#አፊያ #ሁሴን
#ክፍል 2
#እውነተኛ ታሪክ
#ፀሀፊ #ማርያማዊት #ገብረ #መድሕን
#አንባቢ #ገብረ #ሚካኤል
አፊያ ሁሴን (ክፍል ፪)
የስልኩ ጥሪ ጮኾ ጮኾ ሲያበቃ በዚያኛው ወገን የሚያነሳው ማጣቱን ገልፆ በራሱ ጊዜ ተዘጋ፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ደግሜ ብሞክርም ለውጥ አልነበረም፡፡ ዕለቱ ረዥምና አድካሚ ስብሰባ የማደርግበት ቀን በመሆኑ ቀልቤንም ዶክሜንቶቼንም ሰብስቤ ወደ ስብሰባው አዳራሽ ዘለቅሁ፡፡ በሻይ ብሬክም ሆነ በምሳ ሰዓት ስልኬን በደቂቃዎች ልዩነት ከቦርሳዬ እያወጣሁ መመልከቴን የታዘበችው ባልደረባዬ "ወንዶቻችን ዝንጋታ አብዝተዋል፣ ስልክ መደወልም ተዉ እኮ" ብላ እየሳቀች አቀፈችኝ፡፡ ለቀልዷ የፈገግታ አፀፋ ሰጥቼ ወደ ሃሳቤ ገባሁ፡፡ አፊያ ስልኬን ስታይ በፍጥነት እንደምትደውል ጠብቄ የነበረ ቢሆንም እስከ 8፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የውሃ ሽታ ሆነች፡፡ ከሰዓቱም ለውጥ ይዞ አልመጣም፡፡ ስልኬ በነዘረኝ ቁጥር እያወጣሁት ከሌሎች ስሞችና ቁጥሮች ጋር ከመፋጠጥ ያለፈ ነገር አልነበረም፡፡ አታካችና ረዥም የሆነብኝ ስብሰባ በግድም ቢሆን አለቀና ተበተንን፡፡ ከተለመደው የሥራ መውጫ ሰዓት የትራፊክ መጨናነቅ በኋላ አመሻሽ ላይ ወደ ቤቴ ገባሁ፡፡ ያልተለመደ ጥድፊያ ውስጥ ገብቼ ለምን እንደምዋከብ ለራሴ እንኳን አልገባኝም፡፡ እንደ ቸኮለ ሰው በፍጥነት ልብሴን ከቀየርኩ በኋላ ሞባይሌን ይዤ ተቀመጥኩ፡፡ ወደ አፊያ ለመደወል ስሟን ካወጣሁት በኋላ አንዳች ወቃሽ ስሜት ሕሊናዬን ጠቅ አደረገኝ፡፡ "ብቻሽን ነገሮችን አፍርሶ የመስራት አቅም ያለሽ ይመስል ይህ ሁሉ መጨናነቅና እርጋታ ማጣት ምን ይሉታል?" የሚል ቃል በአዕምሮዬ ጓዳ በፍጥነት ሲሯሯጥብኝ ተሰማኝ፡፡ ይሄኔ ስልኬን አልጋዬ ላይ ወርውሬ ነጠላዬን አነሳሁና ከቤታችን በቅርብ ርቀት ላይ ወደሚገኘው አጥቢያ ቤተክርስቲያን አመራሁ፡፡
