ማክሰኞ 21 ኖቬምበር 2017

የ10ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ


https://youtu.be/bxtabq_vFB4  👆👆   *_በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

*_ፍፁም የእግዚአብሔር ሰላም የእናታችን የድንግል ማርያም ምልጃና ጥበቃ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን_*

*እነሆ የአስረኛ (10)ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል  ጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ መልስ 👇👀*
////////👇👇/////

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣ሰኔ 30 የሚከበረው  የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ክብረ በዓል ምንንን አስመልክቶ ነው??

*//መልስ//*

👉ሰኔ 30 ልደቱ ለዮሐንስ መጥምቀ መለኮት

በዚህች ቀን የጌታን መንገድ ጠራጊው፤ ሐዋርያው፤ ነብዩ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ የልደት ቀኑ ነው፤ መስከረም 2 አንገቱ የተቆረጠበት ነው ሚያዚያ 15 እረፍቱ ነው፤ አንገቱ ከተቆረጠ በኋላ የተቆረጠች አንገቱ ክንፍ አውጥታ ለ15 ዓመት በሳውዲ አረቢያና አካባቢው ወንጌልን ሰብካለች፤ የካቲት 30 ቀን የዮሐንስ ራስ የተገለጸችበት ቀን ነው። ከነዚህ አራት በዓላት ሁለቱን ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉን አውጥታ በደማቁ ታከብረዋለች እነዚህም ሰኔ 30 ልደቱና መስከረም ሁለት አንገቱ የተቆረጠበትን ቀን ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 👉2⃣ ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶ የመሰረተልን ማንነው??

*// መልስ//*👉እራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 👉3⃣ትውፊት ማለት፦ ምን ማለት ነው?

*//መልስ//*👉ትውፊት የሚለው  ቃሉ የግሪኩ ፓራዶሊስ የሚለው ሲሆን ትርጉሙም መቀበል፣መረከብ ማለት ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 👉4⃣የመጀመርያዎቹ  የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተፃፉት...በ... ነብይ ዘመን ነው??

*//መልስ//*👉በነብዩ ሙሴ ዘመን ነው።

✍ ጥ ተራ(ቁ)👉5⃣አራቱ(4) የቤተ ክርስቲያን አካላት ተብለው የሚጠሩት ማን ማን ናቸው???

*//መልስ//*👉ጳጳሳት፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት እና ምእመናን ናቸው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉6⃣ቅዱስ ጳውሎስ ለደቀ መዛሙርትነት ሲመረጥ እድሜው ስንት ነበር??

*//መልስ//*👉 በ55 አመቱ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉7⃣ቅዱስ ጴጥሮስ ያስተማረባቸውን ቦታዎች ስም ጥቀስ/ጥቀሽ??

*//መልስ//* በከፊል ለመጥቀስ ያህል👉ሶርያ ፣ ገላትያ ፣ ፍልስጤም ፣ ቢታንያ ፣ ኢዮብ ፣ ቂሳርያ ፣ ሊድያ ፣ ሮሜ ፣ እየሩሳሌም ልዳ ፣   ቂሳርያ ፣ ጳንጦስ ፣  ኢስያ ወ.ዘተ ናቸው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉8⃣ በስርአተ ቅዳሴ ጊዜ/ ወንጌል ሲነበብ ሻማ/ጧፍ ለምን ይበራል???

*//መልስ//*👉1ኛ👉ክብር ይግባውና ጌታችና መድኃኒታችን እኔ የአለም ብርሃን ነኝ ስላለን ነው።

2ኛ✔ሐዋርያትና ሰማዕታት ለወንጌል የከፈቱን ዋጋ/መሰዋትነት የምናስበበት ነው። ይህ ማለት ሻማው እየበራ ይቀልጣል ቅዱሳን ሰማዕታትም ለአለም ብርሃን ብለው ደማቸውን ማፍሰሳቸውን ይዘክራል።

✍ጥ ተራ (ቁ)👉9⃣ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለቤተ ክርስቲያን ከፃፏቸው መጽሐፍት ውስጥ ቢያንስ /አምስቱን 5/ቱን ጥቀስ/ጥቀሽ??

*//መልስ//*
በእግዚአብሔር በሰጣቸው በመንፈሳዊ ጸጋ ብዙ መጽሐፍትን እንደ ፃፉ ይነገራል ከነዚያ መካከል፦
👉መጽሐፈ ውዳሴ መስቀል፣ አርጋኖ፣ መሐፈ ሰዓታት፣ መጽሐፈ እንዝራ፣የሰባቱ ጊዜያት የጸሎት መጽሐፍትመዐዛ ቅዳሴው   ወ.ዘተ የመሳሰሉትን  ጽፈዋል።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉🔟እያሱ ማለት ምን ማለት ነው???

*//መልስ//*👉እያሱ ማለት፦ መድኃኒት ማለት ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣1⃣ አሪዎስ ወልድ ፍጡር ነው ብሎ የተናገረበት ምክንያት ምንድነው???

*//መልስ//*👉መ.ምሳሌ ም. 8፥22 እግዚአብሔር ለሥራው የመንገዱ የመጀመሪያ አድርጎ ፈጠረኝ፥ የሚለውን ሃይቃል በመጠቀም ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 👉1⃣2⃣ ጻዲቁ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የትውልድ ሀገራቸው የት ነው?? እናትና አባታቸውስ ማን እና ማን ይባላሉ??

*//መልስ//*👉በመንዝ አውርጃ ነው የተወለዱት👉አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባሉ ነበር። ፍሬ ብሩክና ዮስቴና በህገ እግዚአብሔር በሃማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣3⃣ የመጀመርያው  የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር የነበረው የሐዲስ ኪዳንን መጽሐፍትን ቆጥሮ ያስረከበው ቅዱስ ማን ይባላል???

*//መልስ//*👉ቅዱስ ቀለሚንጦስ (ፊሊጲንስ 4፥1-3 ላይ ይገኛል።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣4⃣ ታምረ ማርያምን የፃፈው ቅዱስ አባት ማን ይባላል??

*//መልስ//*👉ደቅስዮስ ይባላል።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣  አትሮኖስ ማለት ምን ማለት ነው?? ጥቅሙስ ምንድን ነው?? ምሳሌነቱስ ምንድን ነው??

*//መልስ//*👉ልዑካን በቅዳሴ ሰዓት ቅዱሳት መጻሕፍትን ሊያነቡ ያጠቀሙበታል፡፡ መዘምራንም በቅኔ ማሕሌት በአገልግሎት ጊዜ የሚያስፈልጉ መጻሕፍትን በማስቀመጥ የሚዜመውን ያዜማሉ የሚነበበውን ያነቡበታል በብሉያ ኪዳን በደብተራ ኦሪትና በታላቁ ቤተ መቅደስ መጻሕፍት ማንበቢያነት ያገለግል ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳንም በቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት በላዩ ይዘረጉና ያነቡበታል፡፡
ምሳሌነቱም ፡-
አትሮኖስ የጌታ ዙፋን
መጽሐፉ የጌታ አንድም
አትሮኖስ የእመቤታችን
መጽሐፉ የጌታ ምሳሌ ነው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ማህፀን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ተቀምጧልና፡፡

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣6⃣ልጇ ሐዋርያ ቤቷ ቤተ ክርስቲያን የነበርላት ከቅዱሳት አንስት መካከል የሆነች እናት ማን ትባላለች???

*//መልስ//*👉የቅዱስ ማርቆስ እናት ማርያም ነት።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣7⃣⃣ክርስትና በምንነሳበት ጊዜ ሦስት ዓይነት ከረር ያላቸው ክሮች ከአንገታችን ላይ እናስራለን የነዚህን ክሮችን ከረር ጥቀስ/ጥቀሽ ምሳሌነትቱንም ጭምር??

*//መልስ//*👉(1ኛ)ጥቁር ክር፦በክርስትና የምንቀበለው የመከራ ህይወት ምሳሌ ነው (2ኛ)ነጭ ወይም ቢጫ፦በጥምቀት ያገኘነውን የኃጢአት ስርየት የመመስከራችን ምሳሌ ነው (3ኛ)ቀይ ክር፦በክርስቶስ ደም የመገዛታችን ወይም የመዳናችን ምሳሌ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣8⃣  ነገረ ማርያምን የፃፈው ቅዱስ ማን ይባላል??

*//መልስ//*👉ቅዱስ ዮሐንስ አፈወቅ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ)👉1⃣9⃣  ሚስጢረ ትንሳኤ ሙታን ማለት ምን ማለት ነው?? ትንሳኤ ሙታንስ በስንት ይከፈላል??

