ማክሰኞ 21 ኖቬምበር 2017

የ3ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

*በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!የእግዝአብሔር ፍፁም ሰላም ይብዛላችሁ ይብዛልን_

*ሦስተኛ(3ኛ) ዙር የጠቅላል እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር* _እንደሚከተለው ነው_

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣"አንቺ ሴት ከአንች ጋር ምን አለኝ"? በሚለው ኃይለ ቃል ውስጥ ሴት የሚለው ቃል....ነው??

ሀ/ በእስራኤላውያን የትሕትና አነጋገር ነው።

ለ/ የቁጣ አነጋገር ነው።

ሐ/ ሥጋሽ ከሥጋዬ አጥንትሽ ከአጥንቴ ማለት ነው።

መ/ ሀ እና ሐ መልስ ነው።

*//መልስ//*

መ/ ሀ እና ሐ መልስ ናቸው።
1ኛ👉 በእስራኤላውያን የትሕትና አነጋገግ ነው።

2ኛ 👉አጥንትሽ ካጥንቴ ሥጋሽ ከስጋዬ ማለት ነው። ዘፍ 2፥23 ላይ ማየት ይላልቻ።።

 ጌታችንም  ድንግል ማርያምን አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋሽ ስጋን ከነፍስሽ ነፍስን ነስቼ አካልሽን አካል ባህሪሽን ባህሪ አድርጌ ሰው ሆኛለሁና ማለቱን የሚያመለክ የአክብሮትና የፍቅር ሐይለ ቃል እንደሆነ ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን  ያስተምራሉ።

✅ጥ ተራ (ቁ) 2⃣ሃይማኖት ማለት ምን ማለት ነው? ሃይማኖት ከማን የተሰጠ ሥጦታ ነው??

*//መልስ/*

“ሃይማኖት ወይም እምነት” አምነ አመነ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ዘር ወይም ስም፤ ፤ ሲሆን ትርጉሙም አንድን እውነት መቀበል፤ በአንድ ክፍል ላይ ተስፋ ማድረግ ወዘተ ማለት ነው።
ስለ እምነት ወይም ሃይማኖት ምሥጢራዊ ትርጉም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚከተለው በግልጽ አስቀምጦታል፡
👉 “እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው” ዕብ.11፡1 በዚህ ቃል መሠረት እምነት ተስፋ የምናደርገው ነገር ሁሉ እርግጠኛ ስለመሆኑ፤ የማናየውንም ነገር የሚተርክ የሚያስተምር ነው።

በመቀጠልም ሐዋርያው “ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደተዘጋጁ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን” ዕብ.11፡3 ይላል ። በመሆኑም እምነት ስለፈጣሬ ዓለማት እግዚአብሔር ያለውን
እውነት እንዲሁም ከእርሱ ዘንድ ያለውን ተስፋችንን
የሚያስረዳ፤ የሚያረጋግጥልን እውነት፤ ሁሉንም የምናይበት የልብ መነጽር ነው። ስለዚህ መንፈሳዊውን  ለማወቅና የአምላክን  ለመሳተፍ ማመን እጅግ ተፈላጊና መሠረታዊ ነገር ወይም ምሥጢር ነው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 3⃣ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ  ኢትዮጵያ ከሚለው መጠርያ ስሟ ሌላ ማን ማን እየተባለች ትጠራ ነበር??

*//መልስ//*
1ኛ👉የካም ልጅ ፉጥ በኢትዮጵያ ምድር ስለሚኖር #ፉጥ ተብላለች

2ኛ👉 ቶኔቶር ትባል ነበር ቶኔቶር ማለት ሀገረ እግዚአብሄር ማለት ነው።

 3ኛ👉ሊቀ ነብያት ሙሴ ኢትዮጵያን የኩሽ ምድር እያለ ይጠራት ነበር

4ኛ👉ኢትዮጲስ ተብላለች

5ኛ👉ሳባ የተባለ የኩሽ ልጅ ይኖርባት ስለነበር የሳባ ምድር ትባል ነበር

6ኛ👉ሰብታ ወይም አቢስ ይኖርባባት ስለነበር አቢሲኒያ ተብላለች

✅ጥ ተራ (ቁ) 4⃣ የአስራ ሁለቱ ሐዋርያት ሀገረ ሥብከታቸው የት የት እንደሆነ አስረዳ/ጂ??

*//መልሱን በድምፅ /ከቭዲዮመስዋት/ኦ/ አዳምጡ*

✅ ጥ ተራ (ቁ) 5⃣ በቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ የኦሪት  የሚሰዋባቸው አብያተ ክርስቲያናትን ጥቀስ/ጥቀሽ??

*መልስ*

 (1ኛ)መርጡ ለማርያም

 (2ኛ)ተድባባ ማርያም

(3ኛ)አክሱም ፅዮን

 (4ኛ)ብርብር ማርያም

 (5ኛ)ጣና ቂርቆስ ናቸው

✅ጥ ተራ ( ቁ) 6⃣የጌታችን የመድኃኒታችን 9ኙ ባዕላት የምንላቸው ምን ምን ናቸው??

*//መልስ/፦*

1ኛ👉�ፅንሠት
2ኛ 👉�ልደት
3ኛ👉�ጥምቀት
4ኛ👉� ደብረ ታቦር
5ኛ👉� ሆሳህና
6ኛ👉� ስቅለት
7ኛ👉� ትንሳኤ
8ኛ👉� እርገት.ክርስቲያን
9ኛ👉�ጲራቅሊጦስ ናቸው።

✅ጥ ተራ ( ቁ) 7⃣ቤተ  ክርስቲንያን ስንት ክፍሎች አሏት?? ምን ምን??

*//መልስ//*

1ኛ 👉መቅደስ
2ኛ 👉ቅድስት
3ኛ👉 ቅኔ ማህሌት

✅ ጥ ተራ (ቁ) 8⃣ ሰባቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ የተናራቸው ነገሮች(ሰባቱ አፅረሃ መስቀል የሚባሉት ምን ምን ናቸው??

*//መልስ/*👇

1,,, ኤሉሄ ኤሉሄ ለማ ሰብቅታኒ /አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ,,,, ማቴዎስ 27፥40

2,,,አባት ሆይ የሚያደርገትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ....ሉቃስ 23፥39..

3,,, ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ። ሉቃስ 23፥39

4,,, አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ። ሉቃስ 23፥46...

5,,, እነሆ ልጅሽ...እነሆ እናትህ....ዮሐንስ 19፥26...

6,,,ተጠማሁ፣...ዮሐንስ እና፥28...

7,,,ተፈፀመ...ዮሐንስ 19፥30....

✅ጥ ተራ (ቁ) 9⃣ የቤተ ክርስቲያን አስራ አራቱ/14/ ቅዳሴዎች ምን ምን ናቸው???

*//መልስ//፦*

1ኛ፦ ቅዳሴ ሐዋርያት
2ኛ፦ ቅዳሴ እግዚእ.
3ኛ፦ ቅዳሴ ማርያም
4ኛ፦ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጎድ
5ኛ፦ ቅዳሴ ሰለስቱ
6ኛ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ
7ኛ፦ ቅዳሴ ባስልዮስ
8ኛ፦ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
9ኛ፦ ቅዳሴ ኤጲፋንዮስዲዮስቆሮስ

10ኛ፦ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ
11ኛ፦ ቅዳሴ ቄርሎስ
12ኛ፦ ቅዳሴ ያዕቆብ
13፦ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
14ኛ፦ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ

✅ጥ ተራ (ቁ) 🔟 ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ ሆሳዕና  በአህያ ላይ ለምን ተቀመጠ? ለምንስ በፈረስ ላይ አልተቀመጠም??