ቤት ተመልሼ ስገባ ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ሊሆን ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ነበር የቀሩት፡፡ እንደ ዋዛ ጣል አድርጌ የወጣሁት ሞባይል 8 ሚስድ ኮል አቆየኝ፡፡ አምስቱ የአፊያ ሁሴን ነበሩ፡፡ የፈለጉኝን ስልኮች አይቼ ለኤፊ የመደወያው ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው በማለት ለመደወል እየነካካሁ ሳለ ስልኩ በድንገት ጠራና ንዝረቱ ብርግግ አረገኝ፡፡ በራሴ ድንጋጤ እንደፈገግሁ "ኤፊ.." የሚለውን ስም በሞባይሉ ስክሪን ላይ አየሁት፡፡ የሚታዘብ ቢኖር የጥሪ መዝሙሩን አዝማች ሰምቼ እስክጨርስ ስልኩን አለማንሳቴ የቀድሞውን ውክቢያዬን ለመበቀል ያደረኩት እንደሚመስል ጥርጥር አይኖረውም ነበር፡፡
"ክንድህን እጠፍ የሚልህ ማነው
ማዳንህን ተው የሚልህ ማነው
ቢከፋቸውም አሳዳጆቼ
እስካሁን አለሁ በአንተ ፀንቼ"
ስልኩን ሳነሳው ተስረቅራቂው የኤፊ ድምፅ "ሜሪዬ..!" አለ፡፡ ስደውልላት ስልክ ማንሳት የማትችልበት ሁኔታ ላይ እንደነበረችና ለመደወል ደግሞ ይበልጥ ነፃ የምትሆንበትን ጊዜ በመጠበቅ እንደዘገየች በሚለማመጥ ድምፅ ነገረችኝ፡፡ ከዚያም ስለ ሕይወት፣ ስለ ሥራና ትምህርት፣ ስለ ጓደኞቻችን፣ ስላለፈው ጊዜና መሰል ጉዳዮች በወፍ በረር ቅኝት ስናወጋ ቆየንና "ኤፊዬ ስለ ራስሽ እስቲ ንገሪኝ?" ስል ጠየኳት፡፡ "አይ ሜሪዬ የእኔ ነገርማ እንዲህ በዋዛ፣ በጥቂት ደቂቃዎችና ያውም በስልክ ተነግሮ የሚዘለቅ አይደለም፡፡ ቁጭ ብለን በእርጋታና በሰፊው እናወጋዋለን፡፡ ደግሞስ አልናፈቅሁሸም እንዴ? ልታገኚኝ አትፈልጊም??" አለችኝ፡፡ "ኧረ ኤፊ...ቀላል ናፍቀሽኛል እንዴ፣ በደንብ እንገናኛለን እንጂ፡፡ ከካምፓስ ከወጣሽ በኋላ ድንገት የተሰወርሽበት ሁኔታ እስካሁን እንቆቅልሽ ስለሆነብኝ ነው" አልኳት፡፡ "ታምሜ እኮ ነበር ሜሪዬ፣ መደዋወል ካቋረጥንበት ጊዜ ጀምሮ ለ8 ወራት ያህል አሞኝ ነበር፡፡ ይህ ብዙ የሚያስወራ ነው ሜሪቾ...ከዚያ ትንሽ እንደተሻለኝ ለአንድ የአረብ ዲቃላ በዚያም በዚህ ብለው ዳሩኝ፡፡ የ2 ዓመት ጎረምሳ አድርሻለሁ፡፡ ትዳር ከሚያሳሳ ልጄ ባሻገር አንድ አፓርታማ፣ አንዲት ያሪስና አንድ ቡቲክ አትርፎልኛል፡፡ ሌላውን ለጊዜው ሆድ ይፍጀው ብያለሁ" አለችኝ፡፡ ወዲያው ቀጠል አደረገችና "ስታዪኝ ግን ምን ተሰማሽ ሜሪዬ?" ስትል ጠየቀችኝ፡፡ "ደስታ ነዋ ኤፊዬ፣ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ መጀመሪያ እንደ መገረምም እንደ መደንገጥም አርጎኝ ነበር፡፡ በኋላ ግን እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ፡፡ እንደምወድሽ ታውቂያለሽ አይደል?"