ሚስጢረ ትንሳኤ ሙታን ማለት በዓለም መጨረሻ የፈጣሪያችውን የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምተን ነፍስና ሥጋችን ተዋህዶ ከመቃብር የምንነሳበትና የዘላለም ሕይወትን የምናገኝ መሆናችንን የምንማርበትና የምናምንበት ምስጢር ነው። ትንሳኤ ሙታን በሁለት(2) የከፈላል እነርሱም፦ ትንሳኤ ዘለክብርና ትንሳኤ ዘለሀሳር በመባል ይታወቃል

✍ጥ ተራ(ቁ)👉2⃣0⃣ ማህበረ ጽዋ ማለት ምን ማለት ነው??

*//መልስ//*👉የተጀመረው በሐዋርያ ዘመን  ሲሆን ምእመናንና ነድያን በአንድነት ተሰብስበው በፍቅር በአንድነት ማአድ የሚካፈሉበት ነው ይከውም በጌታችን ስምና በቅዱሳን ስም መታሰቢያ የሚደረግበት የፍቅር ማአድ ማለት ነው።

*✍ማጠቃለያ መልስ*




saramareyama.890@gmail.com

የ9ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ

https://youtu.be/pm3m3DPMzBQ

👆👆👂

*_✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

_ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን እንደምን ሰነበታችሁ? እንደምንስ አላችሁ??_

_እነሆ የ9ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀትየቃ መንፈሳዊ  የጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ መልስ👇👁_

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣👉ከዘመነ መሳፍንት ቀጥሎ ያለው ዘመን ዘመነ ምን ይባል ነበር??

*/መልስ/*

✍መልስ፡- ከዘመነ መሳፍንት ቀጥሎ ያለው ዘመነ ነገሥት ይባላል፡፡ ልዩነታቸው በዘመነ መሳፍንት የሚፈርድ ንጉሥ የለም፡ በዘመነ ነገሥት ከሕዝቡ መካከል የተመረጠ ንጉሥ አለ፡፡

✔ጥ ተራ(ቁ) 2⃣👉መጽሐፈ ሩትን የፃፈው ? ማነው? መጽሐፉስ ስንት ምዕራፎች  አሉት? ሩትስ ማን ነች?

*/መልስ//*

✍መልስ፡- መጽሐፈ ሩትን የጻፈው ነቢዩ ሳሙኤል ነው፡፡ ሩት በዘመነ መሳፍንት የነበረች ሞዓባዊት ሴት ነበረች፡፡ መጽሐፉም 4 ምዕራፎች አሉት፡፡

✔ጥ ተራ( ቁ)3⃣ 👉"በክርስቶስ ኢየሱስ የእዝአብሔር  ልጆች ናችሁ፣ ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋል፤ ይህንን ቅዱስ ቃል በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናገኘዋለን?? ምዕራፍና ቁጥሩን??

*//መልስ//*

/ገላ. 3፥26_27/

✔ጥ ተራ(ቁ) 4⃣👉
"ጥበብ ቤቷን ሰራች ሰባቱንም ምሶሶዎችንም አቆመች፣ ፍሪዳዎችንም አረደች፣ የወይን  ጠጇንም ደባለቀች፣ ማዕድዋንም አዘጋጀች። ባርያዎቿንም ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ሥፍራ ላይ ጠራች /ምሳ 9፥1/ የሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ሲተነተን✍👉ጥበብ የተባለው ማነው?
👉ቤት የተባለውስ?   👉ምሶሶዎች የተባለው
 ምሥጢራትስ ምንድነው?

👇👇👇👇
ጥበብ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ቤት የተባለችው ቤተ.ክርስቲያን ናት። ምሶሶዎች የተባሉትም ምሥጢረ ቤተ.ክርስቲያን ናቸው ለምሳሌ👉 ምሥጢረ ጥምቀት👉ምሥጢረ ሜሮን 👉ምሥጢረ ንስሀ👉ምሥጢረ ቁርባን 👉ምሥጢረ👉ወዘተ እያልን የምጠራቸው ናቸው።

✔ጥ ተራ(ቁ) 5⃣👉 በፍልስጤማውያንና በእስራኤላውያን መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው??

👇👇👇

✍መልስ፡- እስራኤላውያን በግርዛት ለእግዚአብሔር የተለዩ ሲሆኑ ፍልስጤማውያን ያልተገረዙና በጣዖት የሚያመልኩ ናቸው፡፡

✔ጥ ተራ(ቁ)6⃣👉ሶምሶም ፍልስጤማውያንን እንቆቅልሽ ጠይቋቸው ነበር ለመሆኑ የጠየቃቸው እንቆቅልሽ ምን የሚል ነበር?

👇👇👇👇

✍መልስ፡- ከበላተኛ ውስጥ መብል ወጣ ፣ ከብርቱም ውስጥ ጥፍጥ ወጣ አላቸው፡፡ መሳ.14÷14

✔ጥ ተራ( ቁ) 7⃣👉 ፅዮን የሚለው ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለ4 ነገሮች ተነግሯል ለምን ለምን??

👇👇👇👇👇

↪❤1ኛ ከተማ ጽዮን

✔💟ጥቂቶቹን ጥቅስ ለመግለጽ 《ሚኪ 3 ፡ 12》፣ 《2ኛ ሳሙ 5 ፡ 7》 ፣ 《2ኛ ዜና 5 ፡ 2》 ፣《 ኢሳ 64 ፡ 10》

↪❤2ኛ ሰባተኛይቱ ሰማይ ጽዮን

✔💟ጥቂቱን ለመግለጽ 《መዝ 46/50 ፡ 2》 ፣ 《ራዕ 14 ፡ 1》

↪❤3ኛ ቤተ እስራኤል ጽዮን

✔💟አንዱን ለመግለጽ 《መዝ 149/150 ፡ 1》

↪❤4ኛ ድንግል ማርያም ጽዮን
ጽዮን
✔💟ሰው ሁሉ እናታችን  ይላል በውስጥዋም ሰው ተወልዷልና 《መዝ 86/87 ፡ 5》

✔ጥ ተራ (ቁ) 8⃣👉በሰኔ 20 እና 21 ቀን የሚከበርበት  የእመቤታችን ቅድስት  ማርያምን አመታዊ በዓልን ምክንያት አስረዳ/አስረጅ???

ድንግል👇👇👇👇👇👇

..በዓሉ እንዴት ነው ቢሉ፦       እመቤታችን ባረገች በ4 ዓመት ጳውሎስና በርናባስ ፊልጵስዩስ ገብተው አስተማሩ፤ ሕዝቡም አምነው ተጠመቁ እንግዲህ ወዲህ ወደ ቤተ ጣዖት አትሂዱ አሏቸው የለመድነውን ከከለከላችሁንማ መካነ ጸሎት ስጡን አሏቸው፡፡  እንዲህ ብንላቸው እንዲህ አሉን ብለው ወደ ጴጥሮስና ዮሐንስ ላኩ አልቦ ዘትገብሩ ወኢምንተኒ ዘእንበለ ትዕዛዙ ወምክሩ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጌታችን ፈቃድ አንዳች ልታደርጉ አይገባም እናንተም ጸልዩ እኛም እንጸልያለን ብለው ላኩባቸው፡፡ ሱባዔ ሲጨርሱ በዚህ ዕለት ጌታ በሩቅም በቅርብም ያሉ ደቀመዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ዮሐንስ ጌታዬ ለምን ሰበሰብከን ብሎ ጠየቀ ጌታም በእናቴ ስም ጽንፍ እስከ ጽንፍ አብያተ ክርስቲያናት እንዲታነጹ ፈቃዴ ነውና ሕንጻ ቤተክርስቲያን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው አለው፡፡
   ይህንን ብሎ ወደ ምስራቅ ወሰዳቸው ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፣ በተአምራት አቀራርቦ ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ሠጣቸው እሳት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ /እየተሳቡ/ ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ሠርተውታል፡፡ ከእንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ ብሏቸው ዐረገ፡፡
   በማግሥቱ እመቤታችንን መንበር ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡

✔ጥ ተራ(ቁ) 9⃣👉አምስቱ(፭) ሐራ ሲኦል ነገስታት የሚባሉት ማን ማን ናቸው??

👇👇👇

ፈርኦን በኤርትራ የሰመጠው፣ ሰናክሬም፣ አንጥያኮስ፣ ሔሮድስ፣ ዲዮቅልጥያኖስ ናቸው።

✔ጥ ተራ(ቁ)1⃣0⃣👉አምስቱ(፭) አርዕስተ አበው የሚባሉት ማን ማን ናቸው?  ስማቸውን ጥቀስ/ሽ ?

👇👇👇
አዳም፣ ሄኖክ፣ ኖህ፣ አብርሃም፣ ሙሴ ናቸው።

✔ጥ ተራ (ቁ)1⃣1⃣አምስቱ(፭)ሐብታት የሚባሉት ምን ምን ናቸው???