*//መልስ//*👇
👉�ትንቢትና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ እጅግ ደስ ይልበሽ። አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ እልእል በይ እነሆ ንጉስሽ ጻድቅና አዳኝ ነው። ትሑትም ሆኖ በአህያም በአህያይቱም ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመልጣ (ዘካ 9፥9) እንዲል።

•ተንኮለኛ ናት ለጠላትዋም ፈረስ አውድቃ ረግጣ ትገድላለች
•ረጋ ብላ መሄ አችልም ትቸኩላለች
•ልትወጣባት ስትልም ታስቸግራለች አትመችም ተነጣጥረህ ነው የምትወጣባት
•ጌታ የወደደውና በትንአምላክ አህያን መረጠ፡፡

በአህያ መቀመጡ
እደተገለጸው•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝብለው ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ መእመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡
•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ  ነው የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ፤እኛ በትእቢት ተይዘን ነው እንጂ በየዋህነት ብንመላለስ እሱ ያድርብን ነበር፡፡ እኛ የእግዚአብሔር ማደርያ ነንና፡፡

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣ጌታችን በመጣ ጊዜ የምንጠየቃቸው "6"ቃላተ ወንጌል የምንላቸው ምን ምን ናቸው??

*//መልስ//*
 👉ተርቤ አላበላችሁኝምምዕራፍ

👉ተጠምቸ አላጠጣችሁኝም

👉 የማቴዎስ ወንጌል  25፥33 -46 ላይሙሉውን መመልከት ይቻላል።

✅ ጥ ተራ (ቁ)1⃣2⃣ በ186 ዓ.ም በፍቼ የተወለዱና ከኢትዮጵያ የመጀምርያ አራት ጳጳሳት አንዱና የምሥራቅ ኢትዮጵያ ጳጳስ የነበሩት። በኋላም ፋሺስት ኢጣሊያ በ1928 ዓ.ም በኢትዮያ ላይ የግፍ ጦርነት ባነሳ ጊዜ እምቢ ለሃገሬ ለሃይማኖቴ በማለታቸው ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም በፋሽስት ኢጣሊያን ሰማዕትነት የተቀበሉት ታላቅ አባት ማን ይባላሉ??

*//መልስ//* 👇

ታሪካቸውን የማንዘነጋው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ናቸው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣3⃣ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "በኩር" የሚባልበት ምክንያት

ሀ/የአብ አንድያ ልጁ ስለሆነ

ለ/ በእስራኤላውያን መጀመርያ ማኅፀን የሚከፍት ልጅ በኩር ስለሚባል

ሐ/ ሞት የማይገዛው ትንሣኤን ለመነሣት እርሱ የመጀመርያ ስለሆነ

መ/ ሁሉም መልስ ነው።

*// መልስ//*

መ/ ሁሉም

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣4⃣እመቤታችን በስደቷ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ረዘም ላለ ጊዜ ያረፈችበት ቦታ__ይባላል??

*//መልስ//*

በጣና ደሴት ሦስት ወር ከአስር(10)ቀን ቆይታለች

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣የቃል ኪዳኑ ታቦት ከማይነቅዝ እንጨት የተሰራና ከውስጥም ከውጭም  በወርቅ የተለበተ መሆኑን፤ የሚያስረዳን የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል የትኛው ነው??

*//መልስ//*

ዘጸ.25፥1-22 ላይ ይነግረናል።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሐዋርያትን ትምህርት 81 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምትቀበል ስትሆን ሦስቱን  አብያተ ክርስቲያን ጉባኤያትንም ትቀበላለች። የምትቀበላቸውን የጉባኤያትን ስም ጥቀስ/ጥቀሽ

*//መልስ//*👇
ኒቂያ  ጉባኤ ፣ ቁስጥንንጥንያና አፌሶን ናቸው የነዚህን ጉባኤያት ውሳኔዎቻቸውን ትቀበላለች። ሌሎች ጉባኤዎችን አትቀበልም።

✅1⃣7⃣የሙሴን ሕግ በብዙ ጥንቃቄ እንተረጉማለን የሚሉና ሰውም ሕጉን እንዳይተላለፍ በማለት የራሳቸውን ትእዛዝና ሥርዓት ያወጡ በዘመነ ካህናት ጊዜ የነበሩ የቤተ  ክርስቲያን ጠላቶች ምን ተብለው ይጠራሉ??

ሀ/ ፈሪሳውያን

ለ/ ሰዲቃውያን

/ ኤሲያውያን

መ/ አይታወቁም

*//መልስ//*

ሀ/ ፈሪሳውያን የሐዋርያት 👉 ሥራ 15÷5 ላይ ይገኛል

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣8⃣አስራ ሦስቱ/ 13/ የጌታችን ህማማተ መስቀል የምንላቸው ምን ምን ናቸው??

*//መልስ//*

13ቱ ሕማማተ መስቀል

1ኛ. ተአስሮ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)
2ኛ. ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)
3ኛ. ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይመውደቅ)
4ኛ. ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድመረገጥ)
5ኛ. ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋርመላተም)
6ኛ. ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
7ኛ. ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)
8ኛ. ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)
9ኛ. አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)
10ኛ. ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
11ኛ. ተቀንዎ በቅንዎት (በችንካር መቸንከር)
12ኛ. ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይመሰቀል)
13ኛ. ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትንመጠጣት)ጊዜ

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣9⃣በሐዋርያት ጊዜ  የነበሩ የመጀመርያዎቹ  መናፍቃን ምን ተብለው ይጠራሉ??

ሀ/ ግንስቲኮች

ለ/ ቢጽ ሐሳውያን

/ አርዮሳውያን

መ/ ሁሉም

*//መልስ//*
*ለ/*👉ቢጽ ሐሳውያን ሐሰተኛ ወንድሞች ይባሉ ነበር። እነዚህም መናፍቃን ከአይሁድ ወገን ክርስትናን በመቀበል ካመኑና ከተጠመቁ በኋላ ተመልሰው ወደ አይሁድ ሃይማኖት ያዘነበሉ ናቸው።

✅ ጥ ተራ (ቁ) 2⃣0⃣ የግዝት በዓላት የማባሉት ስንት ናቸው?? ምን ምን ?

*//መልስ//*👉� አምስት (5) ናቸው
 1ኛ👉� የወልድ በዓል ወር በገባ በ29 ቀን
2ኛ👉�የመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓል ወር በገባ በ21
3ኛ👉�የመላአኩ ቅዱስ ሚካኤል በዓል ወር በገባ በ12 ቀን
4ኛ👉�እለተ ቅዳሚት ሰንበት
5ኛ👉�እለተ እሁድ ሠንበት ክርስቲያስቲያን ናቸው።

_ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አረሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ_
.
_ወስብሐት ለእግዚአብሔር_saramareyama.890@gmail.com

ዓርብ 10 ኖቬምበር 2017

2ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ!

https://youtu.be/okLkhZbzo-M
*በድምፅ ለምትፈልጉ👆👂👀*
*+በፁፍ ለምትፈልጉ👂👇👀*
 *ለሌሎችም ሽር አድርጉ♥✔*

*ሁለተኛ ዙር የጠቅላላ እውቅተ የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር*

*_✝በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ?? ይህ የጠቅላላ እውቀት የቃል የመንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር ነው።_

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣ሐዋርያውያን አበው ከሚባሉት ውስጥ የሆነው የትኛው ነው?_

ሀ/ በርናባስ፣

ለ/ ሄርማስ፣

ሐ/ ቀሌምንጦስ ዘሮም፣
ነው
መ/ አግናጥዮስ (ምጥው አንበሳ)