አልኳት፡፡ ከአፌ ላይ ነጠቅ አርጋ "አውቃለሁ ሜሪዬ አውቃለሁ፣ እንደምትወጂኝም በመገናኘታችን ደስ እንደሚልሽም አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ያልኩሽ በሙስሊሞች አባያ ተከናንቤ ስታይኝ ምን ተሰማሽ? ነው" አለችኝ፡፡ ፈጣን መልስ ለሚሹ ድንገተኛ ጥያቄዎች ብዙ ጊዜ ምላሽ የማይቸግረኝ እንደሆንኩ ብዙ ሰዎች ቢነግሩኝም ለኤፊ ጥያቄ ግን ወቅታዊ መልስ አጣሁለት፡፡ ስለሆነም ስንገናኝ በሰፊው እንደምናወራው ገልጬ ቅዳሜ ከሰዐት 22 ማዞሪያ የሚገኘው ሱቋ ውስጥ ተቀጣጠርንና የ15 ደቂቃ የስልክ ውይይታችን ተጠናቀቀ፡፡
ቀሪውን ምሽት በሙሉ ከአፊያ ሌላ ማሰብ ተሳነኝ፡፡ እንደ መርሳት ያደረኳት ጓደኛዬ ድንገት ተከስታ አዕምሮዬን ታመሳቅለው ጀመር፡፡ ቤተክርስቲያን ሄጄ ስመለስ ተረጋግቼ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ መልሼ የቀኑ ዓይነት ውል የለሽ ጭንቀትና ውክቢያ ውስጥ የገባሁ መሰለኝ፡፡ ግብታዊ በሚመስል አካሄድ የፎቶ አልበሞቼንና አልፎ አልፎ የምፅፋቸውን ዲያሪዎች ካኖርኩበት አውጥቼ አልጋዬ ላይ ሰፈርኩ፡፡ የፎቶና የዲያሪ ጥምረት በእርግጥም ከትዝታ የላቀ ኃይል አለው፡፡ የጊዜን ውስንነት፣ የቦታን ርቀት፣ የሁኔታዎችን መለዋወጥ ሁሉ ሽሮ በጊዜውና በሥፍራው ዳግመኛ የመገኘትን ያህል የሚያስመስል መግነጢሳዊ ኃይል ያላብሳል፡፡ ከኤፊ ጋርና ከሌሎች ጓደኞቻችን ጭምር ፎቶ ያልተነሳንበት ሥፍራ አልነበረም፡፡ ዶርም ውስጥ፣ መማሪያ ክላስ፣ ላይብራሪ፣ ጊቢው ውስጥ፣ ካፌ፣ በከተማው ጎዳናዎች፣ ቤተክርስቲያን፣ ጣና ሀይቅ፣ ጢስ አባይ ... በጣም ብዙ ቦታ፡፡ እያንዳንዱ ፎቶ የራሱን ትዝታ ይዞ ይመጣል፡፡ ዲያሪዎቼ ደግሞ ጥቃቅኑን ነገር ሁሉ ያስታውሱኛል፡፡ በተለይ ከኤፊ ጋር ያወራናቸውንና የተወያየንባቸውን ርዕሶች በትኩረት አነበብኳቸው፡፡ አፊያ በእርግጥም ለክርስቶስ መንግሥት እጅግ ተቃርባ ነበር፡፡ ከሕይወት ደጃፎች ለጥቂት ወደ ኋላ የተመለሰችበትን ሁኔታ እያሰብኩ በቁጭት እሳት እንደ አዲስ ተንገረገብኩ፡፡ ዓይኖቼ በንባብና ፎቶዎች በማየት አዕምሮዬ በሃሳብ ውጣ ውረድ ተዳከሙ መሰል በዚያው የሞት ታናሽ ወንድም ይዞኝ ጭልጥ አለ፡፡