ሐብተ ፈውስ፣ ሐብተ ክህነት፣ ሐብተ ትንቢት፣ ሐብተ መዊእ፣ ሐብተ መንግስት ናቸው።

✔ጥ ተራ (ቁ)1⃣2⃣✔ አምስቱ (፭)  ህሩያነ ነገስታት የሚባሉት ምን ምን ናቸው???

*/መልስ//*

ሕዝቅያስ፣ ኢዮስያስ፣ ዳዊት፣ ሰለሞን፣ ንግስተ ሳባ/አዜብ/ማክዳ። ናቸው

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣3⃣👉ቃለ ሕይወት ያሰማልን ምን ማለታችን ነው? /ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ማለት ምን ማለት ነው??

*/መልስ/*

//መልስ///👉 ቃለ ህይወት ያልሰማልን ማለት👉 የእግዚአብሔርን ቃል ጠብቀው እንደቃሉ ለኖሩ
 ልብን የምመረምር እኔ ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሥራችሁ ለመክፈል (ራዕ.22፥32) እስክመጣ ድረስ በፍቅር ኑሩ ያለውን ለፈጸሙ ....በአጠቃላይ በጌታ ለኖሩ ፍሬዎች...የሰው ልጅ በክብር በሚመጣበት ጊዜ (ማቴ.25፥31) በጎቹን ከፍየሎች በሚለይበት ጊዜ (ማቴ.25፥34) <<ኑ እናንተ የአባቴ ቡሩካን ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ::>> ብሎ ጌታ የሚፈርደው ፍርድ የሕይዎት ቃል ይባላል::
ሥለዚህ ቃለ ሕይዎት ያሰማልን ማለት ይህን የተወደደ፣ ዘለዓለማዊ  የሚሰጥ ቃል ያሰማልን፤ ከቀኙ ከሚቆሙት ቅዱሳን ይደምርልን እንደማለት ነው።

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣4⃣👉የእግዚአብሔር ጠባይ/ጸባይ ስንል ምን ማለታችን ነው??

*/መልስ/*

// መልስ ///፦የእግዚአብሔር ጠባይ ስንል በማናቸውም  ለእግዚአብሔር  እንጂ ለፍጡር የማይነገር የእርሱ የብቻው የባሕርይው መገለጫ ወይም
በእግዚአብሔር ባህርይ ውስጥ የሚገለጡትን ሁኔታዎች የሚያመለክት ነው።

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣5⃣👉በዓል ማለት ምን ማለት ነው?? የመጀመርያዋ በዓልስ ማናት??

*/መልስ/*

//መልስ ///፦ በአል ማለት፦ አብዐለ፤ አከበረ ፤ አበለጠገ፣ ዕለትን በዓል አደረገ፤ ከሚለው ግስ የወጣ ስም ነው። በቁሙ ሲፈታም የደስታ፤ የዕረፍት ቀን ፣ የዓመት፣ የወር፣ በሳምንት የሚከበር፣ ያለፈ ነገር የሚታሰብበት ተዝካር ማለት ነው።
የመጀመርያዋ በልዓ ቀዳሚት ሰንበት ናት። እግዚአብሔርም ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም፤ እግዚአብሔርሰንበትን ሊያደርገው ከፈጠረው ቀደሰውም በእርሱ ዐርፎአልና> እደተባለ እግዚአብሔር  ለይቶአክብሯታል ቀድሷታልም። ዘፍ. 2፥3 ስለዚህ ይህ የበአል መጀመሪያ ሆነ።

✔ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣👉ቤተ ክርስቲያን የሚለው ቃል ሦስት ትርጉም አለው። ምን ምን ??

*//መልስ//*

1ኛ👉የክርስቲያን መሰብሰቢያ/የጸሎት ቤት

2ኛ👉 እራሱ ሕንፃው ቤተ ክርስቲያን ይባላል

3ኛ👉ምዕመናን ቤተ ክርስቲያን ይባላል

✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣7⃣👉ክብር ይግባውና ጌታችና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ቅዱሳንን ምልጃ ተቀብሏል። ምልጃቸውን ከተቀበለላቸው ቅዱሳን  ቢያንስ ሦስቱን ጥቀስ/ጥቀሽ???

*/መልስ/*

👉የአብርሃምን (ዘፍ 18፥23)
👉የሙሴ የአብርሃም፣የይሳቅ፣እና የያዕቆብን ስም እየጠራ የማለደውን /ዘጸ. 32፥11-13)፣ ሙሴ ለእህቱ ለማርያም ሲል ያቀረበው (ዘኁ. 12፥10)፣ ሳሙኤል ስለ ሕዝቡ ያቀረበውን/ 1ኛ ሳሙ. 7፥5/ ኢዮብ/ ኢዮብ 42፥7/፣ ዳዊት ስለ ሕዝቡ/2ኛ ሳሙ. 24፥17/  ብዙ መቅጥቀስ ይቻላል

ውስጥ✔ጥ ተራ(ቁ) 1⃣8⃣👉
ጉባኤ ቃና ማለት ምን ማለት ነው?? ጉባኤ ቃና በሁለት ክፍል ይከፈላል። ምን ምን ???

*/መልስ/*

 ቃና ማለት የፈጣሪ ጉባኤ ተቃና፣ የቅኔ ትምህርት ተጀመረ፣ ተለካ ጉባኤው ተቃና ማለት ነው። ጉባኤ ጉባኤቃና በሁለት ክፍል ይከፈላል። ይኸውም ግእዝ  ቃና፣ ዕዝል ጉባኤ ቃና ወይም አጭር ጉባኤ ቃና፣ ረጅም ጉባኤ ቃና በመባል ይጠራል።
.

✔ጥ ተራ(ቁ)1⃣9⃣👉የማሕሌት ሰባቱ/፯/ ደረጃዎች የሚባሉት ምን ምን ናቸው???

*/መልስ/*

1ኛ 👉ቁም ዜማ

2ኛ👉ዝማሜ

3ኛ👉ቁም ጸናጽል

4ኛ👉መረግድ

5ኛ👉ጽፋት

6ኛ👉አመላለስ

7ኛ👉ወረብ ናቸው።

✔ጥ ተራ(ቁ) 2⃣0⃣👉
ማሕሌት እንዴት ተጀመረ? ማን ጀመረው? የት ተጀመረ??

*/መልስ/*

ማሕሌት በመላእክት ዘንድ እንደተጀመረ ጀማሪዎችም እነርሱ በሆናቸውን የቃሉ ትርጓሜ ምስጋና ማለት መሆኑን ቅዱሳት በጻሕፍት ይነግሩናል።

*ማጠቃለያ መልስ ይህ ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ*

*ወስብኃት ለእግዚአብሔር*

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=689617831227746&substory_index=0&id=391288387727360

👁ፔጅ⤴

https://www.facebook.com/sara.mareyame.54
✍00971 50 17 21 032saramareyama.890@gmail.com

የ8ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የጥያቄና መልስ ውድድር

saramareyama.890@gmail.comhttps://youtu.be/r_wP_d9IlM0

*በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_8ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር_

*_ማጠቃለያ መልስ_*👀

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣ 👉ቅዱስ ዮሐንስ መልእክ የፃፈላቸው ሰባቱ (7)  አብያተክርስቲያናት ማን ማን ናቸው??

*✍/መልስ/*👇

1. ⛪የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን
2.⛪ የሰርሞኔስ ቤተ ክርስቲያን
3. ⛪የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን
4. ⛪የትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን
5. ⛪የሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን
6. ⛪የፍልድልፊያ ቤተ ክርስቲያን
7. ⛪የሎዶቂያ ቤተ ክርስቲያን
"

✍ጥ ተራ (ቁ) 2⃣👉አምስቱ (5) እቀባተ መስቀል የተባሉት እነማን ናቸው በዝርዝር አስረዳ/ጅ??

*✍/መልስ/*👇

👉1ኛ ጣዖት ማምለክ

👉2ኛ አፍቅሮ ነዋይ

👉3ኛ ተጣልቶ አለመታረቅ

👉4ኛ ሰው መግደል

5ኛ👉እናትን እና አባትን አለማክብር ናቸው።

♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ)3⃣👉መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ ተብሎ በእራይ የተነገረው አባት ማን ይባላል??

*✍/መልስ/*👇

👉አፄ ዘርያእቆብ ነው።

♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ) 4⃣👉በሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመርያው ሊቀ ጳጳስ ማን ይባላል??

*✍/መልስ/*👇

👉አባ ሰላማ ከታሳቴ ብርሀን ይባላሉ።

♥♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ) 5⃣👉በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ካሉ የተባረኩ ጋብቻዎች ውስጥ ሁለቱን ጥቀስ(ሽ)

*✍/መልስ/*👇

✍የኢያቆምና የሐና፣ የዘካሪያስና የኤልሳበጥ ጋብቻ

♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ)6⃣👉 በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ዲያቆን እድሜው ስንት ሲሆን ቅስና ይሾማ??