ሠ/ ሁሉም መልስ

ረ/ ሀ እና ሐ መልስ ናቸው።

*//መልስ//* ሠ/ ሁሉም መልስ ነው።

*_ጥ ተራ (ቁ) 2⃣👉ከ ከጌታችን ከመድኃኒታችን 👉 ትንሳኤ እስከ 70 ዓ.ም ድረስ ያለው ዘመን___*
*👉እንዲሁም 👉ከ 70 እስከ 160 ዓ.ም ያለው ዘመን...እና*
*👉 ከ160 እስከ 312 ዓ.ም ያለው ዘመን*
*ምን ምን በመባል ይታወቃል??  ግለጥ ወይም ግለፅ??*

*//መልስ//*👇

👉ከጌታ ትንሳኤ እስከ 70 አመተምህረት ድረስ ያለው ዘመን ዘመነ ሐዋርያት ይባላል
👉ከ 70 እስከ 160 አመተምህረት ያለው የሐዋርያውያን አባቶቻችን ዘመን ይባላል።
👉ከ160 እስከ 312አመተምህረት ያለው ደግሞ ዘመነ ሰማዕታት በመባል ይታወቃል።

_ጥ ተራ (ቁ) 3⃣ ከቅዱሳት አንስት ወገን ያልሆኑት የትኞቹ ናቸው??_

ሀ/ ኤልሳቤጥና ሐና

ለ/ ጤግላና ጲስ

ሐ/ መግደላዊት ማርያምና ማርያም እንተ እፍረት

መ/ ጲላግያና መሪና

ሠ/ መልስ የለም

*ለ//መልስ//* ሠ/ መልስ የለም ሁሉም ከቅዱሳት አንስት ወገን ናቸው።

_ጥ ተራ (ቁ) 4⃣

*//መልስ//*

*//መልስ//*  ሰማያዊት ኢየሩሳሌም 12 በሮች እና 4 ማህዘን ቅርጽ አሏት በብርሀን የተከበበች ናት።

_ጥ ተራ (ቁ) 5⃣ ከአዳም ጀምሮ አስሩ አበው  የሚታወቁት እነማን ናቸው?? እያንዳንዳቸው ለስንት አመት ያህል በምድር ላይ ኖሩ??_


*//መልስ//* በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ /5/ ላይ የምናገኛቸው ናቸው አንብቡት።

_ጥ ተራ (ቁ) 6⃣ፕሮቴስታንቲዝም በስፋት መንቀሳቀስ የጀመረው መቼ ነው????_

*//መልስ//* በ16ኛው የመቶ  ክፍለ ዘመን በሉተር አስተምሮ መሠረት ሲሆን አስቀድሞ 10ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ብዙ እንቅስቃሴዎች ነበሩ። ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የተለዩ ፕሮቴስታንት በእምነትና (ዶግማና በበዶክትሪን)፣ በአስተተዳደር ትምህርቶች ባለመስማማት የተመሰረተ ድርጅት ነው።


_ጥ ተራ (ቁ) 7⃣የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስቲያን የሚባሉት የትኞቹ ናቸው??_

ሀ/ እስክንድርያ፣ ኢትዮጵያ፣ ዩጎዝላቢያና፣ ኬኒያ

/ አርመን፣ ሕንድ፣ ኢትዮጵያ፣ ናይጀርያ፣ ጃፓን

ሐ/ እስክንድርያ፣ ሕንድ፣ ኢትዮጵያ፣ አርመንና ሮማንያ

መ/ እስክንድርያ፣ ኢትዮጵያ፣ ሶርያ ፣ ሕንድና አርመን።

ሠ/ መልስ የለም

*//መልስ//* መ/ እስክንድሪያ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ሶርያ፣ ሕንድ፣አርመን ናቸው።

*_ጥ ተራ (ቁ) 8⃣ ትክክል / ትክክል አይደለም በማለት መልስ/ ሽ/*

_ምሥጢራትን ለመማር ምሥጢረ ሥላሴን መማር ግድ እንደሆነ ሁሉ ምሥጢረ ሥጋዌን ለመማር ነገረ ማርያም የሚቀድም ትምህርት ነው።_

*//መልስ//* ትክክል ነው።

_ጥ ተራ (ቁ) 9⃣ያዕቆብ በሕልሙ ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋች የወርቅ መሰላል ያየበት ቦታ.._


ሀ/ ካራን

ለ/ ቤርሳቤህ

ሐ/ ቤተልሄም

መ/ ፍኖት..ሎዛ

ሠ/ሁሉም መልስ ነው።

*//መልስ//* መ በፍኖተ ሎዛ ነው።


_ጥ ተራ (ቁ)🔟 ስለ እመቤታችን ኅቱም ድንግልና የተናገረው ነቢይ____ነው.??_


*መልስ*ነ?ነብዩ 👉ሕዝቅኤል ነው።
ሕዝ፵፬፥፩-፫ ወደ ምስራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደመቅደሱ በር አመጣኝ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም ሰውም አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣ቤተክርስቲያን ወደ አንድነት ለመመራት ጥረት የተደረገው ጥረት መቼ ነው??_

*መልስ* 👇

በቤተ ክርስቲያን ላይ ብዙ መለያየትና መከፋፈል ከታየበት ጉባኤ አብዳን ወይም ጉባኤ ከለባት በኋላ በ120/ አመታት የነገሠ የቁስጥንጥንያ ነገሥታት ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት በማለት ወደ አንድነት እንድትመጣ አድርጓል።

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣2⃣ የውላጤ ትምህርት ያስፋፋው። ከሃዲ ማን ተብሎ ይጠራል??_

*መልስ*👉መቅዶኒዎስ ይባላል።

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣3⃣ፍልስፍና ጥንቆላና ምትሕታዊ የነበራቸው እነማን ናቸው??_

ሀ/ ቢጽ ሐሳውያን

ለ/ ግኖስቲኮት .

ሐ/ አርዮሳውያን

መ/ ይሁዳውያን


*//መልስ//* ለ) ግኖስቲኮች ናቸው።

_ጥ ተራ ( ቁ) 1⃣4⃣በጉባኤ ኤፌሶን ለንስጥሮስና ለክህደት ትምህርቱ በሚገባ መልስ የሰጠው ቅዱስ አባት ማነው??_


ሀ/ ቅዱስ ቄርሎስ

ለ/ ቅዱስ እስጢፋኖስ

ሐ/ ቅዱስ ቴዎፍሎስ

መ/ ሁሉም መልስ ነው።

*//መልስ//* ሀ/ ቅዱስ ቄርሎስ

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንን የምትመራባቸው መመርያ ህጎች ስንት ናቸው ምንምን??_

*/መልስ/*

👉ሦስት ናቸው እነርሱም፦

👉ዶግማ
👉ያቄን
👉ትውፊት

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣የእመቤታችን አባት  ኢያቄን ከነገደ__...ሲሆን ቅድስት ሐና ደግሞ ከነገደ.... ናት??_ሌዌ

ሀ/ ሌዊ፣ ይሁዳ

ለ/  ይሁዳ ፣
.
ሐ/ ሌዌ ፣ ብንያም

መ/መልስ የለም

*/መልስ//* ለ/ ይሁዳ&ሌዌ

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣7⃣ከሰባቱ/7/ ሰማያት የመጨረሻው ምን ይባላል የምድር መጨረሻውስአርያም ምን ይባላል??_

*//መልስ//* 👉የሰማይ መጨረሻው ጽርሐ  ይባላል።
👉የምድር መጨረሻው ደግሞ 👉 ኤረር ይባላል።

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣8⃣ የእመቤታችን የሰኔ ጎለጎታ የፃፈው ቅዱስ ማን ነው??_

*//መልስ//*  👉ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው።

_ጥ ተራ (ቁ) 1⃣9⃣ለጌታችን ለመድኃኒታችን  ለእሱሰ ክርስቶስ ያነጠፉለት የቅጠል አይነቶች ስንት ናቸው? ምን ምን ናቸው?_??