ቅዳሜ የሚሉት ቀን እየተጎተተም ቢሆን ደረሰ፡፡ ሳምንቱን የአቅሜን ያህል በጸሎትም፣ በንባብም፣ በስነ ልቡናም ስዘጋጅበት ቆይቻለሁ፡፡ ኤፊም ፍቅር ያገረሸባት ይመስል አንድ ቀን እያለፈች ስትደውልልኝ ነበር፡፡ ዛሬም በጠዋት ደውላ ቀጠሮውን አስታውሳኝ ከ 6 ሰዓት ጀምራ እንደምትጠብቀኝ ነገረችኝ፡፡ እኔም 7፡00 ሰዓት ላይ እንደምደርስ ነግሪያት በሰዓቱ ተገኘሁ፡፡ የአፊያ ቡቲክ በአንድ ሕንጻ ምድር ቤት የሚገኝ ሲሆን ከጠበኩት በላይ ሰፊና ደረጃውን የጠበቀ ነበር፡፡ በውስጡ የሴቶች አልባሳት፣ ጫማዎችና ሽቶዎች በወጉ ተሰድረው፣ የተቀሩትም በቄንጠኛ ተሽከርካሪ መስቀያዎች ተንጠልጥለው ይታያሉ፡፡ የተዋበውን ቡቲክ፣ ልብሶቹን፣ ጫማዎቹንና ሽቶዎችን ተዟዙሬ ስመለከት ቆየሁ፡፡ ኤፊ ስለ አልባሳቱና ሽቶዎቹ ብራንድ፣ ስለሚመጡበት ሀገር፣ ስለ ዋጋቸውና ስላላቸው ተፈላጊነት አነስተኛ ገለፃ አደረገችልኝ፡፡ እጇን ትከሻዬ ላይ ጣል አድርጋ በበሩ አቅጣጫ ወደ ውጪ እያየች በጣቶቿ የሽጉጥ ቅርፅ ሰርታ ካመለከተች በኋላ "ይኸውልሽ ጓደኛዬ.. ተወዳጁ ባሌ የገዛልኝ መኪና" በማለት ከሱቁ ፊትለፊት የጎዳናውን ጠርዝ ይዛ የቆመችውን ያሪስ መኪና አሳየችኝ፡፡ አክት ባደረገችው ነገርና በንግግሯ እኔና የሽያጭ ሰራተኞቹ እየተያየን ሳቅን፡፡ ከዚያም ወደ ውስጠኛው ክፍል ተያይዘን ዘለቅን፡፡
እንደ ቢሮና እንግዳ መቀበያ የሚያገለግለው ክፍል አንድ ኮምፒዩተር፣ ጥቂት ወንበሮችና፣ አነስ ያለ የፋይል ማስቀመጫ መደርደሪያ ይዟል፡፡ በአንዱ ጥግ በኩል ደግሞ ለዛሬ ብቻ ይዘጋጅ ወይም የሁልጊዜ ሥፍራው ይሁን ባለውቅም ባማረ የአረቢያ መጅሊስ ላይ የተነጠፈ ሳሳ ያለ ፍራሽ አለ፡፡ በቀጣዩ ግድግዳ ደግሞ ወደ ሌላ ክፍል የሚወስድ የተዘጋ በር ሲኖር ክፍሉ ስቶር እንደሚሆን ገመትኩ፡፡ ከበሩ አጠገብ ባህላዊው የቡና ማፍያና መጠጫ ዕቃዎቻችን ተሽሞንሙነው ተቀምጠዋል፡፡ ዙሪያ ገባውን ቃኘሁና አንዱን ወንበር ስቤ እየተቀመጥሁ "ቢሮሽ ነው ቤትሽ ነው የጋበዝሽኝ?" ስል እየሳቅሁ ጠየኩ፡፡ ኤፊም "እንግዲህ እሱ ወንበር ላይ ከተቀመጥሽ በንግድና በቢዝነስ ጉዳዮች መደራደር እንጀምራለን