*✍/መልስ/*👇

በሰላሳ አመቱ (30) ይሾማል።

✍ጥ ተራ (ቁ)7⃣👉በኦሪቱ ታቦት የሚባለው ምንድነው ጽላት የሚባለውስ??

*✍/መልስ*/👇
በኦሪቱ ታቦት የሚባለው ጽላት የሚቀመጥበት ማደሪያው ነው። ዘጸ 40፥20-21፣25፥20-22፣መዝ131፥8፣ 2ቆሮ6፥16፣ ዕብ9፥4፣ ራዕ 11፥9 ጽላት  የሚባለው ደግሞ እግዚአብሔር ለሙሴ  አስርቱ ቃላተ ኦሪትን በእጁ የሰጠው ቃሉ ተጽፎ የሚገኝበት ከእብነበረድ የተቀረጸው ነው። ዘጸ31፥18፣24፥12-25፣10፥22አስቀድሞ፣34፥1-29

✍ጥ ተራ (ቁ) 8⃣👉መስዋዕተ ቁርባን ማቅረብ የተጀመረው በማን ነው??

*✍/መልስ/*👇

👉በአባታችን አዳም ነው።

✍,ጥ ተራ (ቁ)9⃣👉 በቅዳሴ ሰዓት ወንጌል ስንሳለም ምን ማለት አለብን??

*✍/መልስ/*👇

👉ነአምን በወንጌክ በቅዱስ እንላለን።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣0⃣👉 ቅጽር ግቢና የውጭ አደባባይ ገበያ ዘርግቶ ንግድ መነገድ ክልክል እንደሆነ  ከሚያስዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በቤተክርስቲያንውስጥ 3ቱን ጥቀሱ???

*✍/መልስ/*👇

👉ኤር 7፥11፣ ማቴ 21፥12-14፣ ማር11፥15-17፣ ሉቃ19፥45-46፣ ዮሐ2፥13-18... እናገኛለን

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣👉ሰባቱ(7) አባቶች የሚባሉት/  ማን ማን ናቸው???

*✍/መልስ/*👇

"ሰባቱ አባቶች"
1ኛ👉ልዑል እግዚአብሔር
2ኛ👉 የንስሐ አባት
3ኛ👉ወላጅ አባት
4ኛ👉 የክርስትና አባት
5ኛ👉የስልጣንየጡት አባት
6ኛ 👉 (የቆብ) አባት
7.ኛ👉የቀለም አባት

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣2⃣👉የክህነት አላማና ጥቅም ምንድነው??

*✍/መልስ/*👇

👉 ሰዎችን ከኃጢአት ከሰይጣን ስራ ሁሉ በመለየት በማስተማር በመቆጣጠር በመጠበቅ በመቀደስና በማንጻት በማናዘዝና በመፍታት
ለጨለማው ብርሃን ለመሆን ፣አልጫ የሆነውን ዓለም ለማጣፈጥ፣ ምስጢራተእንዲሆኑ ቤተክርስትያንን በመፈጸም  ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ማሰጠት የእግዚአብሔር ልጆች የመንግስቱ ወራሾች  ለማብቃትና ድኅነተ ነፍስ ለማሰጠት ፣  እግዚአብሔርን ለምእመናንበቅዳሴና በውዳሴ ለማመስገንና መንፈሳዊ አገልግሎት ለመፈጸም ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣3⃣👉⃣አምስቱ (5) ፍኖተ ኃጢአት የተባሉት እነማን /ምን ምን ናቸው??

*✍//መልስ//*👇

1ኛ👉 ትቢት

2ኛ👉ስስት

3ኛ👉ምቀኝነት

4ኛ👉ስርቆት

5ኛ👉ዝሙት ናቸው።

✍ጥ ተራ (ቁ)1⃣4⃣👉⃣ሥጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ሕይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው። ብሎ የተናገረው አባት ማን ይባላል??

*✍መልስ//*👇

👉ብፁ አቡነ ጎርጎርዮስ ካአል ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣👉ለመጀመርያ ጊዜ ካህን  ሁኖ  የተሾመው ቅዱስ አባት ማን ይባላል???

*✍/መልስ*/👇

👉ካህኑ መልከ ጸዲቅ ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣👉ለመጀመርያ ጊዜ የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው? ወይም የማን መጽሐፍ ነው??

*✍/መልስ//*👇

👉መጽሐፈ ሄኖክ ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣7⃣ሀሌ ሉያ ማለት ምን ማለት ነው???

*✍//መልስ//*👇

👉ሃሌ ሉያ ማለት እግዚአብሔር  ይመስገን ማለት ነው።

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን። ሃሌ ሉያ (መዝሙር 150፥6)

✍ጥ ተራ (ቁ)1⃣8⃣👉 በቅዳሴ ጊዜ 5ት/አምስት መስዋቶች አሉ። ምን ምን ናቸው??

*✍/መልስ//*👇

1ኛ👉 የቁርባን መሰዋት

2ኛ👉 የከንፈር መሰዋት

3ኛ👉 የመብራት መሰዋት

4ኛ👉 የእጣን መሰዋት

5ኛ👉 የሰውነት መሰዋት ናቸው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣9⃣👉 ኤልሻዳይ ማለት
👉ያህዌ ማለት
ምን ማለት ነው የሱሞችን ትርጉም አስረዳ/ጂ??

*✍//መልስ//*👇

ቅ✍🏻_*ኤልሻዳይ*ማለት ምን ማለት ነው??

//መልስ//✔ _ኤልሻዳይ ማለት ሁሉን ቻይ ማለት ነው_
አብርሀምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፦ እኔ ኤልሻዳይ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጹምም ሁን፤
((ዘፈጥረት 17፤1))

✍🏻ያህዌ* ማለት ምን ማለት ነው??.

//መልስ//✍🏻ያህዌ ማለት የነበረ ያለና የሚኖር ማለት ነው።" አብርሃምም ያንን ቦታ ያህዌ ይርኤ ብሎ ጠራው፤ እስከ ዛሬም ድረስ በእግዚአብሔር ተራራ ይታያል ይባላል።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 22:14)

♥♥♥♥♥♥♥

✍ጥ ተራ (ቁ) 2⃣0⃣እምነ ጽዮን ማለት ምን ማለት ነው????

*✍/መልስ//*👇

✍🏻_*እምነ* ጽዮን ማለት ነውምንም ማለት ነው_??

//መልስ//እምነ ጽዮን ማለት እናታታችን ጽዮን ማለት ነው፡፡ በመጀመሪያይቱ የሰው ልጆች ሁሉ እናት ሔዋን አማካኝነት ከርስታ ን ወጥተን መጠጊያ አጥተን ነበግ በዳግማዊ ሔዋን በድንግል ማርያም ደግሞ ወደ ርስታችን ተመልሰናል። እናታችን ጽዮን እንላለን።

♥♥♥♥♥♥♥

*ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነን።*

የ7ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

https://youtu.be/l1IoBZtsdro👂👆

*✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_✍7ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ  ጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ  መልስ።_

✍/ ጥ ተራ (ቁ)1⃣👉 እሕቴ ሙሽራ የተቆለፈ ገነት የተዘጋ ምንጭ የታተመም የውኃ ፈሳሽ ናት"  መኃ 4፥ 10 የሚለው ጥቅስ ምንን ያመለክታል??

ሀ/ የእመቤታችን ፍፁም ድንግልናል

ለ/ እመቤታችን ጌታን መውለዷን

ሐ/ ለእመቤታችን የተሰጠ ቃል ኪዳን.

መ/ የእመቤታችን ስደት

*//መልስ*

👉ሀ/ የእቤባታችን ፍፁም ድንግልናን።

✍ ጥ ተራ (ጥ) 2⃣👉 ከሰው ወገን ለመጀመሪያ  ጊዜ ለእመቤታችን ምስጋና ያቀረበው ____ነው??

ሀ/ ቅዱስ ኢያቄም

ለ/ ቅድስት ሐና

ሐ/ ቅዱስ ዮሴፍ

መ/ ቅድስት ኤልሳቤጥ

*//መልስ//*👇
.
👉መ/ ቅድስት ኤልቤባጥ

✍ጥ ተራ (ቁ) 3⃣👉 ቅዱስ አግናጥዮስ በኤፌሶን ፣ በፊላደልፊያ ፣ በማግኒስያ፣ በቴራሊስ፣ በሮምና  በመሳሰሉት ሀገራት ውስጥ ላሉ ክርስቲያኖች ሰባት መልእክታትን በሰባት ዓይነት አርዕስት ጽፎላቸዋል። እነዚህ ሰባት መልእክታት ምን ምን  ናቸው??

*//መልስ//*

👉 መናፍቃንን በፍፁም መቀዋወም እንደሚገባ።

👉ለሥርዓተ ቤተክርስቲያን መገዛት እንደሚገባ።

👉ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ፍፁም ድንግልና።

👉ስለ ጌታችን ፍፁም ሕማምና መከራ።

👉ስለምሥጢረ ቁርባን።

✍ጥ ተራ (ቁ) 4⃣👉የአለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ጉባኤ ጽ/ቤት የት ይገኛል??