*/መልስ* ሁለት አይነት ናቸው። እነርሱም

👉ዘንባባ (የተምር) ዛፍ እና
👉የወይራ ዛፍ ናቸው።

_ጥ ተራ ( ቁ) 2⃣0⃣የተቀደሱታቦር ተራራዎች የምንላቸው ስንት ናቸው? ስማቸውስ??_??

*/መልስ//* 4ናቸው እነሱሰም፦

👉 ደብረ

👉ደብረ ሲና

👉ደበረ ዘይት

👉 ቀራኒዮ ናቸው።


ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል👀👆

1ኛ ዙር የጠቅላይ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

https://youtu.be/Xu2r7YPcEco

👆👂የጠቅላላ እውቀት 1ኛ ዙር ጥያቄና መልስ ውድድር


*✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_ሰላመ  እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ሁሀን_

*❤✍🏻አንደኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት  ጥያቄና መልስ  ነው* _እንደሚከተለው ይቀርባል_፦
📚📚📚📚📚📚📚📚

*✍🏻ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ምርጥ ወይም ምረጭ*👇�

_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር _1⃣የ�አዳም ሰባተኛ ትውልድ  የትኛው ነው??_

ሀ/ አብርሀም
 ለ/ ሄኖክ
የሆነውሐ/ ሙሴ
መ/ ያዕቄብ

*//መልስ//* ለ/ ሄኖክ ነው።


_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር _2⃣አንድ ሰው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሰላምታ ታቀርባለች በማለት መልእክት ቢያደርስ ቤተክርስቲያን የሚለው ቃል ምንን ያመለክታል??

ሀ/  ሕንፃ ቤተክርስቲያንን
ለ/ እያንዳንዱ ክርስቲያንን
ሐ/የክርስቲያኖች አንድነትን
መ/ አይታወቅም።

*//መልስ//* ሐ/ የክርስቲያኖች አንድነት።

_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 3በፊልጵስዩስ⃣የመጀመርያ  ቤተ ክርስቲያን የተሰራችው በማን ከተማ ነው??_

ሀ)በፊልጵስዩስ

ለ) በደማስቆ

ሐ) በአንጾኪያ

መ) መልስ የለም

*//መልስ//* ሀ/ በፊልጵስዩስ ነው።

_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 4⃣የአለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ንቅናቄ ማህበር መቼ ተመሰረተ??_


*//መልስ//* በ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተመሰረተ።

_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 5⃣የመላው  አፍሪካ አብያተ ክርስቲያን አንድነትጉባኤ ጽ/ት ቤት የት ይገኛል??_


*//መልስ//*  ናይሮቢ ይገልኛ።


_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 6⃣ "መለኮት �ሥጋን ዋጠው መጠጠው  ብሎ  በማስተማሩ በሊቀ ጳጳስ ፍላብያኖስ የተወገዘው ማነው?( ማን) ይባላል??_


*//መልስ//* በሁለተኛው የኤፌሶን ጉባኤ
የተወገዘው  አውጣኪ ይባላል።


✍(ጥ) ተራ ቁጥር 7⃣በሥርዓተ ቅዳሴ ጊዜ የማርቆስ ወንጌል ከተነበበ በኋላ ካህኑ "ጀሮ""ያለው መስማትን ይስማ" ይላል የቅዱስ ማቴዎስ፣ የቅዱስ ሉቃስና የቅዱስ ዮሐንስስ ከተነበበ በኋላ ምንም ይባላል???_

*//መልስ//*👇ለደቀ

የማቴ ፦ከተነበበ በኋላ ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም አለ ጌታ  መዛሙርቱ ይላሉ።

የሉቃ፦ ከተነበበ በኋላ ከኦሪትና ከነብያት አንዲቱ ቃል ከምትወድቅ የማይሰና የምድር ማለፍ ይላልቀ።

የዮሐስ፦ ከተነበበ በኋላ በወልድ ያመነ የዘላለም ሕይትወ አለው ይልሉ።

 _✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 8⃣�ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ   ሐዋርያትን ኃይልን ከአርያም እስክትለብሱ በኢየሩሳሌም ቆዩ ለምን አላቸው???_

*//መልስ//* 1ኛ በሰቂለ ሕሌና ለማቆየት

 2ኛ በአጽኖተ በአት መንፈስ ቅዱስ እንዲቀበሉ ለማድረግ

3ኛ በመንፈስ ቅዱስ ባልታደሰ ሰውነት እንዳይመላለሱ ለማድረግ ነው።


ክርስቶስ_✍🏻(ጥ)ተራ ቁጥር 9⃣በቅዱስ መጽሐፋችን ውስጥ ስለ ኢትዮጵያዊ ከተፃፉት መካከል 5ት ጥቀስ/
ሽ..,??

*//መልስ//*👇👇

ትንቢተ ሕዝቅኤል
29፥10
ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።
30፥4
ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል፤ የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ ይወድቃሉ፥ ብዛትዋንም ይወስዳሉ፥ መሠረትዋም ይፈርሳል።
30፥5
ኢትዮጵያና ፉጥ ሉድም የተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።
30፥9
በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ፤ እንደ ግብጽም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል፤ እነሆ፥ ይመጣልና።
38፥5
ፋርስንና ኢትዮጵያን ፉጥንም ከእነርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ፥

ትንቢተ ዳንኤል
11፥43
በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል፤ የልብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።

ትንቢተ አሞጽ
9፥7
የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር፡፡ እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?

ትንቢተ ናሆም
3፥9
ኢትዮጵያና ግብጽ የማይቈጠር ኃይልዋ ነበሩ፤ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ።

ትንቢተ ዕንባቆም
3፥7
የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።

ትንቢተ ሶፎንያስ
2፥12
እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።
3፥10
ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል።

 _✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 🔟�ሐዋርያት መቼ ተጠመቁ ደሙን ተጠመቁ??_

*//መልስ//* በጸሎት ሐሙስ ማታ ሥጋና  ከመቀበላቸው በፊት ከመታጠቢያው ውሃ ጨምሮ ባጠባቸው ገዜ ነው።

_✍🏻(ጥ)ተራ ቁጥር 1⃣1⃣�የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዴትስዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን ገሞራንም በመሰልን ነበር የሚለው ጥቅስ የሚገኘው በ_____መጽሐፍ በምዕራፍ____በቁጥር___ላይ ነው??_


*//መልስ//* ወደ ሮሜ 9፥29
ት/ኢሳያስ 1፥9

ላይ ይገኛል


በም🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 1⃣2⃣ ንጽሕት ድንግል በእውነት አምላክን የወለደች እንደሆነች እንናገራለን እግዚአብሔር ቃል ከእርሷ ሥጋን ተዋሕዷልና። በማለት ስለ እመቤታችን ክብር የመሰከረው አባት ማነው??_

ሀ/ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ
ዘእንዚናንዙ
ለ/ ቅዱስ ሳዊሮስ  ዘአንጾኪያ

ሐ/ ቅዱስ ጎርጎርዮስ

መ/ ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራቅ

*//መልስ//* ሐ/ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ


_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 1⃣3⃣በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ቤተ ክርስቲያንን ታቃጥል የነበረች አይሁዳዊ ፈላሻ ማን ነበረች??_

*//መልስ//* ዮዲት ጉዲት ትባልለች።

_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 1⃣4⃣መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለነብዩ ዳንኤል ስንት ሚስጥራትን ገለጸለት?? ምን ምን??_

