፡ ፀጥ ብዬ አልፌያት ሄድኩና ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡ ፊቴን ታጥቤ በመስታወት ሳየው ጥቂት ቆየሁና በደረቴ አልጋዬ ላይ ዥው ብዬ ወድቄ እንደተኛሁ "ኡ...! ወይኔ...ኡ..." የሚል የእህቴ ድምፅ ቤቱን ደባለቀው፡፡ ሮጬ ወደ ሳሎን ስደርስ አባቴ ሰውነቱ ግትርትር ብሎና አይኑን ወደ ግንባሩ ሰቅሎ ተንጋሏል፡፡ አረፋ መሳይ ነገርም በአንድ ጉንጩ በኩል ይኩረፈረፋል፡፡ ወዲያው እናቴ ሰራተኞች መጡና ቤቱ በጩኸት ድብልቅልቁ ወጣ፡፡ ወደ ቤት ስንገባ ከኤሌክትሪክ ሰራተኞች ጋር ሰርቪስ ቤቶቹ አካባቢ ያየሁት ታላቅ ወንድሜ ከእነ ሰራተኞቹ ገስግሶ መጥቶ አባቴን አፋፍሰው ወደ መኪና አስገቡት፡፡ ወንድሜ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቶ "ስትሮክ ነው ፍጠኑ፣ ስትሮክ ነው ፍጠኑ" ይላል፡፡ ወንድሜ የአባቴን መኪና እያሽከረከረ የኤሌክትሪክ ሰራተኞቹና ከሰራተኞቻችን አንዷ አባቴን ይዘውት ሄዱ፡፡ እኔ፣ እናቴና፣ እህቴ ደግሞ በሌላ መኪና ተከታትለን ወጣን፡፡ እህቴ ታለቅሳለች፡፡ እናቴም "ምን ሆናችሁ ነበር? ሲናደዱ ደም ግፊታቸው እንደሚነሳ እያወቅሽ ለምን አትታገሻቸውም? ምን ዓይነት መዓት ነው ዘንድሮ ቤቴ የገባው" እያለች በወቀሳ ትለበልበኝ ጀመር፡፡ በአንድ ፊት የአባቴ ሕመምና ሥጋት፣ በሌላ ጎን የሚከተለኝ ወቀሳና ዝልፊያ ታየኝና "አዬ መከራዬ.." ብዬ ጭንቅላቴን ይዤ የዋለብኝን ለቅሶ ቀጠልኩ፡፡
(ይቀጥላል)
------- ማርያማዊት ገብረመድኅን -------
saramareyama.890@gamail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