*//መልስ//*

👉በሆላንድ ሀገር  / በጆኔቫ ይገኛል።

.
✍ጥ ተራ(ቁ) 5⃣👉 ከገነት ፈሳሽ ወንዞች መሀል ኢትዮጽያን የከበበው ወንዝ ማን ይባላል?
ከመጽሀፍ ቅዱስ ማስረጃ ጥቅስ ??

*//መልስ*//

👉*ግዮን ይባላል*
*ዘፍ 2:13*

✍ጥ ተራ (ቁ) 6⃣👉የክርስቲያን  የችግርና የመከራ  መፍቻ ምንድነው??

*//መልስ//*

👉ፆም ፀሎት ሥግደት እግዚአብሔርን በትዕግስት ማገልገል ዘ.ዘተ ናቸው።


 ✍ጥ ተራ (ቁ) 7⃣👉ጥቂት የሰሌን ፍሬዎች እየተመገበ  በበረሀ በተጋድሎ ሲኖር የነበረው ፃድቅ ማነው ይባላል ለስንት አመትስ በተጋድሎ  ኖረ??

*//መልስ//*

👉ፃዲቅ አቡናፍር ናችው።

👉በምድር ላይ 60 አመት ኑረዋል።

✍ጥ ተራ(ቁ) 8⃣👉 ጠፈርን የሚያቀዘቅዘው  ወንዝ ማን ይባላል??

*//መልስ//*

👉ዋኖስ ይባልላ።

✍ጥ ተራ(ቁ) 9⃣ 👉እርፈ መስቀል ማለት ምን ማለት ??

*//መልስ//*

👉የጌታችን ቅዱስ  ክቡር  ደሙ የሚሰትበት ማንኪያ ማለት ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣0⃣👉የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ጥናት በስንት ይከፈላል ጥቀስ/ጥቀሽ?

*//መልስ//*

በሦስት ይከፈላል እነርሱም፦ 1ኛ 👉የጥንት ቤተክርስቲያን ታሪክ ጥናት

2ኛ👉የመካከለኛ ቤተ  ታሪክ ጥናት

3ኛ👉አዲስ  ታሪክ ጥናት በመባል ይታወቃሉ።
ክርስቲያን
የቤተክርስቲያን
✍ ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣👉የአጹማት ማውጫ የሚሆኑ 7 ቀመሮች አሉ  እነርሱን በዝርዝር አስምቀጥ / አስቀምጭ??

*//መልስ//*👇

👉ዓውደ እለት

👉ዓውደ ወርቅ

👉ዓውደ አመት

👉ዓውደ ምክቲ

👉ዓውደ ፀሐይ

👉ዓውደ መሀተብ

👉ዓውደ አብይ ይባላሉ።

✍ጥ ተራ(ቁ)1⃣2⃣👉 የቅዱስ ላሊበላ ውቅር ቤተ ክርስቶያኖች  11አሉ የእነርሱን ቅዱሳን ስም ስያሜ  ዘርዝሩ ??

*//መልስ//*

*እነሱም፦*
1ኛ ቤተ መድሀኒአለም
2ኛ ቤተ ማርያም
3ኛ ቤተ መስቀል
4ኛ ቤተ ደናግል
5ኛ ቤተ ጎለጎልታ
6ኛ ቤተ ቀራኒዮ
7ኛ ቤተ ጊዮርጊስ
8ኛ ቤተ ገብርኤል
9ኛ ቤተ አማኑኤል
10ኛ ቤተ መርቀሪዎስ
11ኛ ቤተ አባ ሊባኖስ ይባላሉ።👆🏻

 ✍ጥ ተራ(ቁ)1⃣3⃣👉 ለመጀመርያ ግዜ እግዚአብሔር ይፍታ ያሉት አባት ማን ይባላሉ??

*//መልስ//*

👉አባ ጼጥሮስ ይባላሉ።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣4⃣👉⃣ የቤተክርስቲያንናችን ሊቅ የዜማው ደራሲ ብርሀነ አለም ቅዱስ ያሬድ የመጀመርያው ዜማው ምን በመባል ይጠራል??

*//መልስ//*👇

👉አራራይ ይባላል። አራራይ ማለት፦ የማትጠፋ ማለት ነው።

✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣5⃣👉⃣የብሉይ ኪዳን መጽሀፍ ከእብራይስጥ ቋንቋ ወደ ግሪክ  እነማን ናቸው ?ማን በነገሰ  ዘመን ቀየሩ??

*//መልስ//*👇

*በዘመኑ የነበሩት  7ቱ ሊቃውንት  ናቸው። ጥሊሞስ በነገሰ ዘመን ነው ከእብራይስጥ ወደ ግርክ ያስቀየረውና የቀየሩት።*

ሊቃውንት✍ጥ ተራ (ቁ) 1⃣6⃣👉ኢትዮጵያ የሚለው ቃል የእያንዳንዱን የፊደል ትርጉም ዘርዝሪ/ ዘርዝር??

ለምሳሌ ኢ ማለት
ት ማለት ምን ማለት ነው?

*//መልስ//*

ኢ= ማለት ለሊሁ ተንሣኢ ወለሊሁ አንሣኢ ማለት ነው።

ት= ማለት ትፍሥሕት ወሐሴት ማለት ነው።

ዮ= ማለት የድ የማነ እግዚአብሔር ማለት ነው።

ጵ= ማለት ጵርስፎራ ማለት ነው።

ያ= ማለት አንተ ኬንያሁ ማለት ነው።

ከፊደላት ትርጓሜ የተወሰደ።

✍ ጥ ተራ (ቁ) 1⃣7⃣👉ሊቅና ፃዲቅ አባ ጊዎርጊስ ዘጋስጫ የት ሀገር ተወለዱ በስንት? ዓ.ም ?? ተወለዱ? የእናትና  የአባታቸው ስም ማን ይባላል የመጀመሪያው ድርሰታቸው ምን ይባላል??

*//መልስ//*👇

👉የትውልድ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ሲሆን በ 1357 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሰግላ በተሰኘው ቦታ ተወለዱ አባታቸው ህዝበ ጽዮን ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ አምሀ ጽዮን ይባላሉ። የመጀመርያ ድርሰታቸው አርጋኖን ይባላል ።

✍ጥ ተራ (ቁ)1⃣8⃣👉መጽሐፈ ቀለሚንጦስ ከ81 መጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ሲሆን የጻፉት ቅዱስ አባት ማን ይባላል???

*//መልስ//*👇

👉መጽሐፈ ቀለሚንጦስን የጻፉት ቅዱስ  ቀለሚንጦስ ሲሆን ቅዱስ ቀለሚንጦስ የተወለዱት  ሮም ውስጥ ነው።

 ያደጉትም በሮምና አካባቢዋ ነው። ቅዱስ ቀለሚንጦስ የሮም አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ሲሆን የቅዱስ ጴጥሮስ ረድዕ(ደቀመዝሙር) ነበሩ። ፊሊ 4፥3።  ክህነታቸውንም የተቀበሉት  ከመምህራቸው  ከቅዱስ ጴጥሮስ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 1⃣9⃣👉የዓለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ጉባኤ ዓላማ ምንድን ነው??

*//መልስ//*👇

👉የአለም አብያተ ክርስቲያን አንድነት ጉባኤ  ዋና አላማ፦  ከሁሉም በላይ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ለማቋቋም ሳይሆን ጥላቸውን እንዲቀንስ፣ የሃይማኖት ጦርነት እንዳይኖር የክርስቶስን ሰላም ቤተክርስቲያንየሚፈጠሩትን እንዳታጣ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ በወንድማማችነት የራሳቸው ባላቸው መንፈስ እየተሰበሰቡ በመካከላቸው የተፈጠሩትንና ለወደፊትም  ችግሮች ለማስወገድ ነው።

✍ጥ ተራ(ቁ) 2⃣0⃣👉የፕሮቴስንቲዝም ሃይማኖት መነሻ የሆነው  ማነው??

*//መልስ//*👇

*//መልስ//*👇

👉ማርቲን ሉተር ነው።

*ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል።ስተት ካለብኝ አርሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ!!*

*ወስብኃት ለእግዝአብሔር*saramareyama.890@gamail.com

የ6ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር

saramareyama.890@gamail.com
*✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

6ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር ማጠቃለያ መልስ*❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤❤

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣)👉ዕፀ በለስ ለምን ተፈጠረች ምክንያቱን አስረዳ/አስረጅ???