*//መልስ//* ሦስት ሚስጢራትን ገልፆለታል
ሰው
1ኛ የቤተ እስራኤል ከ70 አመት በኋላ ወደ እየሩሳሌም መመለስን

2ኛ የኢየሱስ ክርስቶስ  መሆንንና መሞትን

3ኛ የሀሳዊ መሲህ በመጨረሻው ዘመን መንጣቱን ነው።



_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 1⃣5⃣አራቱ (4ቱ) የሴት ነብይት ማን ማን ይባላሉ??_

*//መልስ//* 👇

1ኛ ነብይት የሙሴ እህት ማርያም

2ኛ ነብይት ዲቦራ

3ኛ ነብይት ሃና

4ኛ ነብይት ሑልዳና
ናቸው።

 _✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 1⃣6⃣በቅዱስ መጽሐፍ ላይ ያልተመዘገበ የኢየሱስ ክርስቶስን ታሪክ የያዘ አዋሊድ መጽሐፍ ምን ይባላል??_

*//መልስ//* ታምረ ኢየሱስ ይባላል።

_✍🏻,(ጥ) ተራ ቁጥር። 1⃣7⃣ አዕማደ ሐዋርያት (የምሥጢር ሐዋርያት) ከሚባሉት ውስጥ የሆነው የትኛው ነው??_

ሀ) ዮሐንስ
 ለ) ያዕቆብ
 መ) ጴጥሮስ
 ሠ) ሁሉም

*//መልስ//* መ/ ሁሉም

 _✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 1⃣8⃣ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን ከሰጣቸው መብቶች ውስጥ የትኞቹ ናቸው??_

ሀ) ቤተ ክርስቲያን ከግብር ነጻ ናት።
ለ) ከመንግሥት ገቢ ለቤተ ክርስቲያን የተወሰነ ድርሻ አላት።

ሐ) ዕለተ እሑድ /ሰንበት/ በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ውስጥ ሥራ እንዳይሠራበት አወጀ።

ሐ) ከክርስቲያን ወገን በሕይወቱም ሆነ በሞቱ ንብረቱን ለቤተ ክርስቲያን አወርሳለሁ የሚል ምእመን   ቤተ ክርስቲያን ኑዛዜ የመቀበል፤ ውርስ የመውረስ መብት አላት።

ካለሠ) በክርስቲያኖች መካከል ለሚፈጠሩ አንዳንድ አለመግባባቶች ቢኖሩ ለኤጲስ ቆጶሳት የዳኝነት ሥልጣን ሰጥቷል።

ረ) ሁሉም መልስ ነው።


*//መልስ//* ረ/ ሁሉም መልስ ነው።


_✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 1⃣9⃣ ክህደት የተጀመረው  በ-----------------ነው_

.ሀ) በሳጥናኤል/ዲያብሎስ
ለ) በአርዮስ
ሐ) በይሁዳ
መ) አይታወቅም


*//መልስ//* ሀ በሳጥናኤል ዲያብሎስ

ለ✍🏻(ጥ) ተራ ቁጥር 2⃣0⃣6ቱ ቃለ ወንጌልላት  እነ ማን ናቸው???_


*//መልስ//*

1ኛ በወንድሙ የሚቆጣ ይፈረድበታል


2ኛ ወደ ሴት አይቶ የተመኘ አመነዘረ

3ኛ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚቱተን የሚፈታ የተፈታችውንም ያገባ ያመነዝራል።

4ኛ ፈፅማችሁ አትማሉ

5ኛ ክፉውን በክፉ አትቀዋወሙ

6ኛ ጥላታችሁን ውዱደ


❤❤❤❤❤❤❤

*✍🏻ጥያቄና መልሱ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ ለመታረም ዝጁ ነኝ*

*ወስብኃት ለእግዝአብሔር*
*ወለ ወላዲቱ ድንግል*
*ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን*

እሑድ 29 ኦክቶበር 2017

ድንግል ሆይ፤ ስደትሽ

https://youtu.be/SwwiaieJtD0

♥አጭር መነባንብ♥
////////////////////////

ድንግል ሆይ፤ ስደትሽ
እመብርሃን ሆይ የአምላክ እናት
ከልጅሽ ጋር ሆነሽ ወጣሽ ለስደት
ውሃ ጥም ረሀቡ የአሸዋው ግለት
ሳይገባሽ አየሽ ብዙ እንግልት።
ስቃይሽ ብዙ ነው የደረሰብሽ
በግብፅ በረሃ እንባ እያፈሰስሽ
ልጅሽን እንዳይገሉት አዝለሽው ሸሸሽ
በሄድሽበት ሁሉ ፊት እየነሱሽ
የአምላክ እናት ስትሆኝ ሰዎች ግን ጠሉሽ
ልባቸው ደንድኖ ጠላት አውሮት
በአንቺና በልጅሽ አበዙ እንግልት
የተዓምራት ጌታ ሁሉን እየቻለ
ከእናቱ ጋራ ስደት ተካፈለ

////////////////////////
አንች ሶሎሜ ሆይ እስኪ ተናገሪ
እንዴት እንደነበር ስለ ስደቱ አውሪ
////////////////

ሶሎሜ፦
ያኔማ እንዲህ ነበር ታሪኩ ይዘከር
ድንግል ልጇን አዝላ በግብፅ በረሃ
በየሰው ሁሉ ደጃፍ ስትል ተጠማሁኝ ውሃ።
ጠላት ቀድሞ በልባቸው ገብቶ
ያስነቅፋት ነበር አፋቸውን ከፍቶ
እንባዋ ይፈሳል ቆሞ አያውቅም ከቶ።
ልጄን ይገሉታል እያለች በፍርሃት
እንጓዝ ትላለች በረሃ በረሃ ዳገት ቁልቁለት
ተከታትሎ ሄሮድስ ልጇን እንዳይገልባት።
ከዓኗ እንደሰን ውሃ እንባዋ ይፈሳል
ልቧ በጥልቅ ሐዘን እጅጉን ተጨንቋል
የሄሮድስ ጭካኔ የሰዉ ክፋት
ከበረሃው ጋራ ብዙ አንገላታት
ግብፅ በረሃ ላይ ሲፈፀም ትንቢት
ወደምስራቅ ዞሮ ኢትዮጵያን አያት
በአምላክነቱ በእጁ ባረካት
ልጄ ሆይ ምንድናት ይህች ሀገር
ብላ ጠየቀችው ተገርማ ድንግል
እናቴ እኔና አንቺን ስትቀድስ እምትኖር
ቅድስት ሀገር  አለች ኢትዮጵያን  እምትባል
በደመና ተጭና ኢትዮጵያን ባረከች
አስራት አርጎ ሰጣት ድንግል ተደሰተች
ጌታ ሆኖ ሳለ የሰው ስጋ ለብሶ
ብዙ ተንገላታ ስለእኛ ዐብሶ
የነቢያትን ትንቢት ለመፈፀም ወዶ
ከሰማየ ሰማይ ከድንግል ተወልዶ
ለ42 አውርሃ በግብፅ ተሰዶ
ነጻ አወጣን አምላክ የሰውን ልጅ ወዶ።.
////////////
ድንግል ሆይ፤ በስደትሽ ስደታችንን ባሪኪልን አሜን፫