ማለት ነው" አለችኝ ሳቋን ለማፈንና ቅጭም ለማለት እየሞከረች፡፡ "እንዴት..?" በሚል አስተያየት እንዳስተዋልኳት ተመልክታ "ምክንያቱም እኒህ ወንበሮች የሥራ አጋሮችና የአንዳንድ ቅርብ ደንበኞች መቀመጫ ሲሆን የወዳጆች ሥፍራ ያ ነው" ብላ የተነጠፈውን ፍራሽ አሳየችኝ፡፡ ተነስቼ ፍራሹ ላይ ተስተካክዬ ከተቀመጥኩ በኋላ ቆማ በፈገግታ የምታየኝን ኤፊን "አመሰግናለሁ የእኔ አክባሪ" አልኳት በሕንዶች የሰላምታ አሰጣጥ መዳፎቼን አነባብሬ፡፡ "ለዚህ መሬት ላይ ለሚነጠፍ ፍራሽ ሜሪዬ..? ያንቺ ሥፍራ እኮ እዚህ ውስጥ ነው የእኔ ውድ" አለችኝ ሌባ ጣቷን በቄንጥ ወደ ልቧ እያመለከተች፡፡ ወዲያውም "መጣሁ" ብላ ጣደፍ እያለች ወጣች፡፡
የአፊያ ቤተሰቦች የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት እንደሆኑ ባውቅም አሁን ደግሞ እርሷ "የእኔ" የምትለው ሀብትና ንብረት በአጭር ጊዜ ውስጥ አፍርታለች፡፡ በሀገራችን የኑሮ ደረጃ ሲታይ አብዛኞቹ እንስቶች የሚመኙት ዓይነት ሕይወትን በመምራት ላይም ትገኛለች፡፡ የማየው ነገር ሁሉ ቅምጥልነት የሞላበት ነበር፡፡ ጌታ የዘሪውን ምሳሌ ሲያስተምር ከተዘሩት ዘሮች አንዱ በእሾህ ላይ መውደቁንና እሾሁ ዘሩ ፍሬ እንዳይሰጥ እንዳነቀው በመግለጥ ተናግሮ ነበር፡፡ የሚዘራው ዘር የእግዚአብሔር ቃል ሲሆን እሾህ የተባለው ደግሞ የዚህ ዓለም ብልፅግናና ምቾት እንደሆነ የተረጎመውን አስቤ አንዳች የሥጋት ስሜት ወረር አደረገኝ፡፡ በአንፃሩ የአፊያ ደማቅ አቀባበልና በየምክንያቱ የምታሳየኝ ፍቅር እንደ መጽናኛ የሚታይ ነበር፡፡ ሦሥቱ የሽያጭ ሰራተኞች ሳይቀሩ አንዳች መመሪያ የተቀበሉ የሚያስመስል ልዩ እንክብካቤ ያደርጉልኝ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ አፊያ አሁን የባርነት ምልክት በሆነው ጥቁር መጋረጃ ቁጥጥር ውስጥ ናት፡፡ ባለ ባልና ባለ ልጅም ናት፡፡ ኑሮዋም በዋዛ ፊትን የሚያዞሩበት አይመስልም፡፡ ከዚህ ሁሉ የደቂቃዎች የሃሳብ ውጣ ውረድ በኋላ "እግዚአብሔር በወጀብና በአውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው" የሚለው ቃል ትዝ አለኝና ፈገግ አልኩኝ፡፡