*//መልስ///* 1ኛ👉 አዳምመስራት ለእግዚአብሔር ያለውን ፍቅር እንዲገልፅ  ይህም ስንል አዳም ትእዛዜን እግዝአብሔርን እወዳዋለሁ ካለ ትእዛዙን ማክበር  የአዳም ፉቅር  ትእዛዝ  ስለነበረበት  ምክንያቱም አምላካችን ከወደድከኝ  ጠብቁ ይላልና            2ኛ👉🏻 እንዲገለፅየአዳም ፉጡርነት ይታወቅይታወቅ ዘንድ ዳቢሎስ ፈጣሪነትን ተመኝቶ ነበር ስለዚህ ዕፀ  በለስን  ምልክት አድርጎ አስቀመጠ   ብሎት ስለነበር  በላይ አምላክ  ለማሳወቅ 
3ኛ👉🏻 የአዳም ነፃ ፈቃዱ  ዘንድ  ግዛምክንያቱም እግዚአብሔር ከገነት ዛፉ ሁሉንሁሉ ብላ ነገር ግን ከአንድቱዋ እፅ በባላህ ቀን የሞት ሞትንsaramareyama.890o@gmail.com  ትሞታለህ ብሎ ነፃ ፈቃድ ሰጥቶት ነበርና።

✍ጥ ተራ ቁ(2⃣)👉ስንት ዓይነት ሰማዕትነት አለ??? ምን ምን??

*//መልስ//*ሦስት ናቸው👉 እነርሱም📚አበይት ሰማህታት
📚ንዑስ ሰማህታት
📚ሊቃውንት ሠማህታት ይባላሉ።

✍ጥ ተራ ቁ(3⃣)👉ንጉስ ቆስንጠንጢኖስ በስንት ዓ.ም ተወለደ በስንት አመቱስ ነገሰ???

*//መልስ//* በ272 ዓ.ም ተወለደ በ18 አመቱ በ316 ዓ.ም  በአባቱ ቦታ ሐምሌ 25 ቀን በ316 ዓ.ም በሮም ምዕራብ ክፍል በገላትያ ነገሰ።

✍ጥ ተራ ቁ(4⃣)👉በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ሙት ያስነሳ ነብይ ማን ይባላል??

*//መልስ//* ነብዩ ኤልያስ ነው።

✍ጥ ተራ ቁ(5⃣)👉ከእመቤታችን አንስቶ ወደ ኋላ ሰባተኛ ትውልድ የሆኑት ማንና ማን ናቸው??

ሀ/ ሲካርና ሔርሜላ

ለ/ ቶናህና ደርዳ

ሐ/ ቴክታና ሄኤሜን

መ/ ቴክታና ጴጥርቃ

ሠ/ ሔርሜላና ጴጥርቃ

*//መልስ//* መ/ቴክታና ጴጥርቃ

✍ጥ ተራ ቁ( 6⃣)👉ቤተ ክርስቲያን የሚለውን ቃል በመጀመርያ የተጠቀመበት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  እንደሆነ ቅዱስ ወንጌል ያስረዳናል። ማቴ. ፩፮፥፩፰። ( ደቀመዛሙርት) ለመጀመርያ ጊዜ ክርስቲያን የተባሉት___ ነውና/ በየት ሀገር ነው?

*// መልስ//* በአንፃኪያ ነው። በዋርያት ሥራ ላይ እናገኘልለን።

✍ጥ ተራ ቁ(7⃣)👉ዘመነ ጰራቅሊጦስ የሚባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ከ____ ቀን ጀምሮ እስኪ ___ ቀን ድረስ ያሉት ቀናት ናቸው።

*//መልስ//*
ዘመነ ጰራቅሊጦስ የሚባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ከ50 ቀን ጀምሮ እስኪ ሠኔ  7 ቀድ ድረስ ያሉት ቀናት ናቸው።

✍ጥ ተራ ቁ(8⃣) 👉እስራኤል በጽኑ ተአምራት ከግብፅ ባርነት በጥተው የኤርትራን ባሕር በተሻገሩ ጊዜ በመዝሙር ለእግዝአብሔር ምስጋና ያቀረበቸው ነብይት ማናት መዝሙሩስ ምን የሚል ነበር??

*//መልስ//* ነብይት  የሙሴእህት ማርያም ናት ንሴብሆ ለእግዝአብሔር የሚለውን መዝሙር ነው የመዘረች።

✍ጥ ተራ ቁ(9⃣)👉በተወለድን ወንዶች በ40 ቀን ሴቶች በ80 ቀን ለምን እንጠመቃለን?? ምክንያቱን አስረዳ/አስረጅ?

*//መልስ//*በ 40 እና በ80 ቀን የሆነበት ምክንያት አዳም በተፈጠረ በ40 ቀን ሔዋን በተፈጠረች በ80 ቀን ገነት እንዲገቡ ስለተፈቀደላቸው ነው (ኩፋ
4፣9)።
እንዲሁም በኦሪት ይደረግ የነበረው ሥርዓት ለሃዲስ
ምሳሌ በመሆኑ(ዘሌ12፣12 1-8. ሉቃ 2፣22)። ልጆችም እንደየጾታቸው በ 40 እና በ 80 ቀን የጸጋ ልጅነት ያገኛሉና ነው።(ዘሌ 12፣1-8)።

✍ጥ ተራ ቁ(🔟) የግብፅ መንበር በዱቅስ ማርቆስ ሲጠራ የኢትዮጵያ መንበር በማን ይጠራል??

*//መልስ//* በመንበረ ተክለ ሃይማኖት ይጠልራ።

✍ጥ ተራ ቁ( 1⃣1⃣) ማሕሌተ ጽጌን የደረሱት ታላቁ ሊቅ ማን ናቸው??

*//መልስ//*አባ ጽጌ ድንግል ናቸው ሙሉ ታኩን ገድለ ዜና ማርቆስ ላይ ይመልከቱ።

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣2⃣) ኤፍታህ ማለት ምን ማለት  ነው??

*//መልስ//* ተከፈት ማለት ነው። 👉የማርቆስ ወንጌል (7፥35-36) ላይ ይገልኛ።

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣3⃣)👉አቡነ  ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከግብፅ  ሲመጡ ያረፉበት /የተቀመጡበት ቦታ የት ነው?? የተቀበሩበት ቦታስ የት ነው??

*//መልስ//* የተቀመጡበት ቦታ ዝቋላ ደብረ ከዋክብት ሲሆን የተቀበሩበት ቦታ ምድረ ከብድ ይባላል።

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣4⃣)👉ሰባቱ ሰማያት የሚባሉትን ከታች ወደ ላይ ጥቀስ???

*//መልስ//* ኤረር፣ ራማ፣ ኢዮር፣ አለም፣ መላእክት፣ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት፣ ሰማይ ውዱዝ፣ ጽርሐ አርያም፣  ናቸው።

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣5⃣)👉ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠምቆ ከፆመ በኋላ በመጀመሪያ ያደረገው ታአምር ምንድነው??

*//መልስ//* የቃና ዘገሊላውን ተአምር። የዮሐንስ ወንጌል 2፥1_12 ላይ ይገልኛ።

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣6⃣)👉ሐዋርያት ለመጀመርያ ጊዜ ተሰብስበው ውሳኔን ያስተላለፉት መቸ ነው???

*//መልስ//* በማቲያስ ምርጫ ጊዜ የሐዋርያት ሥራ 1፥15-26 ላይ ይገልኛ።

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣7⃣)👉ኢየሱስ ክርስቶስ  አርባ ቀንና ሌሊት ከፆመ በኋላ ድል ያደረገው ሦስት ታላላቅ ኃጢአቶች ምን ምብ ናቸው??

*//መልስ//*፩ኛ  ስስት፣ ፪ኛ ትዕቢት፣ ፫ኛ ገንዘብ መውደድ። የማቴዎስ ወንጌል 4፥1-15 ላይ ይገኛል።

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣8⃣) 👉ከስምንቱ የአቢይ ፆም ሳምንታት የመጀመርያው ሳምንት ሁለት ስን አለው ምንና ምን ናቸው??

*//መልስ//* ጾመ ሕርቃንና ዘወረደ  በመባል ይታወቃል።

✍ጥ ተራ ቁ(1⃣9⃣)👉ከ36ቱ ቅዱሳን አንስት አንዷ የሆነቸው የአስቆሮቱ ይሁዳ እናት ስሟ ማን ይባላል??

*//መልስ//* ሣራ/ሶፍያ/ ትባላለች

✍ጥ ተራ ቁ(2⃣0⃣)👉በቅዱስ ቅባት ተቀብተው የነገሡ ፬(4) ነገስታት ማን ማን ናቸው??