@ተፃፈ በትዝታ አስፋው

ቅዳሜ 28 ኦክቶበር 2017

አምናና ዘንድሮ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

​አምና እና ዘንድሮ​ 5/13/2009 ዓ.ም

አምና፦ እንደልቤ ስዘል በእሾህ መታነቅ ሞቆኝ
እንዲሁ በባዶ ተስፋ ነገን እየቀጠርኩኝ
ውጥኔ ሳይሞላ ቀርቶ ሌላ ዓለም እየናፈቅሁኝ
አለሁ እላለሁ ሳልኖር የኖርኩ እየመሰለኝ
ለካ ጊዜው አይደለም የቆምኩት እኔው ነኝ
ዛሬ በዳንኪራ በምንዝሩ መንደር
ቤተኛ ሆኛለሁ በመዋል በማደር
ነገ ስለራሱ ይጨነቅበታል እኔ ምን ተዳዬ
በአሜኬላው መኃል ሞቆኛል ኑሮዬ
ገና እልፍ ሰዓታት ከብዙ ቀናት ጋር
ወደፊት እያሉኝ ስለምን ልቸገር
ብዙ ካሰብኩትኝ እሾኩ ይወጋኛል
ሙቀቱን አንስቶ ያቀዘቅዘኛል።

ዘንድሮ፦ አይ! ሞኝ ነህ ወዳጄ
አታየውም እንዴ ያንተ ጊዜ አልቆ ስትወድቅ በእጄ
እኔ ግን አልጣልኩህም ግባ እልሃለሁ ከፍቼልህ ደጄን
እና ምን ወሰንህ በእኔ ጊዜም ቆመህ ያምርሃል መቀለድ?
አይ እንግዲህ!
ይልቅ ይህቺን ዓመት ከሰው ጋር ተጋፍተህ
ደርሰሃል እንዳዲስ አሮጌነትህን ረስተህ
ሞኝ ነህ ወዳጄ ያ ሁሉ እልፍ ጊዜ በከንቱ ያለፈው
በባዶ ተስፋ ውስጥ ቀጠሮ ስትሰጥ ነው
አሁንስ?
እኔ እንደሁ ዘንድሮ የክብር ስሜ ነው
ሁል ጊዜ አዲስ እንደተባልኩኝ ነው
በአንተ ዘመን ላይ የተዘራው ሁሉ
በእኔ ይታጨዳል ፍሬውም ያፈራል
እድሜ ለሰጠው ሰው ዘንድሮንም ያያል

አምና፦ ማየቱንስ አየሁ እግር ጥሎኝ ከደጅህ
አምና እየተባልኩኝ ትውስታ ሆኜልህ
ሞኝ ነህ አትበለኝ እንደኔ ብልጥ የታል
ያለውን ጨርሶ በሰው ይጎለታል
ብልጭ እያለበት ያኔ እኮ ይባላል
ግና ምን ዋጋ አለው ላይመለስ ሄዷል
ካለምንም ትርፍ በኪሳራ ብቻ
በተሰጠው ጊዜ መወላወል ብቻ
የማያልቅ መስሎኝ እድሜና ዘመኔ
ይህቺን አጓጊ ዓለም መች ጠገብኳት እኔ!

ዘንድሮ፦ በል ባለቀው ጊዜህ በንስሀ ታጠብ
ጊዜህን እወቅበት ዓለም ያንተ አይደለም
ይቺን ዓመት ታግሶህ ከእኔ ጊዜ የደረስህ
በብልጠት አይደለም እድሜ የቀጠለልህ
ይልቅ ተነስ ዛሬ በመልካም ጎዳና
የመኸሩ ጌታ መምጫው ቀርቧልና
በእምነት መኖርን ፍጹም እንዳትፈራ
ያ ያለፈው እድሜህ ገፍትሮ ያመጣህ
እንድታፈራ እንጂ አይደለም ሊቆርጥህ
እናም አሁኑኑ ወስን ተረጋግተህ
የበለሷ እጣ ላንተም ከተሰጠህ
በል እንግዲህ አሳየን አብበህ አፍርተህ

አምና፦ እህ!!! ልክ ነህ ወዳጄ አሁን ገና ገባኝ
የእርጅናዬ ምክንያት ያለፈ መባሌ
ለካስ በኃጢአት አልቆ ነው እድሜዬ
ታዲያ ሊቆርጠኝ አልወደደም ምንም ባላፈራም
እድሜ ለንስሀን ከቶ አልነፈገኝም
የማያልቅ በሚመስለው የጊዜ ልኬት ውስጥ
ስዳክር ኖሬአለሁ በድቅድቁ መአጥ
ዛሬስ ይበቃኛል ልመለስ በእንባ
ጌታዬ እንዳይመጣ ንስሀ ሳልገባ
እምቢኝ ዓለም ተይኝ እኔ ትቼሻለሁ
ወደ አባቴ በረት ዛሬውኑ እገባለሁ።

ዘንድሮ፦ እሰይ እሰይ!
 አሁን ገና በሰልህ ሞኝነትህ ለቆህ
የእግዚአብሔር ትእግስት ለቤቱ አብቅቶህ
የወንጌል አርበኛ ምስራች ነጋሪ
መሆን ይገባሃል ሁሉን አስተማሪ
ያለፈውን ዓመት አምና ግብርህን ትተህ
በእኔ በዘንድሮ ፍጹም ተለውጠህ
ልብህን አድሰህ ዓለምን እረስተህ
እግዚአብሔር ይመስገን ይኸው ለዚህ በቃህ።

አምና፦ ያለፈ ያረጀ ያፈጀ የጃጀ ማንነት
ሰንኮፌ ተነቅሎ አዲሱን ሰው ለበስሁ
ይኸው በአምላኬ ፊት ለምስጋና ወጣሁ
ምንም ብትመስልም ዓለም ተብለጭልጫ
የማታልፍ የማትሞት የምትኖር ደምቃ
በመላ በምክንያት በምኞቷ አንቃ
እንዳታስቀርህ አንተ የተኛህ ንቃ
ወግጅልኝ በላት አይበጅህምና ወዳጅነቷ
ይልቅ የሚበጀውን ምረጥ የእምዬ ቤቷን
ያውም በዚህ ዘመን እድሜ ማጣፊያው ባጠረበት
ትውልድ በሰበብ አስባብ ታይቶ በሚጠፋበት
ወገን እንጠይቅ እንረዳ በፍቅርም እንረዳዳ
አባትህን ጠይቅ ተማር ትውፊት ታሪኳን
ትላንት መጥቶ ላንኳኳ ሁሉ አትክፈትለት ልብህን
አጥር ሁንላት መከታ..
በሯም እንዳይዘጋ ትውልድ አትዘናጋ
እራስህን ሥጋህን ከማሸነፍ ጀምር
የአምላክን እናት ይዘህ አዛኝቱን
እመን ታሸንፋለህ ሁሉን
የመዳን ቀን አሁን ነው ነገ አይደለም
ሁላችንም በተሰጠን እድሜ እንጠቀም
በብርቱንነት በጉብዝናችን ወራት
ንስሀ እንግባ እንጀምር አዲስ ህይወት
እድፉ ተወግዶልን እንላበስ አዲስ ሰውነት
እና...