ቀጥሎ አነስተኛ ድግስ የሚመስል ትዕይንት ተከተለ፡፡ በአቅራቢያው ከሚገኝ ትልቅ ሆቴል በትዕዛዝ ያስላከችውን የተለያዩ ምግቦች በሚገባ በለበሱ የሆቴሉ አስተናጋጆች መጥቶ ተደረደረ፡፡ ለስላሳና የታሸጉ ውሃዎችም ቀረቡ፡፡ ከብዙ ሳቅና ጨዋታ ጋር የሽያጭ ሰራተኞቹን ጨምሮ አንድ ላይ ምሳችንን በላን፡፡ ከሰራተኞቹ አንዷ የተዘጋጀውን ቡና ማፍላት ጀመረች፡፡ ቡናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ገጠመኞችና ትዝታዎች እየተነሱ ተጣሉ፡፡ ሣቅና ጨዋታ ደራ፡፡ ወደ 8፡30 አካባቢ የቡናው ሥርዓት እንደ መጠናቀቅ አለ፡፡ ዕቃዎች ተነስተው ክፍሉ በመጠኑ ተፀዳና የሽያጭ ሰራተኞቹ "በሉ ተጫወቱ ጓደኛሞች፣ በጣም እንደተነፋፈቃችሁ ያስታውቅባችኋል" ብለው ሹልክ ሹልክ እያሉ ወጡ፡፡ አጠገቤ የተቀመጠችውን አፊያን ትኩር ብዬ አየኋት፡፡ ዛሬ የፊት መሸፈኛዋ ኒቃብ ባይኖርም ጥቁሩ አባያ ግን እንዳለ ነው፡፡ በመጠኑ ውፍረት ከመጨመር በቀር ተክለ ሰውነቷ ብዙም አልተቀየረም፡፡ እርሷም ዝም ብላ ስታየኝ ቆይታ "በጣም ነው የምወድሽ ሜሪዬ፣ ደግሞም በጣም ታስፈልጊኛለሽ" አለችኝ ትክዝ ብላ፡፡ ቀጥሎ የነበረውን የአፊያ ትረካ በእንዲህ ያለው አጭር ጽሑፍ በምልዐት ለመሸፈን ይቸግራል፡፡
አፊያ በየመሐሉ እያለቀሰች፣ አንዳንዴም እየሳቀች ለ3 ሰዓታት ያህል ስታወራኝ ቆየች፡፡ ባለፉት ጊዜያት ስለሆነው ሁኔታ፣ ስለ ህመሟ፣ ስለ ጋብቻዋ፣ ስለ ባሏ፣ ስለ ቤተሰቧ፣ ስለ ሥራዋና ስላላት ዕቅድ ተረከችልኝ፡፡ ንግግሯ የሆነ የመብሰል ነገር ይስተዋልበታል፡፡ 10 ዓመት የቀለም ትምህርት ከመቅሰም የአንድ ዓመቱ የተግባር ልምምድ የተሻለ ዕውቀት ያስጨብጣል እንደሚባለው የገጠማት የሕይወት ውጣ ውረድ ብዙ እንዳስተማራት ታስታውቃለች፡፡ ኤፊ በዕድሜ እኩያዬ ብትሆንም የብዙ ዓመት ታላቄ እስክትመስለኝ ድረስ በአገላለጿና በቁርጠኝነቷ እደመም ጀመር፡፡ ወሬያችን ባያልቅም በግድ እንዲያልቅ አድርገን 12፡00 ሰዓት ላይ ለመሄድ ተነሳሁ፡፡ እርሷ ቤት ካላደረስኩሽ፣ እኔ ዛሬ በፍፁም አይሆንም በሚል አነስተኛ ግርግር ካስነሳን በኋላ ተቃቅፈን ተሰነባበትን፡፡ ሰራተኞቹ በደማቅ ፈገግታ አፊያ ደግሞ ጥቂት መንገድ ከሸኙኝ በኋላ ወደ ቤቴ አመራሁ፡፡ ከእራት በኋላ የኤፊን ትረካ ከብዙ በጥቂቱ ዲያሪዬ ላይ ልፅፈው ሞከርኩ...