*//መልስ//* ሳኦል፣ዳዊት፣ አዛኤልና ኢዩ ናቸው

*❤ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ*

*ወስብኃት ለእግዝአብሔር*

የ5ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የማጣሪያ ውድድር

https://youtu.be/wlZ-cp5t-dE


*በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን*

_❤ውድ ተወዳጆች ሆይ እንደምን ቆያችሁ?? ሰላማችሁ ብዝት ይበል አሜን፫_

*5ኛ ዙር የማጠርያ/ የማበላለጫ የተወዳዳሪዎች ጥያቄ የማጠቃለያ መልስ እንደሚከተለው ይቀርባል፦*👇
፨፨፨፨፨፨፨♥♥♥፨፨፨፨፨


✍የጥ ተራ (ቁ) 1⃣  ✔መልስ✔ ጌታችና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ ከአብርሀምና ከዳዊት ዘር መወለዱን ለማስረዳት ከአብርሃም እስከ ቅድስት ድንግል ማርያም ድረስ በሰፊው ስለ ፃፈው ከጥንት ጀምሮ ማቴዎስ በገጸ-ሰብእ ተመስሏል። ከሦስቱ ወንጌላውያን ይልቅ በማቴዎስ ወንጌል ክርስቶስ ወልድ እጓል እመሕያው ልጅ በመባል ብዙ ጊዜ ስለተጠራ ለማቴዎስ የገጸ-ሰብእ ምልክት ካሰጡት ምክንያቶች አንዱ ነው።

✍የጥ ተራ( ቁ) 2⃣✔  መልስ✔ ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያና ወንጌላዊ እንደዚሁም ሰማዕት ነው። ቅዱስ ማርቆስ በአንበሳ ተመስሏል ጌታችንተብሎ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  አሸናፊው የይሁዳ አንበሳ  መሰየሙን በራዕይ ዮሐንስ ተጽፏል(፭) ቅዱስ ማርቆስ በአንበሳ የተመሰለበት ዐብይ ምክንያት ደግሞ በግብጽ የነበሩትን የአንበሳ ዕጓል አንበሳ የተባለውን ክርስቶስን በመስበኩ ነው።

✍የ ጥ ተራ(ቁ)✔ መልስ ✔ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ በላም ይመሰላል። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከብቶች በረት መወለዱን በዕለተ ልደቱም የከብት እረኞች ከመላእክት ጋር መዘመራቸውን ከሌሎች ወንጌላውያን ሠፋ አድርጎ ስለሚተርክ ነው። ከዚህም ሌላ ላም በብሉይ ኪዳን የመሥዋዕት እንስሳ ሲሆን ሉቃስም የክርስቶስ መሰዋዕትነት በፊሪዳ ምሳሌ ጽፎታል። በዚህም መሰረት ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ክርስቶስ ቀርነ መድኃኒር እንደሆነ ነቢዩ ዘካርያስየተናገረውን ትንቢት በመግለጽ ስለፃፈ የላም ምልክት እንደተሰጠው መተርጒማን ሊቃውንት ይናገራሉ።



✍የጥ ተራ (ቁ) 4⃣✔መልስ✔ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በንስር ተመስሏል ንስር ከሌሎች አዕዋፍ ሁሉ ተለይቶ ወደ ላይ መጥቶ ይበራል። በላይም ሆኖ በመሬት ላይ ያሉትን ረቂቃን ነገሮች አጣርቶ መመልከት ይችላል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ሲጽፍ ከወንጌላውያኑ አፃፃፍ በተለየ በምሥጢረ ሥላሴ ይጀምራል ስለ ሥጋዌም ሲጽፍ ወደ ላይ መጥቆ በማሰብ ቅድመ ዓለም ስለነበረው ቃል ይተርክና ያ ቀድሞ የነበረውን ቃል ሥጋ ሆነ በማለት ይጽፋል። ቅዱስ ዮሐንስ ረቂቅና ጥልቅ የሆነውን ትምህርት ያስተምር ነበር።ለዚህም "እግዚአብሔር ፍቅር ነው። ክርስቶስ ሕይወት ነው።"የሚሉትን የመሳሰሉት ናቸው።

_ስለ ቃሉ የቃሉ ባለቤት ልዑል አምላካችን የተመሰገነ ይሁን አሜን፫_

*_አውቄው ሳይሆን ከአነበብኩት ገልብጨው ነው። ይልቁንም ከእናንተ የበለጠውን እማራለሁ_*

*ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ መጠየቅ ይችላል*

*ወስብኃት ለእግዚአብሔር*saramareyama.890@gmail.com

የ4ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት መንፈሳዊ የጠያቄና መልስ ውድድር

*✝_በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን_*

 *_አራተኛ (4) ዙር የጠቅላላ እውቀት የቃል መንፈሳዊ ጥያቄና መልስ ውድድር_*

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕፀ መስቀል ላይ ሁኖ  ደሙ ሲፈስ የጌታዬ ደም እንዴት ይፈሳል አያለሁ ብሎ በጽዋ የተቀበለው ሊቀ መላእክት ማነው???.

*//መልስ//*

 ቅዱስ ኡራኤል ነው።

✅ ጥ ተራ (ቁ) 2⃣ አዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከጻፈልን ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ የፍቅር ባህሪያትን ጥቀስ/ሽ

*//መልስ//*

ፍቅር👉 ይታገሳል፣ አይቀናም፣ አይመካም፣ አይታበይም፣አይበዳጭም፣ ሁሉን ያምናል።
1ኛ ቆሮ 13፥4 -7

✅ጥ ተራ (ቁ) 3⃣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር ቅዱስነት፣  ኃያልነት፣ አዋቂነት ጻዲቅነት፣ በጸሎቷ የመሰከረች ሴት/እናት ማናት/ማን ትላባለች??

*//መልስ//*

ቅድስት ሐና/ እመ ሳሙኤል ናት።

✅ጥ ተራ (ቁ) 4⃣ በአንዲት ትል ተበልቶ የመተው ንጉስ ማን ይባላል??

*//መልስ//*

ንጉስ ሄሮድስ

✅ጥ ተራ (ቁ) 5⃣ለመጀመርያ ጊዜ ማዕተብ ያሰረ አባት ማን ይባላል የምን ሀገር ተወላጂ ነው በስንት ዓመተ ምህረት ነው ማዕተብ ማሰር የተጀመረው??

*//መልስ//*.✍🏻

የሶርያ  ተወላጂ አባት ያዕቆብ አልበረዲ ናቸው 500-578 ዓ.ም ነው።

✅ጥ ተራም (ቁ) 6⃣ቤተክርስቲያን ሶስት በሮች አሏት። እነዚህ ሶስት በሮች የምን ምሳሌ ናቸው??

*//መልስ//*.✍🏻 የሶስቱ አበው አባቶች
የአብርሐም.የይስሀቅ. የያዕቆብ ምሳሌ ናቸው።

✅ጥ ተራ (ቁ)7⃣በቤተክርስቲያናችን ምንጣፍ እና መጋረጃ የምን ምሳሌ ናቸው??

*//መልስ.//*✍🏻ምንጣፍ.ምሳሌነቱ ለጌታችን  ሆሳዕና በአርምያ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እያሉ የዘንባባ ዝንጣፊ ያነጠፉለት ምሳሌ ነው።

✅ጥ ተራ (ቁ)8⃣ጌታችንና ኢየሱስ ክርስቶስን ስዕለ አድህኖ መሳል ምክኒያት የሆነው ሠው ማን ነው??

*//መልስ//*.✍🏻በ14-37 ዓመተ/ምህረት ሮምን ይገዛ የነበረው "ጤባሬዪስ ቄሳር ነው።

✅ጥ ተራ(ቁ) 9⃣የመጀመርያው ኢትዮጵያ ጳጳስ በመሾም ወደ ኢትዮጵያ የተላከው የእስክንድርያ ፓትሪያርክ ማን ይባላል??

*/መልስ/*

✍ቅዱስ አትናቴዎስ

✅ጥ ተራ (ቁ)🔟ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታትን ስያሜን አስረዳ/ጅ??

*//መልስ//*

✍ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ስባለመመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

ሐሙስ- አዳም ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ አርብይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ ፡፡

ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት አልሞተምናይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ  ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
ለመቀባት
እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣1⃣በገነት ውስጥ ስንት አይነት ዛፎች ነበሩ??

*//መልስ//*

በገነት ውስጥ 3 አይነት ዛፎች ነበሩ እነርሱም፦👇

✍1ኛ ዕፀ መብል-እንዲበሉት የተፈቀደላቸው ምግብ

✍2ኛ ዕፀ በለስ -እንዳይበሉ የተዘዙት ነው።

✍3ኛ ዕፅ ሕይወት--እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ የሚመገቡት የዘለዓለም ሕይወትን የሚሰጥ ምግብ ነው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣2⃣እግዚአብሔር ሌሎች ፍጥረታትን አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳም አቀንቶ ለምን ፈጠረው??