ዘንድሮ፦
እናማ...
መሰረቱን አጽንተህ ከአባት የወረስከውን
ጠብቃት ተዋህዶ እምነትህን
ከአንገትህም እንዳትበጥስ ማእተብህን
በእምነት በሃይማኖት በምግባር
ጸንተን በቤቱ እንኑር
የበደለንን ክሰን ታርቀን
ቅዱስ ክቡር ሥጋወደሙን ተቀብለን
በአንድ ልብ ሆነን የፍቅር ሸማን ተላብሰን
በክርስቶስ ፍቅር እንቀበለው ይንን አዲስ ዘመን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ሥ/ሃ/ኪ/ክፍል መስከረም 2010 ዓ.ም
@ትዝታ አስፋው

መነባንብ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

​አምና እና ዘንድሮ​ 5/13/2009 ዓ.ም

አምና፦ እንደልቤ ስዘል በእሾህ መታነቅ ሞቆኝ
እንዲሁ በባዶ ተስፋ ነገን እየቀጠርኩኝ
ውጥኔ ሳይሞላ ቀርቶ ሌላ ዓለም እየናፈቅሁኝ
አለሁ እላለሁ ሳልኖር የኖርኩ እየመሰለኝ
ለካ ጊዜው አይደለም የቆምኩት እኔው ነኝ
ዛሬ በዳንኪራ በምንዝሩ መንደር
ቤተኛ ሆኛለሁ በመዋል በማደር
ነገ ስለራሱ ይጨነቅበታል እኔ ምን ተዳዬ
በአሜኬላው መኃል ሞቆኛል ኑሮዬ
ገና እልፍ ሰዓታት ከብዙ ቀናት ጋር
ወደፊት እያሉኝ ስለምን ልቸገር
ብዙ ካሰብኩትኝ እሾኩ ይወጋኛል
ሙቀቱን አንስቶ ያቀዘቅዘኛል።

ዘንድሮ፦ አይ! ሞኝ ነህ ወዳጄ
አታየውም እንዴ ያንተ ጊዜ አልቆ ስትወድቅ በእጄ
እኔ ግን አልጣልኩህም ግባ እልሃለሁ ከፍቼልህ ደጄን
እና ምን ወሰንህ በእኔ ጊዜም ቆመህ ያምርሃል መቀለድ?
አይ እንግዲህ!
ይልቅ ይህቺን ዓመት ከሰው ጋር ተጋፍተህ
ደርሰሃል እንዳዲስ አሮጌነትህን ረስተህ
ሞኝ ነህ ወዳጄ ያ ሁሉ እልፍ ጊዜ በከንቱ ያለፈው
በባዶ ተስፋ ውስጥ ቀጠሮ ስትሰጥ ነው
አሁንስ?
እኔ እንደሁ ዘንድሮ የክብር ስሜ ነው
ሁል ጊዜ አዲስ እንደተባልኩኝ ነው
በአንተ ዘመን ላይ የተዘራው ሁሉ
በእኔ ይታጨዳል ፍሬውም ያፈራል
እድሜ ለሰጠው ሰው ዘንድሮንም ያያል

አምና፦ ማየቱንስ አየሁ እግር ጥሎኝ ከደጅህ
አምና እየተባልኩኝ ትውስታ ሆኜልህ
ሞኝ ነህ አትበለኝ እንደኔ ብልጥ የታል
ያለውን ጨርሶ በሰው ይጎለታል
ብልጭ እያለበት ያኔ እኮ ይባላል
ግና ምን ዋጋ አለው ላይመለስ ሄዷል
ካለምንም ትርፍ በኪሳራ ብቻ
በተሰጠው ጊዜ መወላወል ብቻ
የማያልቅ መስሎኝ እድሜና ዘመኔ
ይህቺን አጓጊ ዓለም መች ጠገብኳት እኔ!

ዘንድሮ፦ በል ባለቀው ጊዜህ በንስሀ ታጠብ
ጊዜህን እወቅበት ዓለም ያንተ አይደለም
ይቺን ዓመት ታግሶህ ከእኔ ጊዜ የደረስህ
በብልጠት አይደለም እድሜ የቀጠለልህ
ይልቅ ተነስ ዛሬ በመልካም ጎዳና
የመኸሩ ጌታ መምጫው ቀርቧልና
በእምነት መኖርን ፍጹም እንዳትፈራ
ያ ያለፈው እድሜህ ገፍትሮ ያመጣህ
እንድታፈራ እንጂ አይደለም ሊቆርጥህ
እናም አሁኑኑ ወስን ተረጋግተህ
የበለሷ እጣ ላንተም ከተሰጠህ
በል እንግዲህ አሳየን አብበህ አፍርተህ

አምና፦ እህ!!! ልክ ነህ ወዳጄ አሁን ገና ገባኝ
የእርጅናዬ ምክንያት ያለፈ መባሌ
ለካስ በኃጢአት አልቆ ነው እድሜዬ
ታዲያ ሊቆርጠኝ አልወደደም ምንም ባላፈራም
እድሜ ለንስሀን ከቶ አልነፈገኝም
የማያልቅ በሚመስለው የጊዜ ልኬት ውስጥ
ስዳክር ኖሬአለሁ በድቅድቁ መአጥ
ዛሬስ ይበቃኛል ልመለስ በእንባ
ጌታዬ እንዳይመጣ ንስሀ ሳልገባ
እምቢኝ ዓለም ተይኝ እኔ ትቼሻለሁ
ወደ አባቴ በረት ዛሬውኑ እገባለሁ።

ዘንድሮ፦ እሰይ እሰይ!
 አሁን ገና በሰልህ ሞኝነትህ ለቆህ
የእግዚአብሔር ትእግስት ለቤቱ አብቅቶህ
የወንጌል አርበኛ ምስራች ነጋሪ
መሆን ይገባሃል ሁሉን አስተማሪ
ያለፈውን ዓመት አምና ግብርህን ትተህ
በእኔ በዘንድሮ ፍጹም ተለውጠህ
ልብህን አድሰህ ዓለምን እረስተህ
እግዚአብሔር ይመስገን ይኸው ለዚህ በቃህ።

አምና፦ ያለፈ ያረጀ ያፈጀ የጃጀ ማንነት
ሰንኮፌ ተነቅሎ አዲሱን ሰው ለበስሁ
ይኸው በአምላኬ ፊት ለምስጋና ወጣሁ
ምንም ብትመስልም ዓለም ተብለጭልጫ
የማታልፍ የማትሞት የምትኖር ደምቃ
በመላ በምክንያት በምኞቷ አንቃ
እንዳታስቀርህ አንተ የተኛህ ንቃ
ወግጅልኝ በላት አይበጅህምና ወዳጅነቷ
ይልቅ የሚበጀውን ምረጥ የእምዬ ቤቷን
ያውም በዚህ ዘመን እድሜ ማጣፊያው ባጠረበት
ትውልድ በሰበብ አስባብ ታይቶ በሚጠፋበት
ወገን እንጠይቅ እንረዳ በፍቅርም እንረዳዳ
አባትህን ጠይቅ ተማር ትውፊት ታሪኳን
ትላንት መጥቶ ላንኳኳ ሁሉ አትክፈትለት ልብህን
አጥር ሁንላት መከታ..
በሯም እንዳይዘጋ ትውልድ አትዘናጋ
እራስህን ሥጋህን ከማሸነፍ ጀምር
የአምላክን እናት ይዘህ አዛኝቱን
እመን ታሸንፋለህ ሁሉን
የመዳን ቀን አሁን ነው ነገ አይደለም
ሁላችንም በተሰጠን እድሜ እንጠቀም
በብርቱንነት በጉብዝናችን ወራት
ንስሀ እንግባ እንጀምር አዲስ ህይወት
እድፉ ተወግዶልን እንላበስ አዲስ ሰውነት
እና...