"... ሜሪዬ.. ከካምፓስ ስባረር በእንዴት ያለ ንዴት ውስጥ እንደነበርኩ ታውቂያለሽ አይደል? የካምፓሱ ሕይወት፣ ከአንቺ ጋር የነበረኝ ጥብቅ ጓደኝነት፣ ያወራናቸው ቁም ነገሮች፣ አጠቃላይ የአኗኗር ዘይቤዬ ሁሉ አስቀድሞ ከነበረው የተለየና ያልተለመደ ነበረ፡፡ እናም የሆነ ዓይነት የሕይወት ለውጥና ሽግግር ውስጥ እንደነበርኩ ይሰማኝ ነበር፡፡ ስለሆነም ወደ ቤቴ ስመለስ ያውም ከውድቀት ጋር ወደዚያው አሰልቺና ተደጋጋሚ የሕይወት ዑደት የገባሁ መሰለኝና በሆነው ባልሆነው መነጫነጭ አበዛሁ፡፡ በዚያ ላይ ይህን ልበሽ ይህን አትልበሽ፣ ፀጉርሽን ሸፍኚ ተከናነቢ የሚለው ንትርክ ከወላጆቼና ከአንዳንድ ወንድምቼ ጋር ሲደጋገም ራሴን ሁሉ መታመም ጀመርኩ፡፡ ነፃ ሆኜ የማወራው ከእናቴ ጋር ነበርና ለእርሷ ምሬቴን ሁሉ በቁጣ ጭምር እናገር ነበር፡፡ ጫና በበረታብኝ ቁጥር እስልምና በአድልኦ የተሞላ ለሴት ልጅ ከመደለያ ያለፈ ክብር የሌለው እምነት መሆኑን በኃይለ ቃል መናገር ቀጠልኩ፡፡ ካንቺ የሰማሁትን ሎጂካዊ ጥያቄዎች በመጠየቅ እናቴን አፋጥጣት ጀመር፡፡ የረባ ዕውቀትም ሆነ ተፅዕኖ የሌላት እናቴ አንዳንዴ እየሳቀች ብዙ ጊዜም እየተቆጣች "አንቺ ልጅ የማታመጪው ጉድ የለም፣ ኋላ አባትሽ እንዳይሰማና ጉድ እንዳይፈላ" እያለች ታስፈራራኛለች፡፡
ነገሩ በዚህ መንገድ እየተወጠረ መጣ፡፡ አባቴ በሂጃብና አባያ ላይ ማመፄንና አልፌ አንዳንድ ነገር መናገሬን ሰማ፡፡ አንድ ቀን እብድ ሆኖ መጣና ዕድሜዬን ግምት ውስጥ ባልከተተ ሁኔታ ደበደበኝ፡፡ ከዱላው ንግግሩ ስላመመኝ ራሴን መቆጣጠር ተስኖኝ እኔም ተናገርኩት፡፡ ከዚህ በፊት እንደነገርኩሽ አባቴ የናጠጠ ሀብታም ከመሆን ባለፈ የልጅ ሀብታምም ነው፡፡ ከሦሥት ሚስቶቹ 16 ልጆች ወልዷል፡፡ እኔ ለእናቴ ሦሥተኛ ለአባቴ ደግሞ አሥረኛ ልጅ ነኝ፡፡ የእናቴን መገፋትና በደል ስመለከት ከመኖሬ ባለፈ በእስልምናው ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን መድልኦ በሽንገላ ሊያስተባብሉኝ የሚቻል አልነበረም፡፡ ስለሆነም በኃይለ ቃል የእናቴን ሕይወት ለማሳለፍ እንደማልሻ፣ በቁሳቁስም እንደማልደለል፣ ምርጫና ነፃነት ያለኝ ሰብዐዊ ፍጡር እንጂ እንደሚያከፋፍላቸው ሸቀጦች አለመሆኔን ከለቅሶና ከጩኸት ጋር ተናገርኩ፡፡ እናቴና ሌሎች ሰዎች ጭምር በትምህርቴ ወድቄ በመባረሬ ብስጭት ላይ እንደሆንኩና ዕድሜዬም ለኃይለኝነት እንደሚጋብዘኝ እየተናገሩ እኔን ለማባበል አባቴንም ለማረጋጋት ሞከሩ፡፡ ምሽቱን ሁሉ ከሳግና ከእልህ ጋር ስነፈርቅ አመሸሁ፡፡ እርሱም ሲያጉተመትምና ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ሲዶልት ቆየና እራት ቀረበ፡፡ ወዲያው ግን ምን እንደሆነ ሳላውቅ ሸተት ብዬ ወደቅሁና ራሴን ሳትኩ፡፡ ...
(ይቀጥላል)
---------- ማርያማዊት ገብረመድኀኅን ----------
saramareyama.890@gmail.com

ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