*//መልስ//*

✍ሌሎችን ፍጥረታት አስጎንብሶ ሲፈጥራቸው አዳምን ለምን አቀንቶ ፈጠረው?፦

👉እርሱ ገዥ እናንተ ተገዥ ናችሁ ሲል ነው፣ እንዲሁም እናንተ ፈርሳችሁ በስብሳችሁ ትቀራላችሁ እርሱ ግን ትንሳኤ ሙታን አለው ሲል አቃንቶ ፈጠረው።

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣3⃣በሐዋርያት ጊዜ የነበሩት ዲያቆናት ስንት ናቸው እነማን ናቸው???
ዲያ/መልስ/*

✍ሰባት (፯) ናቸው እነርሱም

1ኛ ቅዱስ እስሲፋኖስ

2ኛ ቅዱስ ጰርሜናን

3ኛ ቅዱስ ጵሮኮሮስን

4ኛ ቅዱስ ኒቃሮናን

5ኛ ቅዱስ ጢሞናን

6ኛ ቅዱስ ኒቆላዎስን

7ኛ ቅዱስ ፊልጶስን ናቸው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣4⃣መጽሐፈ መነኮሳት የሚባሉት ስንት ናቸው ስማቸውስ??

*//መልስ//*

✍መፅሀፈ መነኩሳት የባሉት ሦስት ናቸው ፦ከምንኩስና በፊትና ከምንኩስና በኋላ የሚነበቡ መፅሀፍት ሲሆኑ እነርሱም ሶስት ናቸው (1ኛ)ፊልኪስዩስ (2ኛ)ማሪስሀቅ እና(3ኛ)አረጋዊ መንፈሳዊ ናቸው።

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣5⃣የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወይም ወንጌል ከፃፉት ቅዱስ ማቴዎስና ቅዱስ ዮሐንስ ከሐዋርያት እንዲሁም ቅዱስ ሉቃስ እና ቅዱስ ማርቆስ ከአርድእት የሆኑበት ምክንያት ምንድን ነው??ለምስ ከሐዋርያት ብቻ ወይም ከአርድእት ብቻ አልፃፉትም??

*//መልስ//*

✔አራቱ ወንጌላውያን ሁለቱ ከአርድእት ሁለቱ ከሐዋርያት መሆናቸው (1ኛ)ስለአርድእት ክብር፦ሐዋርያት ጨርህገ ቢፅፉት አርድእት ለማስተማር በወጡ ጊዜ እኚህማ የውጭ ሰዎች ናቸው የውስጥ ሰዎች ቢሆኑማ ድርጊቱን ህገ ወንጌልን ይፅፉ ነበር ብለው አይሁድ ትምህርታቸውን  እንዳይከለከሉ (2ኛ)ስለወንጌል ክብር፦አርድእት ጨርሰው ቢፅፉት ይህችማ ተርታ ህግ ከመቀበልናት ድርጊቱማ  ሚስጥረ ተዓምራቱን በቤተ ኢያኢሮስ ሚስጥረ ፀሎትን በጌቴ ሰማኔ ሚስጥረ መንግስቱን በደብረ ታቦርሚስጥረ ምፅአቱን በደብረ ዘይት ባዩ ሐዋርያት ልብ ቀርታለች እያሉ አይሁድ ደገኛይቱን ወንጌል ከመቀበል እንዳይከለከሉ

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣6⃣ማቴ 2፥5-6" ..አንቺ ቤተልሔም የይሁድ ምድር ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም ሕዝቤ እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣል"" ተብሎ ሚኪያስ(5፥2) የተነገረው ትንቢት በሐዲስ ኪዳን ከጌታችን ልደት ጋር ያለው ሚስጢራዊ ንፅፅር ምንድን ነው??

*//መልስ//*

✍(1ኛ)ለጊዜው ህዝቡን የሚጠብቅ መስፍን ዘሩባቤል ነግሶባታል ፍፃሜው ግን ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተወልዷል (2ኛ)ዘሩባቤል አህዛብ ገብረውለታል ለኢየሱስ ክርስቶስም ሰብአ ሰገል ገብረውለታል (3ኛ)ዘሩባቤል በቤተልሔም ድንኳን ተክሎባታል በክርስቶስ ጊዜም የብርሃን ድንኳን ተተክሎባታል ይህ ነው ምስጢራዊ ንፅፅሩ

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣7⃣በብሉይ ኪዳን ለመጀመርያ ጊዜ ስዕል የሳለው ሰው ማን ይባላል የሳለው ስዕልስ ምን ነበር??

*//መልስ//* ✍በብሉይ ኪዳን ዘመን ለመጀመርያ ጊዜ ስዕልን የሳለው ሙሴ ሲሆን   ስዕልም ይህ ነው እግዚአብሔርም ሙሴን አለው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች የሳለውእንደፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤ በሰበርኸቸውም በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ። ዘፀ 34፥1-5 ስታነቡት ሙሉውን ታገኙታላችሁ።

✅ጥ ተራ (ቁ) 1⃣8⃣መጽሐፍ ቅዱስ ሁለት(፪) የኤማውስ መንገደኞች እያለ የሚጠራቸው ሰዎች ማን ማን ይባላሉ??

*/መልስ//*

✍ቅዱስ የሉቃስና ቅዱስ ቀለዮጳ (የሉቃ ወንጌል 24፥13_18 )ላይ ይገኛል

✅ጥ ተራ(ቁ) 1⃣9⃣ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ከአባቴ ብቻ በቀር ልጅም ቢሆን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ የሚያውቅ የለም። ማቴ 24፥ 36 የዚህ ቃል አንድምታዊ ትርጉም አብራራ/አብራሪ)??

"""ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም""" ማቴ24፥36 ይህንን በመጥቀስ ጌታ የሚመጣበትን ቀን አያውቅም ስለዚህ ሁሉን የሚያውቅ ሁሉን የሚችል አምላክ አይደለም የሚሉ መናፍቃን አሉ ነገር ግን ዮሀ ራዕ1፥8'""ያለውና የነበረው የሚመጣው ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክ ""' በማለት ሁሉን የሚችል ከእርሱ በላይ ማንም የሌለ መሆኑን ይናገራል በተጨማሪም ጌታ በማቴ24፥1-55 ባለው የምፅአቱን ዋዜማ እንዴት እንደሆነ ግልፅ አድርጎ ተናግሯል ከዚህ የምንረዳው ነገር ቢኖር ክርስቶስ የሚመጣበትን ቀን ማወቁ ነው ታድያ ስለምን ልጅም ቢሆን አያውቅም አለ? (ሀ)ቀኒቱን ከአዳም ልጆችና እና ከመላእክት ሲለያት ነው እንጂ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ ሲለይ አይደለም የሰው ልጅ ብሎ የአዳምን ልጆች ይጠራልና (ለ)አንድም ወልድ ቅድመ ተዋህዶ አላዋቂ የነበረን ስጋ እንደተዋሐደ ለማስረዳት በእውነት ጌታ የሰውን ባህሪ ባህሪው ማድረጉን ሊያስረዳን ፈልጎ ነው እንዲህ ሲባል ከተዋህዶ በኋላ ስጋ አላዋቂ ነው ማለት አይደለም ከመለኮት ጋር አንድ አካል አንድ ባህሪ ከመሆኑ በፊት ያለውን ሲናገር ነው እንጂ (ሐ)አንድም አብ ለልጁ በመስጠት አውቋታል ወልድ ግን በስራ አላወቃትም ይህም  ማለት ጊዜው እስኪደርስ በልቤ አኖራታለሁ በኋላ ግን በቃልነቴ እናገራታለሁ ሲል ነው አብ ልብ ወልድ ቃል መንፈስ ቅዱስ ህይወት ነውና በቃልነቱ በስራ የሚገልፅበትን ሲናገር ነው (መ)አንድም ወልድ ብቻ ያለ አብ አያውቃትም ሲል ነው ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ አያውቃትም በባህሪ በማወቅአንድ ናቸውና ንባቡ '""ወልድም ቢሆን ያለ አብ ብቻውን""' ስለሚል ነው።

✅ጥ ተራ (ቁ) 2⃣0⃣ ከሐዋርያት ውስጥ ሞትን ያልቀመሰው እና የተሰወረው ቅዱስ ማነው??

*//መልስ//*✍ቅዱስ ዮሐንስ ነው።

*_ውድ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ እህት ወንድሞቼ ማጠቃለያ መልስ ይህን ይመስላል ስተት ካለበት አርሙኝ በማንኛውም ሰዓትና ጊዜ ለመታረም ዝግጁ ነኝ_*

*✍ወስብኃት ለእግዚአብሔርsaramareyama.890@gmail.com

የምዕራፍ አምስት(፭)የ46 የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ

✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡ አሜን! ↪️የምዕራፍ አምስት(፭) 46ኛ ዙር የጠቅላላ እውቀት ጥያቄና መልስ⤵️ 1⃣ ቅዱስ ያሬድ ከመላዕክት የተማራቸው ሦስቱ የዜማ ዓይነቶች ምን ምን ናቸው?ሞገር...