ዘንድሮ፦
እናማ...
መሰረቱን አጽንተህ ከአባት የወረስከውን
ጠብቃት ተዋህዶ እምነትህን
ከአንገትህም እንዳትበጥስ ማእተብህን
በእምነት በሃይማኖት በምግባር
ጸንተን በቤቱ እንኑር
የበደለንን ክሰን ታርቀን
ቅዱስ ክቡር ሥጋወደሙን ተቀብለን
በአንድ ልብ ሆነን የፍቅር ሸማን ተላብሰን
በክርስቶስ ፍቅር እንቀበለው ይንን አዲስ ዘመን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ሥ/ሃ/ኪ/ክፍል መስከረም 2010 ዓ.ም
@ትዝታ አስፋው

አምናና ዘንድሮ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

​አምና እና ዘንድሮ​ 5/13/2009 ዓ.ም

አምና፦ እንደልቤ ስዘል በእሾህ መታነቅ ሞቆኝ
እንዲሁ በባዶ ተስፋ ነገን እየቀጠርኩኝ
ውጥኔ ሳይሞላ ቀርቶ ሌላ ዓለም እየናፈቅሁኝ
አለሁ እላለሁ ሳልኖር የኖርኩ እየመሰለኝ
ለካ ጊዜው አይደለም የቆምኩት እኔው ነኝ
ዛሬ በዳንኪራ በምንዝሩ መንደር
ቤተኛ ሆኛለሁ በመዋል በማደር
ነገ ስለራሱ ይጨነቅበታል እኔ ምን ተዳዬ
በአሜኬላው መኃል ሞቆኛል ኑሮዬ
ገና እልፍ ሰዓታት ከብዙ ቀናት ጋር
ወደፊት እያሉኝ ስለምን ልቸገር
ብዙ ካሰብኩትኝ እሾኩ ይወጋኛል
ሙቀቱን አንስቶ ያቀዘቅዘኛል።

ዘንድሮ፦ አይ! ሞኝ ነህ ወዳጄ
አታየውም እንዴ ያንተ ጊዜ አልቆ ስትወድቅ በእጄ
እኔ ግን አልጣልኩህም ግባ እልሃለሁ ከፍቼልህ ደጄን
እና ምን ወሰንህ በእኔ ጊዜም ቆመህ ያምርሃል መቀለድ?
አይ እንግዲህ!
ይልቅ ይህቺን ዓመት ከሰው ጋር ተጋፍተህ
ደርሰሃል እንዳዲስ አሮጌነትህን ረስተህ
ሞኝ ነህ ወዳጄ ያ ሁሉ እልፍ ጊዜ በከንቱ ያለፈው
በባዶ ተስፋ ውስጥ ቀጠሮ ስትሰጥ ነው
አሁንስ?
እኔ እንደሁ ዘንድሮ የክብር ስሜ ነው
ሁል ጊዜ አዲስ እንደተባልኩኝ ነው
በአንተ ዘመን ላይ የተዘራው ሁሉ
በእኔ ይታጨዳል ፍሬውም ያፈራል
እድሜ ለሰጠው ሰው ዘንድሮንም ያያል

አምና፦ ማየቱንስ አየሁ እግር ጥሎኝ ከደጅህ
አምና እየተባልኩኝ ትውስታ ሆኜልህ
ሞኝ ነህ አትበለኝ እንደኔ ብልጥ የታል
ያለውን ጨርሶ በሰው ይጎለታል
ብልጭ እያለበት ያኔ እኮ ይባላል
ግና ምን ዋጋ አለው ላይመለስ ሄዷል
ካለምንም ትርፍ በኪሳራ ብቻ
በተሰጠው ጊዜ መወላወል ብቻ
የማያልቅ መስሎኝ እድሜና ዘመኔ
ይህቺን አጓጊ ዓለም መች ጠገብኳት እኔ!

ዘንድሮ፦ በል ባለቀው ጊዜህ በንስሀ ታጠብ
ጊዜህን እወቅበት ዓለም ያንተ አይደለም
ይቺን ዓመት ታግሶህ ከእኔ ጊዜ የደረስህ
በብልጠት አይደለም እድሜ የቀጠለልህ
ይልቅ ተነስ ዛሬ በመልካም ጎዳና
የመኸሩ ጌታ መምጫው ቀርቧልና
በእምነት መኖርን ፍጹም እንዳትፈራ
ያ ያለፈው እድሜህ ገፍትሮ ያመጣህ
እንድታፈራ እንጂ አይደለም ሊቆርጥህ
እናም አሁኑኑ ወስን ተረጋግተህ
የበለሷ እጣ ላንተም ከተሰጠህ
በል እንግዲህ አሳየን አብበህ አፍርተህ

አምና፦ እህ!!! ልክ ነህ ወዳጄ አሁን ገና ገባኝ
የእርጅናዬ ምክንያት ያለፈ መባሌ
ለካስ በኃጢአት አልቆ ነው እድሜዬ
ታዲያ ሊቆርጠኝ አልወደደም ምንም ባላፈራም
እድሜ ለንስሀን ከቶ አልነፈገኝም
የማያልቅ በሚመስለው የጊዜ ልኬት ውስጥ
ስዳክር ኖሬአለሁ በድቅድቁ መአጥ
ዛሬስ ይበቃኛል ልመለስ በእንባ
ጌታዬ እንዳይመጣ ንስሀ ሳልገባ
እምቢኝ ዓለም ተይኝ እኔ ትቼሻለሁ
ወደ አባቴ በረት ዛሬውኑ እገባለሁ።

ዘንድሮ፦ እሰይ እሰይ!
 አሁን ገና በሰልህ ሞኝነትህ ለቆህ
የእግዚአብሔር ትእግስት ለቤቱ አብቅቶህ
የወንጌል አርበኛ ምስራች ነጋሪ
መሆን ይገባሃል ሁሉን አስተማሪ
ያለፈውን ዓመት አምና ግብርህን ትተህ
በእኔ በዘንድሮ ፍጹም ተለውጠህ
ልብህን አድሰህ ዓለምን እረስተህ
እግዚአብሔር ይመስገን ይኸው ለዚህ በቃህ።

አምና፦ ያለፈ ያረጀ ያፈጀ የጃጀ ማንነት
ሰንኮፌ ተነቅሎ አዲሱን ሰው ለበስሁ
ይኸው በአምላኬ ፊት ለምስጋና ወጣሁ
ምንም ብትመስልም ዓለም ተብለጭልጫ
የማታልፍ የማትሞት የምትኖር ደምቃ
በመላ በምክንያት በምኞቷ አንቃ
እንዳታስቀርህ አንተ የተኛህ ንቃ
ወግጅልኝ በላት አይበጅህምና ወዳጅነቷ
ይልቅ የሚበጀውን ምረጥ የእምዬ ቤቷን
ያውም በዚህ ዘመን እድሜ ማጣፊያው ባጠረበት
ትውልድ በሰበብ አስባብ ታይቶ በሚጠፋበት
ወገን እንጠይቅ እንረዳ በፍቅርም እንረዳዳ
አባትህን ጠይቅ ተማር ትውፊት ታሪኳን
ትላንት መጥቶ ላንኳኳ ሁሉ አትክፈትለት ልብህን
አጥር ሁንላት መከታ..
በሯም እንዳይዘጋ ትውልድ አትዘናጋ
እራስህን ሥጋህን ከማሸነፍ ጀምር
የአምላክን እናት ይዘህ አዛኝቱን
እመን ታሸንፋለህ ሁሉን
የመዳን ቀን አሁን ነው ነገ አይደለም
ሁላችንም በተሰጠን እድሜ እንጠቀም
በብርቱንነት በጉብዝናችን ወራት
ንስሀ እንግባ እንጀምር አዲስ ህይወት
እድፉ ተወግዶልን እንላበስ አዲስ ሰውነት
እና...


ዘንድሮ፦
እናማ...
መሰረቱን አጽንተህ ከአባት የወረስከውን
ጠብቃት ተዋህዶ እምነትህን
ከአንገትህም እንዳትበጥስ ማእተብህን
በእምነት በሃይማኖት በምግባር
ጸንተን በቤቱ እንኑር
የበደለንን ክሰን ታርቀን
ቅዱስ ክቡር ሥጋወደሙን ተቀብለን
በአንድ ልብ ሆነን የፍቅር ሸማን ተላብሰን
በክርስቶስ ፍቅር እንቀበለው ይንን አዲስ ዘመን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
ሥ/ሃ/ኪ/ክፍል መስከረም 2010 ዓ.ም
@ትዝታ አስፋው

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...